Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናገዥው ፓርቲ ተጨማሪ የባሕር በር አማራጮችን በሰጥቶ መቀበል መርሕ ለማግኘት እንደሚሠራ አስታወቀ

ገዥው ፓርቲ ተጨማሪ የባሕር በር አማራጮችን በሰጥቶ መቀበል መርሕ ለማግኘት እንደሚሠራ አስታወቀ

ቀን:

  • ፓርቲው አቶ ደመቀ መኮንን ከብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳትነት በክብር ሸኝቷል

ገዥው ብልፅግና ፓርቲ ከሰሞኑ ከሶማሌላንድ ጋር የባህር በር ለማግኘት ከፈጸመው ስምምነት በተጨማሪ የባህር በር አማራጮችን በሰጥቶ መቀበል መርሕ ለማግኘት ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሠራ አስታወቀ፡፡

መደበኛ ስብሰባውን ከጥር 13 እስከ 17 ቀን 2016 በአዲስ አበባ ከተማ ሲያካሂድ የሰነበተው የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ ከጎረቤቶች አገሮች፣ ከአፍሪካ ቀንድና ከዓለም ጋር ያለውን የወገን ዘለል ትስስር ሁኔታ መገምገሙን አስታውቋል፡፡

የፓርቲው መግለጫ እንደሚያሳየው ኢትዮጵያ እያደገ ከሚሄደው የሕዝብ ብዛቷና ኢኮኖሚዋ ጋር የሚመጣጠን የባህር በር እንደሚያስፈልጋትና ከሶማሌላንድ ጋር የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት፣ ኢትዮጵያ ለቀጣናዊ የኢኮኖሚና የባህል ትስስር ያላትን አቋም የሚያሳይ መሆኑን መረዳቱን አስታውቋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በቀጣይም የተጀመረውን የመግባቢያ ስምምነት ወደ ተግባራዊ ስምምነት ለማድረስ፣ ከሌሎች ጎረቤት አገሮችም ጋር ተጨማሪ የባህር በር አማራጮችን በሰጥቶ መቀበል መርሕ ለማግኘት ትኩረት ተሰጥቶት እንዲሠራ ውሳኔ ተላልፏል፡፡

 በሰሜኑ ጦርነት ጊዜ ተቀዛቅዞ ነበር ያለውን ከምዕራቡ ዓለም ጋር ያለው ግንኙነት ወደ ቀድሞ ቦታው እየተመለሰ መሆኑንና፤ ከምሥራቁ ዓለም ጋር ያለው ግንኙነትም እየተጠናከረ መምጣቱን መረዳቱን ፓርቲው ገልጿል፡፡

የ2016 የበጀት ዓመት የኢኮኖሚ ዕድገት 7.9 በመቶ እንደሚሆን መተንበይና ይሄንንም ለማሳካት ከአመራሩ፣ ከአባላቱና ከሕዝቡ ጋር በመሆን በቀሪ ጊዜያት ጠንክረው መሥራት አለባቸው የሚል ውሳኔ መተላለፉን መግለጫው አመላክቷል፡፡

ሜጋ ፕሮጀክቶች ያሉባቸውን ማነቆዎች በመፍታት በቀሪዎቹ ጊዜያትም የተጠናቀቁት እንዲመረቁ፣ ያልተፈቱ ችግሮች ያሉባቸውም ችግሮቻቸው ተፈትተው እንዲጠናቀቁ አቅጣጫ መቀመጡንና የሕዳሴ ግድቡንም በ2017 የበጀት ዓመት ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኢኮኖሚ ዕድገቱ ከዚህ በላይ ለመሄድ እንዳይችል አንዱ ዕንቅፋት በጠባብ ቡድናዊ ፍላጎት የተፈጠሩ ትሥሥሮች ያስከተሏቸው አካባቢያዊ ግጭቶች መሆናቸውን የሚገልጸው ፓርቲው፣ ከታጣቂ ቡድኖች ጋር የተጀመሩ ሰላማዊ አማራጮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አቅጣጫ መቀመጡ ተመላክቷል፡፡

በሰላማዊ የፖለቲካ መንገድ ጥያቄዎቻቸውን ለሚያቀርቡ አካላት ሰላማዊ መንገዶች እስከሚቻለው ድረስ እንዲመቻቹ፣ ዓላማቸው በነፍጥ ፍላጎታቸውን ማስፈጸም በሆኑ አካላት ላይ ደግሞ፣ ተገቢው ሕግን የማስከበር ሥራ በተጠናከረ መንገድ እንዲካሄድ ውሳኔ መተላለፉም ፓርቲው በመግለጫው አስታውቋል፡፡

ፓርቲው በጉባዔው ማጠናቀቂያ የብልፅግና ማዕከላዊ ኮሚቴ የፓርቲውን የአመራር፣ የመተካካት መርህንና የአሠራር ሥርዓት በመከተል አቶ ደመቀ መኮንን በሙሉ ድምፅ  በክብር መሸኘቱን አስታውቋል።

በምትካቸውም የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ የነበሩትን አቶ ተመስገን ጥሩነህን ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ በአብላጫ ድምጽ መርጧል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...