Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜና‹‹እንደ አፍሪካ ዋንጫ በቀጥታ በተላለፈው የግብፅ መግለጫ የሚረበሽ የለም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

‹‹እንደ አፍሪካ ዋንጫ በቀጥታ በተላለፈው የግብፅ መግለጫ የሚረበሽ የለም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ቀን:

‹‹እንደ አፍሪካ ዋንጫ በቀጥታ በተላለፈው የግብፅ ፕሬዚዳንት መግለጫ የሚረበሽ የለም›› ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በሶማሌላንድ የባህር በር ለማግኘት ኢትዮጵያና ሶማሌላንድ የመግባቢያ ስምምነት ከተፈራረሙ በኋላ የግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ባለፈው ሳምንት በሰጡት መግለጫ፣ በሶማሊያ ላይ ሊኖር የሚችል ማንኛውም የደኅንነት ሥጋት አገራቸው እንደማትፈቅድና ለሶማሊያ ድጋፏን እንደምትሰጥ ማስታወቃቸው አይዘነጋም፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ መለስ ዓለም (አምባሳደር) ጥር 16 ቀን 2016 ዓ.ም. በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ፣ ‹‹የመግለጫ ጋጋታ በኢትዮጵያ ላይ የሚፈጥረው ነገር የለም፡፡ ይህ አገር ትልቅ አገር ነው፣ በስኒ ውስጥ ባለ ማዕበል ዝም ብሎ የሚናጥ አይደለም፤›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ቃል አቀባዩ አክለውም ከካይሮ ምንም የተለየ አዲስ ነገር አለመኖሩንና ከዚህ በፊትም ከህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ በርካታ መግለጫዎች ይወጡ እንደነበር፣ የተለመደው መግለጫ ቀጥሎ አሁን ያለበት ደረጃ መድረሱን ‹‹የግብፅ መግለጫ ዜና አይደለም፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በኢትዮጵያ መረጋጋት እንዳይኖር ይሠራሉ፤›› ብለዋል።

‹‹መግለጫው እንደ ሰሞኑ የአፍሪካ ዋንጫ በቀጥታ የቴሌቪዥን ሥርጭት የተላለፈ ነው፣ ስለዚህ መደምደሚያ ላይ ለመድረስ ብዙም የሚቸግር አይደለም። አሁን ያለን ሕዝብ በመግለጫ የሚሸበርና የሚረበሽ አገር አይደለም፡፡ ነፃነታችን በዋጋ የመጣ ነው፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

‹‹ባለፉት ሦስት ዓመታት ያለፍንበትን ሁኔታ ሌሎች አገሮች ያልፉበታል ብላችሁ እንዳትገምቱ›› ብለው፣ ባለፉት ሺሕ ዓመታት አገሪቱ ያለፈችበት ብዙ አገሮች የሚያልፉበት እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ የዓረብ ሊግ መግለጫም ብዙም የሚያመጣው ለውጥ የለም ያሉት ቃል አቀባዩ፣ ‹‹ኢትዮጵያ ሁልጊዜም ለንግግር ክፍት ነች፡፡ ነገር ግን የውጭ ጣልቃ ገብነት ግጭቱን፣ ቁርሾውን፣ ጥላቻውንና ቀውሱን ማርገብ ሳይሆን ማራገብ ስለሚሆን በእኛ በኩል ቀውሱን የማርገብ ሥራ እንሠራለን፡፡ የሚጠቅመውም ይኼ ነው፤›› ብለዋል፡፡

ከኢትዮጵያ በላይ ለሶማሊያ አስባለሁ ብሎ የሚጮህ ከንቱ ማፏጨት ነው ያሉት መለስ (አምባሳደር)፣ ‹‹ተቋማት እንዲቋቋሙ ዋጋ የሚከፍሉና እየከፈሉ ያሉ ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ ኢትዮጵያና ሶማሊያ አንድ ሕዝብ ናቸው፣ ወዳጅ አይደሉም ቤተሰብ ናቸው፤›› ሲሉ አክለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...