Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየተቀናጀው የባህል መድኃኒት ዕፀዋትን ማራባት

የተቀናጀው የባህል መድኃኒት ዕፀዋትን ማራባት

ቀን:

ከኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል 80 ከመቶ ያህሉ ከልዩ ልዩ ዕፀዋት የተቀመሙ ወይም የተዘጋጁ የባህል መድኃኒቶችን ተጠቃሚ መሆኑን በተለያዩ ጊዜያት የተከናወኑ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡

ዕፀዋቱ ኅብረተሰቡ ለሚጠቀምባቸው መድኃኒቶች እንደ ጥሬ ዕቃ ወይም ግብዓት ሆነው ካገለገሉ፣ ተገቢው ጥበቃና እንክብካቤ ሊደረግላቸውና የሚስፋፉበትም መንገድ ሊመቻችላቸው እንደሚገባ ብዙዎች ይስማሙበታል፡፡

የተቀናጀው የባህል መድኃኒት ዕፀዋትን ማራባት | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
ለባህል መድኃኒት ምንጭ ከሆኑት መካከል ዕፀዋት ይገኙበታል

በዚህም መሠረት በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የጉለሌ ዕፀዋት ማዕከል ከተለያዩ አካባቢዎች የተሰባሰቡ ዕፀዋትን ለማራባትና ለዚህም ተስማሚ ቦታዎችን ለማመቻቸት የሚያስችል እንቅስቃሴ በመከናወን ላይ ነው፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

እስካሁንም በተካሄደው እንቅስቃሴ የሚራቡ ዕፀዋትን መለየቱ ተከናውኗል፡፡ በዚህም ሥራ ሊጠፉ ለተቃረቡና አገር በቀል ለሆኑ ዕፀዋት ቅድሚያ ተሰጥቷል፡፡

አቶ ገዛኸኝ ኮኔ የኢትዮጵያ የባህል መድኃኒት ሕክምና አዋቂዎች ማኅበር ምክትል ፕሬዚዳንት ናቸው፡፡ እንደ ምክትል ፕሬዚዳንቱ አነጋገር፣ የማራባቱ ሥራ ሊካሄድ የተቻለው ማኅበሩ አዲስ አበባ ከሚገኘው የጉለሌ የዕፀዋት ማዕከል ጋር ከሁለት ወራት በፊት ባደረገው ስምምነት መሠረት ነው፡፡

ከዚህም ሌላ በሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች እንደዚሁ የዕፀዋት ማራቢያ ቦታ ለማግኘት ጉዳዩ የሚመለከታቸው መንግሥታዊ አካላት ተጠይቀው መፈቀዱንና ቦታዎቹም መለየታቸውን ገልጸው ነገር ግን በተፈጠረው የፀጥታ ቀውስ የተነሳ የልየታና የማራባቱ ሥራ አለመጀመሩን አስረድተዋል፡፡

በባህር ዳር ዙሪያም ተስማሚ ቦታ ለመጠየቅ ታስቦ አሁን ያለው የፀጥታ ሁኔታ አስቸጋሪ ሆኖ በመገኘቱ የታሰበው ተግባራዊ ሳይሆን መቅረቱንም ምክትል ፕሬዚዳንቱ አስታውሰዋል፡፡

ከዚህም ባለፈ ከባህል መድኃኒት አዋቂዎች መካከል አንዳንዶች የሚሰጡትን የባህል ሕክምናን አስመልክቶ በተለያዩ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች ከሚያወጡት ማስታወቂያዎች ጋር በማያያዝ ‹‹ሥልጣን እንሰጣችኋለን፣ ዓረብ አገር ለሥራ አለምንም ችግር እንድትሄዱ እናስደርግላችኋለን፣ አሠሪዎቻችሁ እንዳይቆጧችሁ ፀጥ እናስደርግላችኋለን›› የሚሉና ከባህል ያፈነገጡና አስነዋሪ ጽሑፎችን ለጥፈው ማየት የተለመደ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡

ማኅበሩ ጉዳዩ በይበልጥ ከሚመለከታቸው መንግሥታዊ አካል ጋር በመተባበር ይህንኑ ተግባር ለማስቀረት የሚያስችል ፕሮግራም ማውጣቱንም ለተግባራዊነቱም አስፈላጊው ዝግጅት በማከናወን ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ የባህል መድኃኒት ሕክምና አዋቂዎች ማኅበር፣ በአሁኑ ጊዜ እየተገለገለ ያለው በኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ቅጥር ግቢ በሚገኘው ቢሮው ውስጥ ሲሆን፣ ቢሮውንም በነፃ የለገሰው ኢንስቲትዩቱ መሆኑን ገልጸው፣ ወደፊትም አለርት ግቢ ውስጥ የሚገኘው አርማወር ሀንሰን ምርምር ኢንስቲትዩት (ኢህሪ) ባሠራው ሕንፃ ላይ ለቢሮ የሚውል ክፍል ሊሰጠው ቃል የተገባለት መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ማኅበሩ በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ውስጥ ጠቅላላ ጉባዔ ለመጥራት መወሰኑን፣ ለዚህም የሚያስፈልገውን ፋይናንስ ከኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩትና ከጤና ሚኒስቴር ለማግኘት ማቀዱንና ዕቅዱም ሙሉ ለሙሉ ተፈጻሚ ይሆናል የሚል እምነት ማሳደሩን ነው ያመለከቱት፡፡

በኢትዮጵያ ከአሥር ሺሕ በላይ የሚሆኑ የባህል ሕክምና አዋቂዎች እንዳሉ መገመቱንና ከእነዚህም መካከል ከአንድ ሺሕ በላይ በአባልነት መመዝገባቸውን፣ ትክክለኛ ክትትልና ተገቢ የሆነ ቆጠራ ቢካሄድ የአዋቂዎቹ ቁጥር ከፍ ብሎ ከተጠቀሰው መጠን የሚበልጥ መሆኑን ከአቶ ገዛኸኝ ማብራሪያ ለመረዳት ተችሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...