Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅየአብዮቱ ክስተቶች

የአብዮቱ ክስተቶች

ቀን:

በ1965 ዓ.ም. ሁለተኛ ሴሚስተር በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ማኅበር አነሳሽነት በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም አስተባባሪነት፣ በፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ እርዳታና ድጋፍ በዶክተር አብርሃም ደመወዝ፣ በዶከተር አሉላ አባተና ሌሎች ቀጥተኛ ተሳታፊነት፣ በወሎ ሕዝብ ለደረሰው ጉዳት ተጨባጭ መረጃ በፎቶግራፍ ቀርጸው ለዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ፣ ለተማሪዎች ጭምር፣ ይፋ ተደረገ። ተማሪዎች ለተቸገረው ወግነው ቁርሳቸውን አበረከቱ፤ መምህራን ገንዘብ አዋጡ፤ መንግሥት በይፋ ታማ፣ ተደፈረ ። የመንግሥት ግድየለሸነት የቀን ተቀን የመወያያ ርዕስ ሆኖ ነበር። 

ለዚህ ሒደት አንድ ምሳሌ አለ። በአፄ ቴዎደሮስ ዘመን የተከሰተ- የመደፈር ምልክት፣ ወዳጄ ፕሮፊሰር ነቢያት ተፈሪ (በሕክምና ፋካልቲ የሕፃናት ክፍል መምህር፣ እና ከእኔ ጋር አንድ ሕንፃ/ፎቅ ውስጥ አብረን ለዓመታት የኖሮን) ያወጋልኝ አለ። በአፄ ቴዎድሮስ ዘመነ መንግሥት ይኖር የነበረ ገበሬ አንድ አስቸጋሪ በሬ ነበረው፤ የሌሎች ገበሬዎችን ማሳ፣ አዝመራ እየዞረ የሚቃርም። በዚህ ምክንያት የበሬውም ባለቤት አዝመራቸው የተበላባቸው ሌሎች ገበሬዎች አፈላማ (ካሳ) መክፈል ስለ ሰለቸው እንዳይሸጠው አመለኛ በሬ የሚገዛ ሞኝ ገበሬ በአካባቢው በቀላሉ አይገኝም፣ አርዶ እንዳይበላው በሬው አሳዘነው፤ ያን ማድረግ ኪሳራም ነበር። 

ከችግሩ ለመላቀቅና እንደውለታም እንዲቆጠርለት ብሎ፣ በሬውን ለአፄ ቴዎድሮስ ሰጣቸው፡፡ ይህ አስቸጋሪ በሬ፣ የንጉሡ በሬ፣ እንደለመደው እየዞረ ከበሬው ማሳ አዝመራ መብላት ቀጠለ፣ ንጉሡን አፈላማ ማስከፈል አይቻልም፤ መጠየቁም ነውር ይሆናል። በተጨማሪ የንጉሡን በሬ ከማሳ ማባረርም፣ አዝመራ እንዳይበላ መከልከልም፣ የማይፈለግ አፃፋ ሊያሰከትል ይችላል፤ ያውም በርህሩህነቱ የማይታማውን የመሬሳው ካሳ ኃይሉን (የአፄ ቴዎድሮስን) በሬ። 

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

አፄ ቴዎድሮስን ሰው በጣም እየጠላቸው ሲሄድ፣ ጉልበታቸውም በዚያ መጠን እየኮሰሰ ሄደ፤ ይህን ግንዛቤ አንግቶ፣ ዙሪያውን ቃኝቶ አንድ ደፋር ገበሬ፣ የንጉሡን በሬ አርዶ ለሕዝብ አቀራመተ። በዚህ ጊዜ ገበሬ ከአንድ አምባ ወደ ሌላ አምባ እየተጣራ፣ ወሬውን በአንድ አፍታ አስተጋባ ይባላል፣ ‹‹የንጉሡ በሬ ታርዶ ተበላ አሉ!›› የሚለውን። ይህም ንጉሡ መናከሻ ጥርስ እንደሌለው፣ እንዲሁ እንደሚጮህ ውሻ መገመታቸውን ገበሬ በሙሉ ተረዳ፤ በአፄ ቴዎድሮስ ተደፈሩ አለቀላቸው። 

በተመሳላይ ሁኔታ በወሎ ረሃብ ምክንያት፣ በ1966 ዓ.ም. ሕዝብ በይፋ መንግሥትን መዝለፍ፣ ባለሥልጣኖችን ማዋረድ ጀመረ። የየካቲት 1966 ዓ.ም. ሕዝባዊ አመፅ በይፋ ታየ፤ ከወራት በኋላ መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም. ንጉሠ ነገሥቱ ከሥልጣን ወረዱ፤ አገር በለውጥ ማዕበል መናወጡ ቀጠለ። የኢትዮጵያ መንግሥት የወደፊት አቅጣጫ ምን ይመስል ይሆን የሚለው በሁሉም ጭንቅላት ይብላላ ጀመር። ያም ሆኖ፣ ያ ወቅት ሁሉም በየአቅጣጫው ለወደፊት የኢትዮጵያ ደኅንነት፣ እድገት ድርሻውን ለማበርከት የተነሳሳበት ጊዜ ነበር። 

  • ሽብሩ ተድላ ‹‹ከጉሬዛም ማርያም እስከ አዲስ አበባ››
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...