Sunday, March 3, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅደስተኛ ሕዝብ ሊኖር የሚችለው…

ደስተኛ ሕዝብ ሊኖር የሚችለው…

ቀን:

ያለፉት አምስት መቶ ዓመታት፣ አስገራሚ የሚባሉ ተከታታይ አብዮቶችን አስተናግደዋል፡፡ ምድራችን ወደ አንድ ሥነ ምህዳራዊና ታሪካዊ መንደር ተቀይራለች፤ ኢኮኖሚው በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ነው፤ ዛሬ ላይ ዘረ ሰብ የጥንት ሰዎች በተረቶቻቸው ይመኙት የነበረው ዓይነት ሀብትና ችሎታ አግኝቷል፡፡ ሳይንስና የኢንዱስትሪው አብዮት ለሰብዓዊ ፍጡራን ልዕለ ኃያልነትና ገደብ የለሽ ኃይል ሰጥተዋል፤ በዚህም የተነሳ ማኅበራዊ ሥርዓት፣ ፖለቲካ የሰዎች ሥነ ልቦና እና የዕለት ተለት ኑሮ ፍጹም ሽግግሮሽን አድርገዋል።

ነገር ግን ደስተኞች ነን? ላለፉት አምስት መቶ ዓመታት የሰው ልጅ ያከማቸው ሀብት ውስጣችንን አርክቶ እፎየው አስብሎናል? የማይነጥፍ የኃይል ምንጭ መገኘቱ የማይነጥፍ ሀብት፣ ተድላና ፈንጠዝያ ከፊታችን አስቀምጦልናል? ወደ ኋላ ነጉደን፣ ከእውቀት ክምችት አብዮት ጀምሮ ለ70 ሺሕ ዓመታት ያሳለፍነው ያልተረጋጋ ዘመን፣ ዓለማችን ለሕይወት የተሻለች ስፍራ እንድትሆን አስችሏል? ንፋስ በማይነፍስበት የጨረታ ገጽ ላይ የጫማውን ምልክት አኑሮ የመጣው ጠፈረተኛው አርምስትሮንግ፣ ከዛሬ 30 ሺሕ ዓመታት በፊት በሾቬ ዋሻ ግድግዳ ላይ የእጁን መዳፍ ካተመው ስም የለሽ አዳኝና ቃራሚ ሰው የበለጠ ደስተኛ ነው? ካልሆነ የግብርናው፣ የከተማው፣ የሥነ ጽሑፉ፣ የሳንቲሙ፣ የኢምፓየሮች፣ የሳይንስና የኢንዱስትሪው ዕድገት ነጥቡና ፋይዳው ምንድነው? 

የታሪክ ምሁራን እንዲህ ያሉትን ጥያቄዎች የሚያነሱት ከስንት አንዴ ነው?  እነኝህ ልሂቃን የኡሩክና የባቢሎን ዜጎች ቀድመዋቸው ከነበሩት የአዳኝና ቃራሚ ማኀበረሰቦች የበለጠ ደስተኞች ነበሩ ወይ፣ የእስልምና መነሳት ግብፃውያንን በሕይወታቸው የበለጠ ደስተኛ አድርጓቸዋል ወይ፣ ወይም ደግሞ በአፍሪካ የአውሮፓ ኢምፓየር መፈራረስ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩት አፍሪቃውያን ደስታ ላይ ያመጣው ለውጥ አለ ወይ ብለው አይጠይቁም፡፡ ነገር ግን ጥያቄዎቹ አንድ ሰው ከታሪክ ሊጠይቃቸው የሚገቡ አስፈላጊና ወሳኝ ነጥቦች ናቸው፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

 አብዛኞቹ ርዕዮተ ዓለሞችና የፖለቲካ ፕሮግራሞች፣ የሰው ልጅ እውነተኛ የደስታ ምንጭ ናቸው ብለው የሚያነሷቸው ሐሳቦች መሠረታቸው በእጅጉ ደካማ ነው፡፡ ብሔራዊ ፓርቲዎች ሰዎች ደስተኛ የሚሆኑት ራሳቸውን በራሳቸው ሲያስተዳድሩ ነው ብለው ያምናሉ፤ ኮሚኒስቶች ደግሞ ሰዎች በጸጋ የተሞላ ደስተኛ ሕይወት ሊኖሩ የሚችሉት በወዛደሩ አምባገነናዊ አመራር ሥር ነው ብለው ይበይናሉ፡፡ ካፒታሊስቶችም በተራቸው – ደስተኛ ሕዝብ ሊኖር የሚችለው ነፃ ገበያን ተቀብለን እያደገ በሚሄድ ኢኮኖሚያዊ አቅርቦትን በመጨመር ሰዎች ንቁ ተሳታፊ ሆነው እንዲነግዱና ራሳቸውን እንዲችሉ በማስተማር ብቻ እንደሆነ ከልባቸው ይከራከራሉ።

  • አብዲሳ ቶላ (ተርጓሚ) ‹‹ሳፒያንስ -የጠቢቡ ሰው አጭር ታሪክ››
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...