Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊለአውት ሶርሲንግ አስቻይ ፖሊሲ እንዲኖር ተጠየቀ

ለአውት ሶርሲንግ አስቻይ ፖሊሲ እንዲኖር ተጠየቀ

ቀን:

በቀጣዮቹ ስድስት ዓመታት ውስጥ ለግማሽ ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ማቀዱን የኢትዮጵያ ዓውት ሶርሲንግ ማኅበር አስታወቀ፡፡ ለአውት ሶርሲንግ አስቻይ ፖሊሲ እንዲኖርም ጠይቋል፡፡

ከዚህ በፊት የነበሩ ፖሊሲዎች ከተሻሻሉና ምቹ የሥራ አካባቢ ከተፈጠረ እ.ኤ.አ. 2030 ለግማሽ ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድልን መፍጠር እንደሚቻል የማኅበሩ ዋና ኃላፊ ታዲዎስ ተፈራ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ለአውት ሶርሲንግ አስቻይ ፖሊሲ እንዲኖር ተጠየቀ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚልና አቶ ንጉሡ ጥላሁን በመድረኩ
ተገኝተዋል

ማኅበሩ ላለፉት አራት ዓመታት 15 ሺሕ ለሚሆኑ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠሩን፣ ታኅሣሥ 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በጋራ ለመሥራት ባደረጉት ውይይት ላይ ገልጸዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በውይይቱም የዲጂታል ኢንዱስትሪውን ለማሻሻልና ወጣቶችን ተሳታፊ ለማድረግ የተለያዩ ሥልጠናዎችን ከመስጠት ጀምሮ ቋሚ የሥራ ዕድልን እስከመፍጠር የሚደርስ ሥራን በትብብር ለመሥራት ቃል ተገብቷል፡፡

በብዛት የሚሠሩ ሥራዎች ዲጂታል ቴክኖሎጂንና ኢንተርኔትን መሠረት አድርገው የሚሠሩ መሆናቸውንና ለአብነትም ወጣቶች ኮምፒዩተራቸውን በመጠቀም ከውጭ የሚገቡና ወደ ውጭ አገር የሚላኩ ዕቃዎችን በቀላሉ በመላክና በመቀበል የተሻለ ገቢን ማግኘት ይቻላል ብለዋል፡፡

ሥራውን ለማከናወን የቋንቋ ክህሎትና በቂ የኮምፒዩተር ዕውቀት ካላቸው በቀላሉ መሥራት እንደሚችሉ አብራርተዋል፡፡     

ከሥራው ጋር የሚገናኙ ሥልጠናዎችን በመስጠት፣ አዳዲስ ወጣቶችን ወደ ሥራ እንዲገቡ በማድረግ ብዙ ጊዜ፣ ገንዘብና ጉልበት የሚጠይቁ አሠራሮችን በማስወገድና በቴክኖሎጂ አሠራር በመቀየር በስፋት እንደሚሠራም ታዲዎስ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

በማኅበራዊ ትስስር ሚዲያ ላይ ተሳትፎ የሚያደርጉና ለቴክኖሎጂ ቅርበት ያላቸው ወጣቶች ሥራውን ለመሥራት ብዙም እንደማይቸገሩም አክለዋል፡፡

‹‹የታክስ ጉዳዮችን ጨምሮ ሌሎች ማበረታቻዎች ከተደረገላቸው ዘርፎች አንዱ አውትሶርሲንግ ነው፤›› ያሉት የሥራና የክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ናቸው፡፡

ሥራው በአዲስ መልክ በመጀመሩ በተለይ የቴሌኮም ሥራ መስፋፋትን ተከትለው እየተፈጠሩ ያሉ መልካም ዕድሎችን በመጠቀም፣ በመስኩ ሰፋ ያለ እንቅስቃሴ እንዲኖር እየተሠራ መሆኑን ወ/ሮ ሙፈሪያት ጠቅሰው፣ በሰው ኃይል ዙሪያ በመሥራት አገልግሎት ከሚሰጡት ባሻገር ዕውቀትንም አውት ሶርሲንግ የማድረግ ዕድል እንዳለ ጠቁመዋል፡፡

‹‹ወጣቶች ራሳቸውን ብቁ አድርገው እንዲሠሩ ማበረታታት ይገባል፤›› ያሉት ሚኒስትሯ፣ ኮሌጆችን ጨምሮ በዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ የሥልጠና ሥርዓተ ትምህርት ተዘጋጅቶ በትኩረት እየተሠራበትና የውጭ ምንዛሪን ወደ አገር ውስጥ በማስገባት ረገድም የራሱ አበርክቶ አለው ሲሉ አክለዋል፡፡

ማኅበሩ ላለፉት ሦስት ዓመታት ሲሠራ እንደነበር አውስተው፣ በአሁኑ ወቅት በአዲስ መልኩ በስፋት ለመሥራት አቅዶ ወደ ሥራ መግባቱንና አዳዲስ ኩባንያዎችም ወደ መስኩ እየገቡ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

ዘርፉ ዘንድሮ ወደ 50 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ወደ አገር ያስገባል ሲሉ ወ/ሮ ሙፈሪያት አስረድተዋል፡፡

በቀጣይ ሊያጋጥሙ ይችላሉ የተባሉ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ ከፖሊሲ ጀምሮ የሕግ ማዕቀፎች እየተዘጋጁ መሆኑንም ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡

ዘርፉ አዲስ እንደመሆኑ በርካቶች እንዲገቡበት የማበረታቻ ሥራዎች እየተሠሩ እንደሆነም አክለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...