Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበአዲስ አበባ የተጀመረው የሕመም ስቃይ ማስታገሻ አገልግሎት

በአዲስ አበባ የተጀመረው የሕመም ስቃይ ማስታገሻ አገልግሎት

ቀን:

የመድኃኒትና የድጋፍ እንክብካቤ በጣም ይለያያል፡፡ ይህም ሆኖ ግን ሊሰጣቸው የሚችል የተለያዩ የሕክምና ዓይነቶች አሉ፡፡ እነዚህ ዓይነቶችም የሕመም ምልክቶችንና የጎንዮሽ ጉዳቶችን ለማስታገስ የሚያስችሉ መሆናቸውን የሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

ከመረጃው ለመረዳት እንደተቻለው የሕመም ምልክቶችንና የጎንዮሽ ጉዳቶችን በመድኃኒት፣ በጨረር ሕክምና ወይም ቀዶ ሕክምና ባሉ የሕክምና መንገዶች ማስታገስ ይቻላል፡፡

ከዚህም ሌላ የአመጋገብ ለውጥ፣ ምክርና መዝናናትን
ጨምሮ መንፈሳዊ ድጋፍ ለተንከባካቢዎች ወይም ለልጆች የሚሆን ድጋፍ ያካተተ ሕክምናና ተሃድሶ መስጠት ሌላው ማስታገሻ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በዚህም መሠረት በአዲስ አበባ በጤና ተቋማት የመጀመሪያው አሃድ ደረጃ የሕመም ስቃይ ማስታገሻ ሕክምና አገልግሎት መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡ ታካሚዎች በአቅራቢያቸው በሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ የመጀመሪያ አሃድ ደረጃ የሕመም ማስታገሻ ሕክምና ማግኘት ይችላሉ ብሏል፡፡

ታካሚዎች ከሚደረግላቸው ከመደበኛ ሕክምና አገልግሎት በተጨማሪ ሕመሙ የሚያደርሰውን ጫና ለመቀነስ ሥነ ልቦናዊ፣ አካላዊ፣ መንፈሳዊ ጥንካሬና አዕምሯዊ ብርታት እንዲያገኙ የባለሙያ ምክር፣ ድጋፍና ክብክቤ የሚያገኙበትም አሠራር ተዘርግቷል፡፡

የጤና ቢሮው ይህንን አገልግሎት ለሕሙማን ተደራሽ ለማድረግ፣ ሕክምናውን በ34 ጤና ጣቢያዎች ላይ ተግባራዊ ለማድረግ እየሠራ ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንት መገባደጃ በሚኪሊላንድ፣ በልደታ፣ በቸርችልና በኮልፌ ጤና ጣቢያዎችም አገልግሎቱ በይፋ በማስጀመር በቀጣይ ቀናት በሌሎቹ ላይም አገልግሎቱ እንደሚጀምር ተጠቁሟል፡፡

በማስጀመሪያ መርሐ ገብሩ ላይ የተገኙ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሙሉጌታ እንዳለ (ዶ/ር)፣ መከላከልን መሠረት ባደረገው የጤና ፖሊሲ በርካታ በሽታዎችን በቀላሉ መከላከል የሚችል መሆኑን ገልጸው፣ ከመከላከሉም ሥራ አንደኛው የታካሚውን ሕመም ማስታገሰስ የሚያስችል ፕሮግራም መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የሕመም ማስታገሻ ሕክምና በየትኛውም የዕድሜ ክልል ከሕፃን እስከ አዋቂ ያሉ ታካሚዎች በአቅራቢያቸው በሚገኝ የጤና ተቋም ተደራሽ በማድረግ፣ ከማከምና መድኃኒት ከመስጠት ባለፈ ሥነ ልቦናዊ ድጋፍ መስጠት የሚያስችል በመሆኑ፣ አገልግሎቱ በጤና ተቋማት ተደራሽ ለማድረግ በስፋት እየተሠራ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡

የቢሮው የሜዲካል ሰርቪስ ዳይሬክተር አቶ መልካሙ ጥሩነህ በበኩላቸው፣ የመጀመሪያ አሃድ ደረጃ የሕመም ማስታገሻ ሕክምና፣ በአገር ደረጃም ሆነ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጤና ጣቢያ ደረጃ ሲሰጥ የመጀመርያ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ተግባሩን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ክትትልና ድጋፍ፣ እንዲሁም የአቅም ግንባታ ሥራዎችን አጠናክሮ በመሥራት የጤና ጣቢያዎች ከሆስፒታሎች ጋር በቅንጅት እንዲሠሩ ለማስቻል እንደሚሠራ አመልክተዋል፡፡

ሕክምናው የጤና ተቋማት ለኅብረተሰቡ የሚሰጡትን አገልግሎት ይበልጥ የሚያሳድግ መሆኑንና ይህም መልካም ተሞክሮ ወደ ሌሎች የጤና ተቋማት በማስፋትና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራ አቶ መልካሙ ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...