Monday, February 26, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በብሔራዊ ባንክ መሪነት በተካሄደው ጉባዔ የተመረጡት አዲስ የንብ ባንክ የቦርድ አባላት ሹመት ፀደቀ

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቅርቡ የተመረጡትን የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ሹመት አፀደቀ፣ ይህንንም ተከትሎ አዲሶቹ ተመራጮች በሚቀጥለው ሳምንት ከተሰናባቹ ቦርድ ኃላፊነት እንደሚረከቡ ታውቋል፡፡ 

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በቅርቡ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ የተመረጡት 12 የባንኩ ቦርድ ዳይሬክተሮች ሹመትን ብሔራዊ ባንክ በማፅደቅ ባለፈው ዓርብ ጥር 17 ቀን 2016 ዓ.ም. ለባንኩ ማሳወቁን የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡ 

ንብ ባንክን በቦርድ ዳይሬክተርነት ለማገልገል ከፍተኛ ድምፅ ያገኙትና ሹመታቸው በብሔራዊ ባንክ ተቀባይነት አግኝቶ የፀደቀላቸው አሥራ ሁለቱ ተመራጮች፣ መሐሪ መኮንን (ዶ/ር)፣ ወንድሙ ተክሌ (ዶ/ር)፣ አቶ ፀጋዬ ደገፋ፣ አቶ አበራ ሽር፣ አቶ ሳላዲን ኢብራሒም፣ አቶ ሠይፈ አዋሽ፣ ወ/ሮ ገነት ወልዴ፣ አቶ በንቴ ሲራኒ፣ አቶ ዘውዴ ሲርባሮ፣ አቶ ተስፋዬ  ይርጋ፣ አቶ ማሙሸት አፈወርቅና አቶ ሺሰማ ሽዋንቃ እንደሆኑ ሪፖርተር ከምንጮቹ ያገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡ 

ታኅሳስ 18 ቀን 2016 ዓ.ም. በተካሄደው የንብ  ኢንተርናሽናል ጠቅላላ ጉባዔና ምርጫ ከቀድሞ የቦርዱ አባላት ውስጥ አምስት የሚሆኑት ተወዳዳሪ ሆነው የቀርቡ ቢሆንም የባንኩ ቦርድ አባል ለመሆን የሚያስችል በቂ ድምጽ ከባንኩ ጠቅላላ ጉባዔ ማግነት አልቻሉም። 

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ውስጥ አጋጠመ የተባለውን ችግር በመመርመር በታኅሳስ ወር ውስጥ ለተካሄደው የባንኩ ጠቅላላ ጉባዔ ሪፖርት ያቀረበው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ነባሩ የዳይሬክተሮች ቦርድም ሆነ ማኔጅመንቱ ንብ ባንክ ያጋጠመውን ችግር ይፈታል የሚል እምነት እንደሌለው አስታውቆ ነበር።

አዲስ የተመረጠው የዳይሬክተሮች ቦርድ ስብስብም ኃላፊነቱን ከተረከበ በኋላና  ባንኩን ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላት በአዲስ ይተካል ተብሎ  የሚጠበቅ እንደሆነም እየተነገረ ነው፡፡  ብሔራዊ ባንክ ቀደም ብሎ ካደረገው ምርመራ በተጨማሪ በእያንዳንዱ ጉዳዮች ላይ መረጃ በመውሰድ ሲያደርግ የነበረውን ምርመራ ውጤት  ይፋ ያደርጋል ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

ይህ የምርመራ ውጤት ተጨማሪ ዕርምጃዎችን  እንዲወስድ ያስገድደዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሪፖርተር ከምንጮቹ ያገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡ 

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በ2015 የሒሳብ ዓመት ካስመዘገበው ትርፍ ውስጥ ለባለአክሲዮኖች ተመድቦ የነበረው የትርፍ ድርሻ ሳይከፈል የባንኩን ካፒታል ለማሳደግ እንዲውል ተወስኗል። 

ንብ ባንክ ባለፈው ወር ያካሄደው የዳይሬክተሮች ቦርድ የምርጫ ሂደት ከተለመደው አሰራር ወጪ በብሔራዊ ባንክ ሰብሳቢነት መከናወኑ ይታወሳል።

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች