Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየመዝናኛ ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ አስፋው መሸሻ (1959-2016)

የመዝናኛ ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ አስፋው መሸሻ (1959-2016)

ቀን:

ከሩብ ምዕት ዓመት በፊት የኢትዮጵያ ሬዲዮ ከብሔራዊው ማሠራጫ ባሻገር የኤፍኤም መደበኛ ሥርጭቱን ኤፍኤም አዲስ 97.1 ሲጀምር፣ ከተባባሪ አዘጋጆች አንዱ የነበረው የመዝናኛ መርሐ ግብር፣ በልዩ መጠርያው ‹‹አይሬ›› የተሰኘው ነበር፡፡ እንደ መጠርያው ብዙዎችን እያዝናና የሚያስደስት እንደነበር ይነገርለታል፡፡ በርካታ አድማጮች በነበረውና በየዕለቱ ከሰንበቶች ውጪ አይሬ በተሰኘ የሙዚቃ ፕሮግራም ከባልንጀራው ዳንኤል ግዛው ጋር ያቀርብ የነበረው አስፋው መሸሻ ነበር፡፡

የመዝናኛ ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ አስፋው መሸሻ (1959-2016) | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
ነፍስ ኄር አስፋው መሸሻ

ለስድስት ዓመታት በዘለቀው ሙዚቃዊው መሰናዶን አስፋው ሲያጋፍር፣ አቀራረቡ አድማጭን ዘና በሚያደርግና በማያሰለች መልኩ እንደነበር፣ የቋንቋ አጠቃቀሙም ለዛና ላህይ እንደነበራቸው የሚመሰክሩለት ቁጥራቸው ቀላል አይደለም፡፡ ከሬዲዮ የሙዚቃ ፕሮግራሙ በተጓዳኝም ማስታወቂያዎችንም ይከውን ነበር።

ኑሮውን በአሜሪካ ካደረገ በኋላ በኢትዮጵያ ሦስተኛ ሚሌኒየም መባቻ (በ2001 ዓ.ም.) የአዲሱ የቴሌቪዥን ጣቢያ – ኢቢኤስ – ባልደረባ በመሆን ታዋቂነትን ያተረፈለት ‹‹ኑሮ በአሜሪካ›› የተሰኘ ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ ነበር፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በገጸ ታሪኩ እንደተገለጸው፣ ኑሮ በአሜሪካ በተሰኘው መሰናዶው በአትላንታ፣ ኮሎራዶ፣ ሲያትል፣ ዴንቨር፣ ቨርጂኒያ፣ ዲሲ፣ ሜሪላንድና በሌሎችም ግዛቶች በመዘዋወር የኢትዮጵያውያንና የትውልደ ኢትዮጵያ አኗኗርን አሳይቷል፡፡

አስፋው ጓዙን ጠቅሎ ኑሮውን በአዲስ አበባ ካደረገ በኋላ ‹‹እሑድን በኢቢኤስ›› በተሰኘ ፕሮግራም ላይ አቅራቢ በመሆን ሲሠራ ተመልካቾችን የሚያዝናኑና ቁምነገር አዘል መልዕክቶችን በማስተላለፍ ታዋቂነትን ማትረፉም ይነገርለታል።

ከእናቱ ከወ/ሮ ዘነበ ወርቅ አሻግሬና ከአባቱ ከአቶ መሸሻ አስፋው (አምባሳደር) ረቡዕ ሐምሌ 19 ቀን 1959 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ የተወለደው አስፋው መሸሻ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በቤተልሔም ትምህርት ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃና የዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን በታንዛኒያና ኬንያ በመከታተል በኮምፒዩተር ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪውን ተቀብሏል።

አስፋው ባደረበት ሕመም ምክንያት ሕክምናውን በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ እየተከታተለ ሳለ ቅዳሜ ጥር 4 ቀን 2016 ዓ.ም. ያረፈው አስፋው፣ ሥርዓተ ቀብሩ በአዲስ አበባ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሰኞ ጥር 13 ቀን ተፈጽሟል፡፡ ሥርዓተ ቀብሩ ከመፈጸሙ በፊት- በዋሽንግተን የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ ረቡዕ ጥር 8 ቀን እንደተደረገለት የስንብት ሥነ ሥርዓት- በሚሌኒየም አዳራሽም በልዩ ሥነ ሥርዓት ስንብት ተደርጎለታል፡፡

በሚዲያው የመዝናኛ ዘርፍ ለሩብ ክፍለ ዘመን የሠራው ነፍስ ኄር አስፋው መሸሻ የአንድ ልጅ አባት ነበር፡፡

‹‹አስፋው ሕይወትን ቀለል አድርጎ  ይመለከት የነበረ ፈታ ያለ ሰው ነው፡፡ መሳቅ፣ መጫወት፣ ታሪክ ማውራት  የሚወድ፣  ከትልቅም ከትንሽም ሰው ጋር የጓደኛ ያህል የሚቀርብ፣ ከተማረውም ካልተማረውም ከሁሉም ጋር በየደረጃው የሚግባባ፣ ሰውን የሚያከብር ሰው ነበር፤›› በማለት ለተወዳጅ ሚዲያ አስተያየቱን የሰጠው አብሮት የሠራው ዲጄ ፋትሱ ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...