Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊከአርዓዮች የሚቀዳ ጥበብ

ከአርዓዮች የሚቀዳ ጥበብ

ቀን:

ወጣቶቹ  በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሚዘጋጅ የኪነ ጥበብ መድረክና በሌሎች  ጥበብ ጥበብ በሚሸቱ ዝግጅቶች ላይ አይጠፉም። ምንም እንኳ ወጣቶቹ የየራሳቸው ችሎታና ዝንባሌ ቢኖራቸውም፣ ህልማቸው ጎምርቶና አፍርቶ ለቁም ነገር ለመብቃት ብዙ ውጣ ውረድ ገጥሟቸዋል።

በሙዚቃ፣ በሥነ ጽሑፍ፣ በሥዕልም ሆነ በማንኛውም የኪነ ጥበብ ዘርፍ ውጤታማ ሆኖ ለመገኘት ትዕግስትን፣ ጽናትንና ብርታትን መላበስ እንዲሁም ፈተናዎችን ሁሉ በአሸናፊነት ማለፍ ያስፈልጋል፡፡

ከአርዓዮች የሚቀዳ ጥበብ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
ሚኪያስ ደምስ

በኪነ ጥበብ ዘርፍ ውጤታማ በመሆን ነገ ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ብሎም አገራቸውን ለማስጠራት ከወዲሁ እየሠሩ እንደሆነ የነገሩን ወጣቶችም የአሸናፊነትን ሐሳብ ይገዙታል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ወጣት ሚኪያስ ደምስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሦስተኛ ዓመት የቴአትር ተማሪ ሲሆን፣ በሙዚቃው ዘርፍ የራሱን አሻራ ለማስቀመጥ እየሠራ መሆኑን ይናገራል።

በዘርፉ ጥሩ የሚባሉ ወጣት ድምፃውያን ተደብቀው ሥራቸውን ይሠሩና  ዘመኑ ባፈራቸው ማኅበራዊ ትስስር ገፆች፣ አልያም በቴሌቭዥን መስኮት በድንገት ብቅ በማለትና ችሎታቸውን በማሳየት ብዙዎችን እያስደሰቱና ለቀጣይ ሥራቸውም መደላድል እየፈጠሩ ይገኛሉ። ወጣት ሚኪያስም ከእነዚህ ወጣቶች መካከል አንዱ በመሆን ወቅቱን ጠብቆ ብቅ እንደሚል ገልጿል፡፡

ሕይወቱ ከሥነ ጽሑፍ ጋር በእጅጉ እንደተቆራኘች የሚናገረው ወጣት አልአዛር ጥበቡ ነው።

አልአዛር ግጥምና ልዩ ልዩ መጣጥፎችን መጻፍ የጀመረው ገና የአንደኛ ደረጃ ተማሪ በነበረበት ወቅት እንደነበር ያስታውሳል።

ለነበረው የኪነ ጥበብ ጅማሮው ዕድገት ደግሞ፣ የትምህርት ቤቱ የኪነ ጥበባት ክበብ የማይተካ ሚና እንደነበረው የሚናገረው አልአዛር፣ የወረዳ ኪነት ቡድኖች ጥበብን በዕውቀትና በጥረት ለተሻለ ደረጃ ለማድረስ የሚረዱ መንደርደሪያዎች ስለመሆናቸው ያክላል።

ወጣቱ የኪነ ጥበብ ጅማሮውን ዕውን ለማድረግ ዋነኛ መሰላል ነው ብሎ ወዳሰበበት ዩኒቨርሲቲ ለመግባት ጉጉቱ ከፍተኛ ነበር። በመሆኑም ከዛሬ ሦስት ዓመት በፊት የብዙ የኪነ ጥበብ አባቶች መፍለቂያ ወደ ሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተቀላቅሏል፡፡

ከአርዓዮች የሚቀዳ ጥበብ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
አልአዛር ጥበቡ

‹‹ሕይወት ሁሌም እኛ በፈለግናት መንገድ የማትሄድ ናት›› የሚለው አልአዛር፣ ማንም ሰው ባሰበው ዓላማና በጠበቀው መንገድ ላይራመድ እንደሚችልም ይናገራል፡፡

 በአርት ትምህርት ክፍል ገብቶና የኪነ ጥበብ ሙያውን ለማዳበር አልሞ ወደ ዩኒቨርሲቲ የገባው ወጣቱ፣ ከገባ በኋላ የገጠመው ሌላ እንደነበር ያስታውሳል።

ያሰበውና ያልጠበቀው ቀርቶ በማኅበረሰብ ጥናት (ሶሺዮሎጂ) ትምህርት ክፍል ገብቶ እንዲማር መደረጉን የሚናገረው አልአዛር፣ በዚህ ተስፋ ሳይቆርጥ ሌሎች ዕድሎችን ማማተር እንደጀመረ ተናግሯል።

‹‹ያሰቡት ነገር አልተሳካም ብሎ ለሚርቅ ሰው፣ ኪነ ጥበብ የበለጠ ትርቃለች›› ያለው ወጣቱ፣ የሶሺዮሎጂ ትምህርቱን እየተከታተለ ጎን በጎን ‹‹የንጋት ኮኮብ›› በተባለ የቴአትርና የሥነ ጹሑፍ ክበብ በመግባት ሙያውን ለማዳበር እንደቻለ ያስረዳል።

አልአዛር በአሁኑ ወቅት የዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን ቢያጠናቅቅም፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል በየሳምንቱ በሚያዘጋጀው የኪነ ጥበብ ምሽት መድረክና በሌሎች መድረኮች በመገኘት የግጥም ሥራዎቹን ለታዳሚዎች በማድረስ ላይ ይገኛል። በቀጣይም በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች በመጠቀም ሥራዎቹን ለሕዝብ እንደሚያደርስ ጠቁሟል።

‹‹ነገ በሕዝብ ፊት የሚያስመሠግን ሥራን ይዞ ለመገኘት ከወዲሁ ከታላላቆቼና አርአያ ይሆኑኛል ካልኳቸው ሰዎች እውቀትን እየቀሰምኩ ነው›› የሚለው ደግሞ ወጣት ሚኪያስ ነው።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሦስተኛ ዓመት የአርት ተማሪ እንደሆነ የገለጸው ሚኪያስ፣ የባህል ማዕከሉ ለሙያው ዕድገት ትልቅ አስተዋፅኦ እያደረገለት እንደሆነ ተናግሯል።

በማንኛውም የሙያ ዘርፍ ፍተናዎች ከፊት መቅደማቸው የማይቀር ነው የሚለው ወጣቱ፣ በኪነ ጥበብ ዘርፍ ያለው እንቅፋት ግን ከሁሉም የከፋና ውስብስብ ነው ይላል።

ይሁን እንጂ ነገ በሙዚቃው ኢንዱስትሪ ተሳታፊ ለመሆን የሚያስብ ሁሉ ነገሮች አልጋ በአልጋ ስለማይሆኑ፣ ከወዲሁ ለፈተና በመዘጋጀትና ተስፋ ባለመቁረጥ ፈተናዎችን በፅናት ማለፍ እንደሚጠበቅባቸው አስተያየቱን ሰጥቷል።

ሚኪያስ የባህል ማዕከሉ ለሙያው ዕድገት ትልቅ አስተዋፅኦ እያደረገለት እንደሆነም ተናግሯል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...