Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበአፍሪካ ዋንጫ የደመቀው ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ

በአፍሪካ ዋንጫ የደመቀው ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ

ቀን:

በአይቮሪኮስት እየተከናወነ የሚገኘው የአፍሪካ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎችን እያስተናገደ ይገኛል፡፡ በዋንጫ ጨዋታ ከፍተኛ ግምት የተሰጣቸው በርካታ ብሔራዊ ቡድኖች በጠዋቱ ተሰናብተዋል፡፡ በአንፃሩ እምብዛም ግምት ያልተሰጣቸው ብሔራዊ ቡድኖች ጥሎ ማለፉን መቀላቀል የቻሉ አሉ፡፡ ጋና፣ ካሜሮን፣ ግብፅ፣ እንዲሁም ሴኔጋል ሻንጣቸውን ሸክፈው ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡

ዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ ጊኒ፣ ኬፕቨርዴና አንጎላ ወደ ሩብ ፍፃሜውን የተቀላቀሉ ብሔራዊ ቡድኖች ናቸው፡፡

በድራማዊ ትዕይንቱ የቀጠለው የዘንድሮ አፍሪካ ዋንጫ አሸናፊውን ለመገመት አደጋች ሆኖ ቀጥሏል፡፡ በአንፃሩ በተለይ የኢትዮጵያውያኑን ቀልብ የገዛው ጉዳይ የዋንጫ ጨዋታ አንዱ ክስተት ሆኗል፡፡ የተለያዩ አኅጉርና ዓለም አቀፍ ውድድሮችን መምራት የቻለው ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ ነው፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የአይቮሪኮስቱን አፍሪካ ዋንጫ ለመምራት ከተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ከተውጣጡ 33 ዳኞች ባምላክ ተሰማ አንዱ ነው፡፡

ባምላክ በአፍሪካ ዋንጫው የምድብ ጨዋታና የጥሎ ማለፍ ጨዋታ መምራት የቻለ ሲሆን፣ ከፍተኛ አድናቆት እያገኘ ይገኛል፡፡ ይህም በተለይ ጨዋታዎችን የሚዳኝበት መንገድ ዕርጋታዊ እንቅስቃሴው፣ እንዲሁም ውሳኔው የበርካቶችን ቀልብ ከመሳቡም በላይ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል፡፡

ባምላክ በምድብ ጨዋታ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ከዛምቢያ፣ እንዲሁም ካሜሮን ከዛምቢያ ያደረጉትን ጨዋታ በብቃት መወጣት ችሏል፡፡

ከዚህም ባሻገር በጥሎ ማለፍ ጊኒ ከኢኳቶሪያል ጊኒ ያደረጉትን ጨዋታ አራተኛ ዳኛ ሆኖ መርቶታል፡፡

በቪዲዮ ቴክኖሎጂ የታገዘው የእግር ኳስ ዳኝነት በርካታ አወዛጋቢ ውሳኔዎችን በአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች ሳይቀር ስህተቶች እየተከሰቱ፣ ክለቦች ክስ ሲመሠርቱም ይስተዋላል፡፡

በዚህም ምክንያት ዳኝነት ከፍተኛ የጥንቃቄ ውሳኔን የሚያሻ የሥራ ዘርፍ መሆኑን ያመለክታል፡፡ ሆኖም ኢትዮጵያዊ ባምላክ የመራቸውን ጨዋታዎች በብቃት መወጣቱን ተከትሎ በተደጋጋሚ በካፍና በፊፋ ተመራጭ እንዲሆን አስችሎታል፡፡

እ.ኤ.አ. በ2003 ዳኝነት የጀመረው ባምላክ በ2009 ኢንተርናሽናል ዳኛ ለመሆን ችሏል፡፡ ከዚህም በ2010 ጂቡቲ ከሱማሌያ ያደረጉትን ጨዋታ በመምራት ዓለም አቀፍ ተሳትፎ ጀመረ፡፡

ባምላክ እ.ኤ.አ. በ2010 የተደረገውን የሴካፋ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታውን ጨምሮ አምስት ጨዋታ በመምራት፣ በተለይ በአፍሪካ ውድድሮች የበለጠ ተቀባይነት እንዲያገኝ ረድቶታል፡፡

በ2009 የፊፋ ዳኛ መሆን የቻለ ሲሆን፣ በ2014 ዓ.ም. የተከናወኑ የፊፋ የማጣሪያ ጨዋታዎችን መርቷል፡፡

በ2022 የካሜሮን አፍሪካ ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ሴኔጋል ከቡርኪና ፋሶ ያደረጉትን ጨዋታ የመራው ባምላክ፣ በበርካታ ተመልካቾች ዘንድ የማይረሳ ክስተት እንዲታወስ አድርጎታል፡፡

ይህም ባምላክ በጨዋታ ሁለት የፍፁም ቅጣት ምቶችን ከወሰነ በኋላ፣ በቪዲዮ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ሁለቱንም ውሳኔዎች መሻሩን ተከትሎ ነበር፡፡

ከዚህም ባሻገር ባምላክ የ2023 የአፍሪካ ሻምፒንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ በሞሮኮ ካዛብላንካ መሐመድ አምስተኛ ስታዲየም 80,000 ተመልካች የሞላበትን ጨዋታ መምራቱ ይታወሳል፡፡

በአንፃሩ ባምላክ የፍፃሜ ጨዋታውን እንደሚመራ ከታወቀ በኋላ፣ በተለይ ከግብፅ ክለብ አል አህሊ ቅሬታ ሲነሳበት ነበር፡፡ ሆኖም ኢንተርናሽናል ዳኛው የሚነሱበትን ትችቶች በመቋቋም ጨዋታውን በብቃት መምራት ችሏል፡፡

ኢትዮጵያዊው ዳኛ በአይቮሪኮስት የአፍሪካ ዋንጫ በተለይ የካሜሮንና ጋምቢያ ጨዋታ ከመራ በኋላ፣ የተለያዩ አስተያየቶች በተለያዩ ድረ ገጽ ላይ ሲሠፍሩ ነበር፡፡

‹‹ኢትዮጵያዊው ዳኛ ካሜሮን ከጋምቢያ ያደረጉትን ጨዋታ በፍጥነትና ጥንካሬ ተሞልቶ ላሳየው ድንቅ ዳኝነት ሊመሠገን ይገባል፤›› በማለት አስተያየታቸውን ከተዘረዘሩት መካከል ነው፡፡

አስተያየት ሰጪዎቹ ሲቀጥሉም፣ ከፍተኛ ጫና በበዛበት ጨዋታ ብዙ ዳኞች ሊቋቋሙት የማይችሉትን፣ የጨዋታ ቆይታውን በመጠበቅ ትክክለኛ ውሳኔዎችን ማሳለፉን አድንቀዋል፡፡

የሶሊዮሎጂ ምሩቁ ባምላክ ከዳኝነት ሥራው ተጨማሪ በክሊኒካል አስተባባሪነት እየሠራ ይገኛል፡፡

የአፍሪካ ዋንጫ ሌላው ድምቀት የሆነው ዋና ዳኛ ባምላክ የአይቮሪኮቱን የፍፃሜ ጨዋታ ለመዳኘት የመጀመሪያ ግምት እየተሰጠው ይገኛል፡፡ የአፍሪካ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ መርቶ የማያውቀው ባምላክ ዘንድሮ ዕድል ሊያገኝ ይገባል የሚሉ አስተያየቶች እየተሰነሰዘሩ ይገኛል፡፡

ባምላክ የአይቮሪኮስቱን አፍሪካ ዋንጫ መምራት ከቻለ፣ ከዚህ ቀደም የፍፃሜ ጨዋታዎችን መምራት የቻለውን ተስፋዬ ገብረየሱስ ታሪክ ይጋራል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...