Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትግራንድ አፍሪካ ሩጫ አሌክሳንደሪያ ቶዮታ የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ማሰሩን አስታወቀ

ግራንድ አፍሪካ ሩጫ አሌክሳንደሪያ ቶዮታ የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ማሰሩን አስታወቀ

ቀን:

በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ በየዓመቱ ሕዝባዊ የጎዳና ሩጫና በሙያቸው የጎላ አስተዋፅኦ ላደረጉ ግለሰቦች ሽልማት የሚያበረክተው ግራንድ አፍሪካ ሩጫ፣ ተሽከርካሪዎችን ለገበያ ከሚያቀርበው አሌክሳንደሪያ ቶዮታ ጋር የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ማሰሩን አስታውቋል። 

የኖቫ ኮኔክሽን ዋና ዳይሬክተር  ጋሻው አብዛ (ዶ/ር)  እንደተናገሩት፣ ከአሌክሳንደሪያ ቶዮታ የተፈረመው ስምምነት፣ ዓመታዊ  ዝግጅቶችን በብቃት ከማዘጋጀት በላይ፣ የግሉ ዘርፍ ከማኅበረሰቡ ጋር ለሚመሠርተው አጋርነት ማሳያ ማሳያ ሆኖ ያገለግላል፡፡

ስምምነቱ በሰሜን አሜሪካ ዳያስፖራ ዘንድ፣ በተለይ ዲሲ፣ ሜሪላንድና ቨርጂንያ አካባቢ በየዓመቱ በሚከናወነው የጎዳና ሩጫ በሚካፈሉ ተሳታፊዎች ዘንድ  አዎንታዊ ተፅዕኖዎችን በመፍጠር እርስ በእርስ እንዲቀራረቡ ከማድረግ  አኳያ ከፍተኛ አስተዋኦ ያበረክታል ተብሏል፡፡ 

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በሌላ በኩል የአሌክሳንደሪያ ቶዮታ ጠቅላላ ሽያጭ ሥራ አስኪያጅ አቶ ያሬድ ማንያለብህ በበኩላቸው፣ ድርጅታቸው ዓመታዊ ውድድሩን ስፖንሰር ማድረጉ፣ ተቋሙ ከንግድ ሥራ ባለፈ ለኅብረተሰቡ እርስ በርስ እንዲቀራረብ ይረዳዋል ብለዋል፡፡

በስምምነቱም መሠረት አሌክሳንደሪያ ቶዮታ ዓመታዊ የሩጫ ውድድሩን የስም የስያሜ በመውሰድ ለአራት ዓመት እንደሚዘልቅ ተብራርቷል።

ግራንድ አፍሪካ ሩጫ ‹‹አብሮነት መሻል ነው›› በሚል መሪ ቃል በየዓመቱ እየተሰናዳ ይገኛል፡፡ በዓመታዊ ውድድሩ ኢትዮጵያውያንን ማሰባሰብ የመጀመርያው ትውልድ ልጆችን ከባህላቸው ጋር የበለጠ ማቀራረብና ለተለያዩ በጎ ሥራዎች ገቢ ማሰባሰብን ዓላማው አድርጎ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

በዓመታዊ የጎዳና ሩጫው በሺዎች የሚቆጠሩ የዳያስፖራው ማኅበረሰብ አባላት እየተሳተፉበት የሚገኙ ሲሆን፣ የተሳታፊ ቁጥርም ከዓመት ዓመት እየጨመረ መምጣቱን አዘጋጁ አስታውቋል።

በሌላ በኩል በቀጣይ በሚከናወነው ውድድር ማግሥት ምሽት የሽልማት መርሐ ግብር የሚከናወን ሲሆን፣ በዚህም በሕይወት እያሉ ለማኅበረሰባቸው አስተዋጽኦ ያደረጉ ግለሰቦች ይዘከሩበታል፣ ይወደሱበታል፡፡ በዚህም መሠረት በዘንድሮው መርሐ ግብር በአትሌቲክሱ ስኬታማ ጊዜን ያሳለፉ የዲባባ ቤተሰቦችን ጨምሮ፣ በኢትዮጵያ የረዥም ርቀት ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስም ያለው ስለሺ ስህን ዓለም አቀፍ የክብር ዕውቅና ተበርክቶለታል፡፡

ከዚህም ባሻገር በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለረዥም ዓመታት ያገለገሉትና ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ግርማ ዋቄና፣ የኢትዮ ጃዝ ሙዚቃ ፈር ቀዳጁ አቶ ሙላቱ አስታጥቄ ተሸላሚ መሆናቸው ይታወሳል።

ባለፉት የውድድር ዓመታት፣ የኢትዮጵያ ብርቅዬ አትሌቶች ደራርቱ ቱሉ፣ ቀነኒሳ በቀለ፣ ገንዘቤ ዲባባ፣ ሚሊዮን ወልዴ፣ ፋጡማ ሮባ፣ ብርሃኔ አደሬ፣ ስለሺ ስህን፣ ቁጥሬ ዱለቻና ሌሎችም በክብር እንግድነት ተገኝተውበታል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...