Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ደረጃን ማሟላት የሚጠበቅበት ዓመታዊው የአትሌቲክስ ሻምፒዮና

ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ደረጃን ማሟላት የሚጠበቅበት ዓመታዊው የአትሌቲክስ ሻምፒዮና

ቀን:

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከሚዘጋጁት ዓመታዊ ውድድሮች  የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮን አንዱ ነው፡፡ በውድድሩ በርካታ ዓለም አቀፍ ልምድ ያላቸውና አዳዲስ አትሌቶች ይሳተፉበታል፡፡ ዘንድሮ ለ53ኛ ጊዜ በሚከናወነው በዚህ ሻምፒዮን ከ1,000 በላይ አትሌቶች እንደሚካፈሉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡ 

ሻምፒዮናው ከጥር 21 እስከ 26 ቀን 2016 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ስፖርት አካዴሚ እንደሚከናወን ተገልጿል፡፡ በሻምፒዮናው ክልሎች፣ የከተማ አስተዳደሮች፣ ክለቦች፣ እንዲሁም ተቋማት በተለያዩ የውድድር ዓይነቶች አትሌቶቻቸውን ይዘው ይቀርባሉ፡፡ 

ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ደረጃን ማሟላት የሚጠበቅበት ዓመታዊው የአትሌቲክስ ሻምፒዮና | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
ዓመታዊ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና

በሻምፒዮናው ከ100 ሜትር ርቀት ጀምሮ በ200፣ በ400፣ በ800፣ በ1500 ሜትር፣ በ3000 መሰናክል፣ በ5000 ሜትርና በ10 ሺሕ ሜትር ውድድሮች ይከናወናሉ፡፡ በአጭር ርቀት በወንዶች 110 ሜትር መሰናክል፣ 400 ሜትር ዱላ ቅብብል፣ 100 ሜትር መሰናክል ውድድሮች ይካሄዳሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በሜዳ ተግባር፣ አሎሎ ውርወራ፣ ሥሉስ ዝላይና የምርኩዝ ዝላይ ውድድሮች ይጠበቃሉ፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ተሳታፊ ያጣበት የ20 ኪሎ ሜትር የዕርምጃ ውድድር በሻምፒዮናው እንደሚከናወን ተገልጿል፡፡ 

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በ1963 ዓ.ም. የተጀመረው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በርካታ አንጋፋ አትሌቶችን ማፍራት ችሏል፡፡ በቅብብሎሽ 53ኛ ዓመቱ ላይ የደረሰው ሻምፒዮናው በዓመቱ አዳዲስ አትሌቶችን እያፈራ ቀጥሏል፡፡ 

በዚህም መሠረት አዳዲስ አትሌቶችን ለመመልመል ከዓለም አትሌቲክስ ፈቃድ ያገኙ ማናጀሮች፣ የማናጀር ተወካዮች፣ እንዲሁም በዓለም አቀፍ መድረክ ልምድ ያካበቱ አሠልጣኞች በሻምፒዮናው ይገኛሉ፡፡

በተለይ በሻምፒዮናው በዓለም አቀፍ መድረክ መካፈል የቻሉ አትሌቶች የሚሳተፉበት በመሆኑ በአዳዲስ አትሌቶች የሚፈተኑበት መድረክ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ 

ሻምፒዮናው አዲስ ክብረ ወሰኖች ሲመዘገቡበት የኖረ ሲሆን በተለይ በ2014 ዓ.ም. በሐዋሳ ስታዲየም በተከናወነው 51ኛው አትሌቲክስ ሻምፒዮናው በወንዶች 10 ሺሕ ሜትር ለ16 ዓመታት ተይዞ የቆየው ክብረ ወሰን መስበር መቻሉ ይታወሳል፡፡ በሐዋሳው ሻምፒዮና በወንዶች 10 ሺሕ ሜትር ታደሰ ወርቁ 28፡11፡92 በመግባት የ16 ዓመቱን በስለሺ ስህን ተይዞ የነበረውን 28፡16፡23 ክብረ ወሰን መስበር የቻለበት ነበር፡፡

በተመሳሳይ በሴቶች 10 ሺሕ ሜትር ግርማዊት ገብረ እግዚአብሔር 31፡21፡48 በመግባት የሻምፒየናው ሌላኛውን ክብረ ወሰን መስበር ችላ ነበር፡፡

ግርማዊት በ2011 ዓ.ም. የትራንስ ኢትዮጵያ አትሌት በነበረችው ለተሰንበት ግደይ ተይዞ የነበረውን 32፡10፡13 ክብረ ወሰን ማሻሻል ችላለች፡፡ 

ዘንድሮ በየትኛው ርቀት አዲስ ክብረ ወሰን ይመዘገባል ለሚለው ጥያቄ ከጥር 21 ጀምሮ ለስድስት ቀናት በሚከናወነው ሻምፒዮና ምላሽ ያገኛል፡፡

በአንፃሩ የሻምፒዮናው አብዛኛው ውድድሮች በትራክ ላይ የሚከናወኑ መሆናቸውን፣ ትራኩም ብቸኛ የልምምድ እንዲሁም የውድድር አማራጭ መሆኑን ተከትሎ እርጅና እየተጫጫነው እንደሆነ በተደጋጋሚ ሲነሳ ቆይቷል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም አትሌቶች በርቀቶቹ ሊያስመዘግቡ የሚፈልጉትን ሰዓት ለማምጣት አዳጋች እንደሚሆንባቸው በተደጋጋሚ ሲያነሱ ከርመዋል።  ይህም በአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ ዘንድ ቅሬታ ሲነሳበት የሰነበተ ጉዳይ ሆኗል፡፡ 

በልምምድ ሥፍራ ዕጦት እየተፈተኑ የሚገኙት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ባገኙት መድረክ ሁሉ መንግሥት ጆሮ እንዲሰጣቸው ሲማፀኑ መመልከት እየተለመደ መጥቷል፡፡ በዓለም አትሌቲክስ መድረክ ስሟን መትከል የቻለችው ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ውድድር ማስተናገድ እንደሚጠበቅበትም ይነሳል፡፡ 

በተለይ ቀድሞ ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድሮች ማስተናገድ ብርቅ የሆነበት አፍሪካ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተወሰኑ አገሮች እየተስተናገዱ መምጣታቸውን ተከትሎ ኢትዮጵያስ? የሚል ጥያቄን እየጫረ ከመጣ ሰነባብቷል፡፡ በዓለም አትሌቲክስ ፈቃድ ካለቸው የአትሌት ማናጀሮች  በሚሰነዘረው አስተያየት መሠረት፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ሻምፒዮናዎች ማስተናገድ እንዲያስችላት የአገር ውስጥ ውድድሮችን ማዘመን ይጠበቅባታል፡፡

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በሚከናወኑት ዓመታዊ ውድድሮች ላይ የሚመዘገቡ ሰዓቶች በቀጥታ በዓለም አትሌቲክሱ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖራቸው መሥራት እንደሚገባ ያስረዳሉ፡፡ ይህም በተለይ በአገር ውስጥ ውድድሮች ላይ የሚመዘገቡ ሰዓቶች በዓለም አቀፍ ውድድሮች ጋር ተቀራራቢ መሆናቸውን ተክትሎ፣ ኢትዮጵያ ውድድሮቿን ማዘመን እንደሚገባት ይመክራሉ፡፡

እ.ኤ.አ. በ2021 ኬንያ ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮን ለመጀመሪያ ጊዜ ማስተናገድ መቻሏ ይታወሳል፡፡ 

በ2024 የዓለም አትሌቲክስ መርሐ ግብር መሠረት ኬንያ፣ ቦትስዋና፣ ካሜሮንና ደቡብ አፍሪካ የተለያየ ውድድሮችን ለማሰናዳት ኃላፊነት ወስደዋል፡፡

በአንፃሩ በዓለም አቀፍ መድረክ በአትሌቲክሱ ስሟን የተከለችው ኢትዮጵያ የዓለም አትሌቲክስን ውድድር ከማዘጋጀት ይልቅ ለአትሌቶች የልምምድ ሥፍራ ማቅረብ ምጥ ሆኖባታል፡፡ ለዚህም ፌዴሬሽኑ እንዲህም መንግሥት ከፊት ለፊታቸው ትልቅ የቤት ሥራ ይጠብቃቸዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...