Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊዳግም የተነሳው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል

ዳግም የተነሳው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል

ቀን:

ለብዙ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች መነሻ በመሆን ለበርካታ አሠርታት የኪነ ጥበብ መፍለቂያ በመሆን ሲያገለግል ቆይቷል፡፡

በዚህም ብዙዎች ባገኙት አጋጣሚ የዋለላቸውን ውለታ ለኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ዕድገት ያበረከተውን ጉልህ ሚና ሳይመሰክሩ አያልፉም፡፡

ይህ ለብዙዎች ባለውለታ የሆነውና ዕውቅ ከያንያን የማይፋቅ አሻራቸውን ዛሬም የማይደበዝዝ ትዝታቸውን ያስቀመጡበት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል ላለፉት ዓመታት ሥራ ፈትቶ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ዳግም የተነሳው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
ድምፃዊ ጎሳዬ ተስፋዬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኪነ ጥበብ ምሽት ላይ ንግግር ሲያደርግ

 በመሆኑም በተማሪዎች ጥያቄ በኪነ ጥበብ አፍቃሪያን ውትወታና በዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ቀና ትብብር ባለፈው ኅዳር 13 ቀን 2016 ዓ.ም. አንጋፋ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ አርቲስቶችና የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በተገኙበት ከአሥር ዓመት መዘጋት በኋላ ዳግም ወደ ሥራ መመለሱ ይፋ ተደርጓል፡፡

የባህል ማዕከሉ ወደ ሥራ ከተመለሰ በኋላ በየሳምንቱ ረቡዕ አመሻሽ ልዩ የሆነ የኪነ ጥበብ መሰናዶ ማቅረብ ከጀመረ ጥር 8 ቀን 2016 ዓ.ም. ሰባተኛ ሳምንቱን ይዟል፡፡

በዚህ የኪነ ጥበብ ምሽት ተማሪዎች ግጥሞችን፣ ተውኔቶችንና ሙዚቃን እያዘጋጁ ለታዳሚዎች ያቀርባሉ፡፡

መድረኩን ልዩ የሚያደርገው ገጣሚዎችም ሆኑ ጀማሪ ድምፃውያን ሥራቸውን  ለታዳሚያን አቅርበው ከመድረክ አይወርዱም፡፡ ይልቁንስ ወጣትና አንጋፋ አርቲስቶች በመድረኩ እየተገኙ አስተያየታቸውንና ሙያዊ ምክራቸውን ይለግሷቸዋል፣ ያበረታቷቸዋል፡፡

አርቲስቶቹ አዜብ ወርቁ፣ ገነት ንጋቱ፣ ግሩም ዘነበና ሰለሞን ቦጋለ የወሩ ‹‹የአንድ ግጥም የአንድ ወግ እንግዳ›› በሚለው የኪነ ጥበብ ምሽት መድረክ በመገኘት ሙያዊ ምክርና አስተያየታቸውን የሰጡ አርቲስቶች ናቸው፡፡

በጥር 8ቱ የወሩ የኪነ ጥበብ ምሽት ‹‹የአንድ ግጥም የአንድ ወግ›› እንግዳ ድምፃዊ ጎሳዬ ተስፋዬ ነበር፡፡

ድምፃዊ ጎሳዬ ታዳሚዎችን ያስተምራሉ ያላቸውን አንዳንድ ተሞክሮዎቹን  አቅርቧል፡፡ የድምፃዊ ቴዎድሮስ ታደሰና የድምፃዊ ሙሉቀን መለሰ አድናቂ እንደሆነ የገለጸው ድምፃዊ ጎሳዬ፣ መርካቶ ተወልዶ ስለማደጉና ከድምፃዊ አብዱ ኪያር ጋር በመሆን ወደ ቪዲዮ ቤት በመሄድ የተለያዩ የውጭ አገር ፊልሞችን በመመልከት ቀዳሚ እንደነበር  ያስታውሳል፡፡

‹‹አዳዲስ ነገሮችን ለመሞከር እንድደፍር ያደረገኝ ከልጅነቴ እያየሁ ያደግኩት ነገር ነው ብዬ አስባለሁ፤›› የሚለው  ጎሳዬ፣ እንደ ብዙዎቹ አርቲስቶች በማኅበራዊ ሚዲያ ልታይ ልታይ የማትልበት ምስጢር ምን ይሆን? ተብሎ ሲጠየቅ ‹‹በአያት እጅ ተቀማጥዬና ተቀጥቼ በሥርዓት ማደጌ ሳይሆን አይቀርም፤›› ሲል ተናግሯል።

‹‹ሁልጊዜ ባለቤቴን እንድታመሰግኑልኝ እፈልጋለሁ›› የሚለው አርቲስቱ ራሱ ከሚፈጥረው መልካም ግንኙነት ባሻገር ባለቤቱ ሥርዓት ያላት የቤተ ክርስቲያን ልጅ እንደመሆኗ ነገሮችን በሥርዓት በማድረግ አባቶችን እያከበርን የሚጠበቅብንን ግዴታችንን እየተወጣን መኖር እንጂ ወጣ ወጣ ማለቱ አስፈላጊ አይደለም፣ ሥራው ከወጣ ይበቃል፤›› ሲል ገልጿል፡፡

በሌላ በኩል ስለአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ሲናገር ‹‹በአገራችን በአራቱም አቅጣጫ ያለውን ነገር ሁላችሁም ታውቁታላችሁ፣ ከሁላችንም የሚደበቅ አይደለም ልባችንን እየሰበረ ያለ የሰላም ማጣት አለ፣ ሕፃናት ልጆቻችን አረጋውያንና ወጣቶች ባልተገባ ሁኔታ ሕይወታቸውን እየገበሩ ስላሉበት ሁኔታ የተሰማኝን ጥልቅ ሐዘን እንደ ኢትዮጵያዊነቴ ልገልጽላችሁ እወዳለሁ፤›› በማለት ተናግሯል፡፡

በመድረኩ የአርት ተማሪዎች ሙዚቃቸውን ያቀረቡ ሲሆን ገጣሚዎችም ግጥሞቻቸውን ለግቢው ማኅበረሰብ አቅርበዋል፡፡ ‹‹ምንትስ›› የሚል ርዕስ ያለው የመድረክ ላይ ተውኔትን በግጥም የታጀበ የአናን ማስታወሻና ሌሎች በራሳቸው የተደረሱ ተውኔቶች በአንድ ትዕይንት ላይ አቅርበዋል፡፡

‹‹ልጆቹን ማመስገን እፈልጋለሁ በጣም ጎበዝ ናቸው፣ በርቱ ማለት እፈልጋለሁ፤›› ሲል ለሁሉም ተሳታፊዎች አስተያየቱን የሰጠው አርቲስቱ ታላላቅ ሰዎችን ካፈራው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከምትማሩ ተማሪዎች ብዙ ነገር እጠብቃለሁ ሲል ያክላል፡፡

‹‹ከእናንተ አንደበት የሚወጣው ኪነ ጥበብ አገራዊ ችግሩንም ሆነ መልካም ነገሩን በማሳየት ማኅበረሰቡን ያነቃቃል፤›› በማለት አርቲስት ጎሳዬ ተናግሯል፡፡ ‹‹ብትችሉ ግብስብስ የሆነ ፖለቲካ በውስጣችሁ እንዳይተራመስ በዘርና በጎሳ እንዲሁም በሃይማኖትና በመሳሰሉት ቀሽም ነገሮች ውስጣችሁ እንደማይረታ እምነቴ ነው፤›› በማለት ምክሩን ለግሷል፡፡

ሁሉም የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በቴአትር ጥበባትም ይሁን በኪነ ጥበብም በሙዚቃው ዘርፍ የሚሰማችሁንና ትክክለኛውን ነገር ተናገሩ ያለው አርቲስቱ፣ ‹‹መንግሥትን መውቀስ ያለባችሁ ነገር ካለ መውቀስ፣ ማበረታታት ያለባችሁ ማኅበረሰብን እያበረታታችሁና እየረዳችሁ እንድትቀጥሉ እፈልጋለሁ፤›› ብሏል፡፡

ሰባት ሳምንታትን ያሳለፈው የኪነ ጥበብ ምሽት ተማሪዎች በጉጉት የሚጠብቁትና የሚናፍቁት ምሽት እየሆነ መጥቷል ያሉት የባህል ማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ተስፋዬ እሸቱ (ረዳት ፕሮፌሰር) ናቸው፡፡

ተማሪዎች ከተጠበቀው በላይ ወደ ኪነ ጥበብ ምሽቱ በመግባታቸው አዳራሹ ሞልቶ ፕሮግራሙን ለመታደም የማይችሉ ተማሪዎች ጥቂት አይደሉም፡፡

ችግሩን ለመቅረፍ ትልቅ አዳራሽና ትልቅ የድምፅ ሲስተም እንደሚያስፈልገው የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ይህንን ለማድረግ ደግሞ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቃል እንደገባላቸው ገልጸዋል፡፡

የባህል ማዕከሉ ከሌሎች የኪነ ጥበብ መፍለቂያዎች የሚለየው ከሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች የሚመጡ ባለተሰጥኦዎች ገጣሚዎች፣ ዘፋኞችና ሌሎችም የኪነ ጥበብ ዝንባሌ ያላቸው ተማሪዎች በኅብረት የሚገኙበት በመሆኑ እንደሆነ ተስፋዬ ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...