Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ክለቡ ጠቅላላ ጉባዔን እንዲጠራ ጥያቄ ሊያቀርቡ ነው

የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ክለቡ ጠቅላላ ጉባዔን እንዲጠራ ጥያቄ ሊያቀርቡ ነው

ቀን:

  • ፌዴሬሽኑ ጠቅላላ ጉባዔን በተመለከተ አስገዳጅ ደንብ ማውጣቱን አስታውቋል

የአንጋፋው ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ደጋፊ አባላት፣ ክለቡ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ እንዲጠራ ጥያቄ ሊያቀርቡ እንደሆነ ተጠቆመ፡፡

ለ16 ጊዜ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆን የቻለው ክለቡ ጠቅላላ ጉባዔውን ከጠራ አምስት ዓመት እንዳለፈው የሚገልጹት ደጋፊ አባላቱ፣ ዘንድሮ ጉባዔውን እንዲያደርግ ለክለቡ ቦርድ አባላት ጥያቄ እንደሚያቀርቡ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

ደጋፊ አባላቱ፣ ክለቡ የመጨረሻ ጉባዔውን የጠራው መስከረም 14 ቀን 2010 ዓ.ም. መሆኑን ጠቅሰው፣ ምንም መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ሳይደረግ ለዓመታት ቆይቷል ብለዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ከዚህ ጋር ተያይዞም አሁን ክለቡን እያስተዳደሩ የሚገኙ የቦርድ አባላት የተመረጡት ግንቦት 28 ቀን 2008 ዓ.ም. ሲሆን፣የአራት ዓመት የማስተዳደር ዘመናቸው የተጠናቀቀው በ2012 ዓ.ም. ቢሆንም ምርጫ ሳይከናወን ለዓመታት መዝለቃቸው ጠቅሷል።

በዚህም መሠረት ክለቡ ባለፉት ዓመታት ያከናወናቸው የተለያዩ ውሎች ጥያቄ ሊያስነሱ የሚችሉ መሆናቸውን፣ ደጋፊ አባላቱ አስተያየታቸውን ሰንዝረዋል፡፡

አንድ ክለብ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን መጥራት የሚገደድበት አሠራር  በክለቡ መተዳደርያ ደንቡ ውስጥ ቢካተትም፣ ተግባራዊ አለመሆኑ አግባብ እንዳልሆነ አባላቱ ያስረዳሉ፡፡ 

በመደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ የክለቡን ቀጣይ አቅጣጫና አዳዲስ የለውጥ ሐሳቦች የሚንሸራሸሩበት፣እንዲሁም በአራት ዓመታት አዲስ አመራሮች የሚሾሙበት አሠራር ቢኖርም፣ ሳይተገበር ቆይቷል ብለዋል።

ከዚህም በላይ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አማካይነት በሚከናወኑ ውድድሮች ላይ ለመሳተፍ፣ክለቦች ማሟላት ከሚገባቸው አንኳር ጉዳዮች መካከል መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔያቸውን ማድረግ እንደሆነ ተቀምጧል፡፡በአንፃሩ ክለቦች ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ሳያከናውኑ ውድድር ላይ እንዲካፈሉ መፈቀዱ አግባብ አይደለም ብለው የሚከራከሩ አሉ፡፡ 

በአንፃሩ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከዚህ ቀደም በደንቡ ውስጥ አስገዳጅ ሕግ አለመካተቱን ገልጾ፣ በቀጣይ በደንቡ ውስጥ አካቶ ተግባራዊ እንደሚያደርግ፣ የፌዴሬሽኑ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

‹‹ከዚህ ቀደም ክለቦች ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔያቸውን እንዲያደርጉ ባናስገድድም ከቀጣይ የፌዴሬሽኑ ጠቅላላ ጉባዔ በኋላ፣ማንኛውም ክለብ ጠቅላላ ጉባዔውን እንዲያከናውን የሚያስገድድ አዲስ ደንብ አካተናል፣ ተግባራዊም ይሆናል›› በማለት አቶ ባህሩ ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ላይ የሚካፈሉ በርካታ ክለቦች በዓለም ደረጃ ክለቦች የሚከተሉትን ዘመናዊ የክለብ አስተዳደር አለመከተላቸው ይተቻል፡፡በተለይ በፊፋና በካፍ የተቀመጠውን የክለብ ላይሰንሲንግ ደረጃ አለማሟላታቸው ይጠቀሳል።

የክለብ ፈቃድ አሰጣጥ በፊፋና በካፍ የተቀመጡ የእግር ኳስ መለኪያዎችን በኢትዮጵያ እግር ኳሱ የጥራት ደረጃውን የጠበቀና ፕሮፌሽናል ሆኖ እንዲጓዝ መቆጣጠር እንደሆነ ያስቀምጣል፡፡

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የክለብ ላይሰንሲንግ ጉዳይ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑ መግለጹ ይታወሳል፡፡የክለብ ላይሰንሲንግ ዲፓርትመንት ተጠሪነቱ ለፌዴሬሽኑ ጽሕፈት ቤት ሲሆን፣የፊፋና የካፍ ፕሮፌሽናል ፉት ቦል ዲፓርትመንት የሚያወጧቸውን መመርያዎች በማጣጣም በሚወጡ መመዘኛዎች አማካይነት ቁጥጥር ያደርጋል።

የክለብ ፈቃድ ከሚያካትታቸው ጉዳዮች መካከል ከምዝገባ ጀምሮ ሕጋዊ አስተዳደርና የፋይናንስ አሠራር፣መሠረተ ልማቶችና ስፖርታዊ መሥፈርቶች መሟላታቸው ይገኙበታል።

በአንፃሩ በክለብ ሳይሰንሲንግ መሥፈርት መሠረት በቀጥታ ስለክለቦች ጠቅላላ ጉባዔ መጥራትና አለመጥራት በግልጽ ያስቀመጠው ነገር ባይኖርም፣የክለቦችን አስተዳደራዊ ጉዳዮችን ግን አካትቷል፡፡

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ምሥረታ ሒደት ታሪካዊ መሠረት እንዳለው የሚነገረው ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ፣በኢትዮጵያ ከሚገኙ ክለቦች መካከል በአደረጃጀት፣ እንዲሁም በአስተዳደራዊ ጉዳዮች የተሻለ እንደሆነ ሲነገር ቆይቷል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ክለቡ ለከፍተኛ የመዋቅር ችግርና የገንዘብ ዕጦት መዳረጉ ይደመጣል፡፡በተለይ የክለቡ የበላይ አስተዳዳሪ አቶ አብነት ገብረ መስቀል ክስ ተመሥርቶባቸው በሕግ ጥላ ሥር መዋላቸውን ተከትሎ፣በክለቡ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ላይ መንገዳገዶች መስተዋላቸው እየተነሳ ሲሆን፣የክለቡ ደጋፊዎችም ቦርዱ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ጠርቶ የክለቡን ህልውና መታደግ ይገባዋል የሚል አስተያየት እየሰነዘሩ ይገኛሉ፡፡

የክለቡ ደጋፊዎች የጠቅላላ ጉባዔ ይጠራ ጥያቄን በተመለከተ ሪፖርተር የክለቡን ሥራ አስኪያጅ ለማነጋገር ያደረገው ጥረት አልተሳካም።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...