Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅታሪክን ወደ ሁዋላ እና ወደፊት

ታሪክን ወደ ሁዋላ እና ወደፊት

ቀን:

በታሪካችን የጨለማ ገጾቻችን መካከል ስንቀዝፍ አልፎ አልፎ ሚጢጢ የብርሃን ደሴቶች ያጋጥሙናል፡፡ በቀደም ‹‹ያች ቀን ተረሳች›› የሚል ርዕስ ያለውን አቧራ የጠገበ አሮጌ መጽሐፍ ገረብኩ፣ በሙሶሎኒ ወረራ ወቅት በስደትና በአርበኝነት የታገሉ ገብረሕይወት ህዳሩ የተባሉ ምሁር የጻፉት ነው፡፡ ሰውየው ታላቅ ሰው ቢሆኑም እንዳለመታደል ሆኖ የጽሑፍ ስጦታ አልተሰጣቸውም፣ መጽሐፋቸው እንደ መከራ ቀን በቀላሉ አይገፋም፣ ለታግሶ ለዘለቀው ብዙ የሚገርሙ ምስክርነቶችን ያገኛል::

አንድ ቀን ገብረሕይወት ደባርቅ አካባቢ ከሌሎች አርበኞች ጋር ሆነው ወደ ቤተክርስቲያን ይሄዳሉ፣ ቤተክርስቲያኑ በር ላይ አንዲት በሽተኛ መሳይ መነኩሲት ኩርምት ብለው ተቀምጠዋል፡፡

‹‹እማሆይ ምንድነው እሚያምዎት?›› አሉ ገብረሕይወት፣

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

‹‹ከረሃብ በቀር ሕመም የለብኝም›› ሲሉ መለሱ መነኩሴይቱ፣

በዚህ ምላሽ ልባቸው የተነካው፣ ገብረህይት፣ አርበኞች ያላቸውን እንዲመጸውቷቸው ማስተባበር ጀመሩ፣ በዚህ ጊዜ፣ በቦታው ራስ ውብነህ ተሰማ እሚባሉ አርበኛ ነበሩ፣ ከዝናራቸው ጥይት አውጥተው ለመነኩሴቱ እጃቸውን ዘረጉ፣ በጊዜው ጥይት ዶላር ማለት ነው፣ ትልቅ ዋጋ ያለው መገበያያ ስለሆነ ብዙ እህል የመሸመት አቅም ነበረው፣

እማሆይ ግን የጥይቱን ስጦታ ሊቀበሉ አልፈለጉም፣ ‹‹ምንም ቢርበኝ፣ ምንም በረሃብ አለቅጥ ብጠቃም የጀግናውን ጥይት አልቀበልም! በጥይቱ ጀግናው ሙያ ይሥራበት ‹‹የሚል ምላሽ ሰጡ፣

አርበኞች ባልተጠበቀው ምላሽ ተደንቀው እህል እንደሚመጸውቷቸው ቃል ገቡ፣

የሰዎች ምግባር የሚለካው በጣም ሲቸግራቸው ወይ በጣም ሲደላቸው ነው፣ ‹‹የራበው ዜጋ መሪውን ይበላል›› ይላል መረራ ጉዲና’፣ ግን መሪው በቀላሉ ራሱን ለመብልነት አያቀርብም፣ ስለዚህ የተራበ ሰው በቅርቡ ያገኘውን ይበላል፣ የአገሩን ንብረት ሊሸጥ ይችላል፣ ሸማች ካገኘ አገሩን እንደ ቦንዳ ጨርቅ ጠቅልሎ ለመቀወር ዓይኑን አያሽም! ከዚያም የባሰ አለ፣ በክፉ ቀን ልጆቻቸውን ቆርጥመው የበሉ ሰዎች በታሪክ ተመዝግበዋል፣ ራስን በሕይወት ማቆየት ከባድ ቀንበር ነው፣ ለዚያ ነው፣ የሠለጠኑ የሚባሉ አገሮች መንግሥታት ዜጎች መሠረታዊ ፍላጎታቸውን ማሟላትን ቀዳሚ ተግባራቸው አድርገው የሚይዙት! በዚህ መሀል፣ የእማሆይ ዓይነት›› ችግሬና ረሃቤ ከአገሬ አይበልጥም ‹‹የሚሉ ጥቂት ብርቅ ሰዎች ይኖራሉ፣ የኒህ ሰዎች መስዋዕትነት በዘመናችን እንደ ፋርነት ይቆጠራል፡፡

  • በዕውቀቱ ሥዩም በማኅበራዊ ገጹ እንደከተበው
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...