Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ፍሬከናፍር‹‹ባለመዘናጋት ለመጪው ወረርሽኝ ‹በሽታ ኤክስ› መዘጋጀት የግድ ነው››

‹‹ባለመዘናጋት ለመጪው ወረርሽኝ ‹በሽታ ኤክስ› መዘጋጀት የግድ ነው››

ቀን:

የዓለም ጤና ድርጅት፣ መሰንበቻውን በስዊዘርላንድ ዳቮስ፣ በተከናወነው የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ላይ ያሳሰበው፡፡ ኤክስ የሚል ጊዜያዊ ስያሜ በድርጅቱ የተሰጠው በሽታው  ወደፊት በወረርሽኝነት ሊከሰት የሚችል ተብሎ ተገምቷል፡፡  ዓለም አቀፍ የጤና ባለሙያዎች በሽታ ኤክስ ተብሎ ለሚጠራው ገዳይ አዲስ በሽታን አምጪ ተህዋስን ለመግታት መዘጋጀት እንደሚያስፈልግ ማስጠንቀቂያ እያሰሙ መሆኑም ተዘግቧል። በፎረሙ ላይ ‹‹ለበሽታ ኤክስ መዘጋጀት›› በሚል ርዕስ በተደረገው ውይይት ወደፊት ከኮቪድ የከፋ ወረርሽኝ ቢከሰት የጤና መዋቅሩ በቶሎ እንዲመክት እንዴት መዘጋጀት ይቻላል የሚል ነበር። ውይይቱን የመሩት የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም (ዶ/ር) እንደተናገሩት፣ አንዳንድ ሰዎች በሽታው ገና ሳይከሰት ለገዳይ ወረርሽኝ መዘጋጀት ፍርሃትን ሊፈጥርባቸው ቢችልም የሚያዋጣው በቂ ዝግጅት ማድረግ ነው ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። አንዳንድ ባለሙያዎች በሽታ ኤክስ በተቻለ መጠን ከኮቪድ-19 በሃያ ዕጥፍ ገዳይ ሊሆን እንደሚችል ያምናሉ ይላል የሲቢሲ ዘገባ፡፡ በመተንፈሻ አካል ላይ ጉዳት የሚያደርሰው ቀድሞውኑ በእንስሳት ዝርያዎች ውስጥ ሊሠራጭ ቢችልም ወደ ሰዎች ግን ሊተላለፍ አልቻለም።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...