Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊዓመቱን በዓለም ደረጃ የሚያከርመው የሉሲ ግኝት የወርቅ ኢዮቤልዩ

ዓመቱን በዓለም ደረጃ የሚያከርመው የሉሲ ግኝት የወርቅ ኢዮቤልዩ

ቀን:

  • 2024 ‹‹የሉሲ ዓመት›› ተብሎ ተሰይሟል

በየማነ ብርሃኑ

በሳይንሳዊ ስሟ ‹አውስትራሎፒቲከስ አፋራንሲስ› በመባል የምትታወቀውና የ3.2 ሚሊዮን ዓመት ዕድሜ ያላት የሉሲ ቅሬተ አካል የተገኘበት 50ኛ ዓመት ዓመቱን ሙሉ እንደሚከበር ተገለጸ፡፡

‹ድንቅነሽ› የሚል አገራዊ መጠርያ የተሰጣት የሉሲ ቅሬተ አካል በአፋር አዋሽ ወንዝ አቅራቢያ ሀዳር በተሰኘ ቦታ ኅዳር 15 ቀን 1967 ዓ.ም. (ኖቨምበር 24 ቀን 1974) በአሜሪካዊው ዶናልድ ጆንሰንና ፈረንሣዊው ማውረስ ታይብ መገኘቷ ይታወቃል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ዓመቱን በዓለም ደረጃ የሚያከርመው የሉሲ ግኝት የወርቅ ኢዮቤልዩ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
የአሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ የሰው ዘር አመጣጥ ኢንስቲቲዩት ዳይሬክተር ዮሐንስ ኃይለ ሥላሴ (ፕሮፌሰር)

ቅሪተ አካሏ፣ አንድ ሜትር ከ10 ሳንቲ ሜትር ቁመት ነበረው። 40 በመቶውን አካል የሚሸፍኑ ቁርጥራጭ ቅሪተ አካላቷም አብረዋት ነበር  የተገኙት።

ዘንድሮ 49 ዓመቱ ባለፈው ኅዳር ያለፈው ሳይንሳዊው ግኝትን እስከ ኅዳር 15 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ እንደሚከበር፣ በብሔራዊ ሙዚየም የተገኙት የአሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ የሰው ዘር አመጣጥ ኢንስቲቲዩት ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ዮሐንስ ኃይለ ሥላሴ አስታውቀዋል፡፡

የጎርጎርዮሳዊው ቀመር አዲስ ዓመት (2024) ‹‹የሉሲ ዓመት›› (The Year of the Lucy) ተብሎ ዓመቱን በሙሉ በልዩ ሁኔታ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበርም ገልጸዋል፡፡

ክብረ ቀኑን ለማስጀመርም የሉሲ ቅሬተ አካልን ካገኙት አንዱ በሆኑት በዶናልድ ጆሃንሰን (ፕሮፌሰር) የተመራ፣ ከአሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ የሰው ዘር አመጣጥ ኢንስቲቲዩት 25 አባላትንና ደጋፊዎች የያዘው ቡድን፣ ጥር 8 ቀን 2016 ዓ.ም. በብሔራዊ ሙዚየም የሉሲ ቅሬተ አካልን እና ከሰው ዘር አመጣጥ ጋር የተያያዙ የተለያዩ ስብስብ ክፍሎችን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ላይ በአሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ የሰው ዘር አመጣጥ ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ዮሐንስ ኃይለ ማርያም (ፕሮፌሰር)፣ ሉሲ እና ሌሎችም የቅድመ ሰው ቅሪቶች ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ መሆኗን ለዓለም ያስተዋወቁ፣ በቅድም ሰው ዘር አመጣጥ ታሪክ ላይም ስሟን በቀዳሚነት ያስቀመጡ ናቸው ብለዋል፡፡

 ዩኒቨርሲቲያቸው የሉሲን 50ኛ ዓመት አስመልክቶ የፎቶ ዓውደ ርዕዮችን፣ ሲምፖዚየሞችንና ሌክቸሮችን በማዘጋጀት ዓመቱን የሉሲ ዓመት ብሎ በመሰየም እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ሉሲ በኢትዮጵያ መገኘቷ በቅድመ ሰው አመጣጥ ዙሪያ በተመራማሪዎች ለሚደረገው ምርምር ታላቅ ስኬት የነበረ መሆኑን የተናገሩት ፕሮፌሰሩ ዮሐንስ፣ ሉሲን መዘከርና ማስታወስ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ በድጋሚ ማስተዋወቅና ስሟንም ከፍ ማድረግ መሆኑን በመረዳት ኢንስቲትዩታቸው ይህንን የጉብኝት መርሐ ግብር አዘጋጅቷል ብሏል፡፡

ቅሪተ አካሏን ካገኙ ከሰዓታት በኋላ፣ በምሽቱ አረፍ ብለው ካዳመጡት የ1960ዎቹ የቢትልሶች ዘፈን ‹‹Lucy in the Sky with Diamond›› (በግርድፉ ሲመለስ ሉሲ ባለአልማዛዊው ሰማይ) መጠርያውን ሉሲ እንዳገኘች ይነገርላታል፡፡

ኢቭ ኮፐንስ የ3.2 ሚሊዮን ዓመት ባለዕድሜዋ ሉሲ ቅሬተ አካሏን ያገኙት አሜሪካዊው ዶናልድ ጆሃንሰን እና በሕይወት የሌሉት ፈረንሳውያኑ ኢቭ ኮፐንስና ሞሪስ ታይብ ናቸው፡፡ ሦስቱ ተመራማሪዎች ቅሬተ አካሏን ካገኙ ከሰዓታት በኋላ ምሽት ላይ አረፍ ብለው ካዳመጡት፣ የ1960ዎቹ የቢትልሶች ዘፈን ‹‹Lucy in the Sky with Diamond›› በመነሳት ለቅሬተ አካሏ ሉሲ የሚል መጠርያ መስጠታቸው ይታወቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...