Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅእተርካለሁ፣ ስለዚህም እኖራሁ! “I Tell Stories, Therefore, I Exist!”

እተርካለሁ፣ ስለዚህም እኖራሁ! “I Tell Stories, Therefore, I Exist!”

ቀን:

በተማሪ ቤት ተምሬ አልተማርኩም

እተርካለሁ፣ ስለዚህም እኖራሁ! “I Tell Stories, Therefore, I Exist!” | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

ታሪኮቼ ተቀፍድደዋል

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የባህል ማጥፋት ተፈጽሞብኛል

በክፍል እንዳልናገር ታፍኜአለሁ

በጽሑፍ ሳንሱር ተደርጌአለሁ

ለንግግሬ ጆሮ ዳባ ተብያለሁ

በሚዲያ ውክልናዬ ተዛብጧል

በራዲዮ ተዋሽቻለሁ

በቴሌቪዥን ተዋርጃለሁ

በፊልም አልታይም የለሁ

በታሪክ ድንክዬ ተደርጌአለሁ

በሥነሰብዕ (በአንትሮፖሎጂ) እንደብርቅዬ እጎበኛለሁ

በትወና አገልጋይ ገጸ ባሕርይን ብቻ ተጫውቻለሁ

በሥነ መለኮትም ቅጽል ተሰጥቶኛል

ሆኖም በእንምቢባይነት መንፈስ

ታሪኬን እተርካለሁ

ከታፈንኩማ ህልውናዬ ኮስሶ ይጠፋል

እናማ ጠማማ ትምህርቴን

እያልተማርኩ

በቡሽ ማማ የማንነቴን አቅም ገነባሁ

አርቴፊሻል ፀጉሩ ወልቋል፣ ዊጉ ወልቋል

ወርቅ ያልሆነው ዝምታዬን ሰባበርኩ

ያልተነገሩ ታሪኮቼን በደብረ ጥሞና አደመጥኩ

በታሪኮች ላይ ታሪኮች ተደራርበው

በምስሎች ላይ ምስሎች ተዛዝለው

ተዘክሮዎች ሲዘንቡ

ዥረት ሆነው እንደወንዝም ሲፈስሱ

ስሙኝማ

ጆሮ ያላችሁ ሁላ

ስሙኝ

የኢ-ፍጹማዊነት የጉዞ ተረኮች

የሞራል፣ የክብር

የሰቀቀን፣ የተስፋ

ወደስሮቼ ስመለስ

በሳንኮፋ ወፍ ወደኋላ ዞር ስል

ትውስታዎቼ ተመለሱልኝ

በእናቴ ተረቶች ትዝታዎቼን አጣጣምኩኝ

እንደ ንሥርም ታደስኩኝ

ባትሪዬም ኃይሉ ሞላልኝ 

ወደልጅነቴ ስመለስ

ቤቴን አገኘሁኝ

ከማለዳ ጤዛ ጥበብን ቀዳሁኝ

‹‹ስሄድ አገኘኋት ስመለስ አጣኋት?››

ከልጅነት ባልንጀሮቼ ጋር እንቆቅልሽን ስንጫወት

ምስጢርን ታቅፌ፣ ጫጩት ሕይወትን ፈለፈልኩ

የእልምእዥቴን ቋጠሮ ፈታሁ

እናም በራዕዬ ለመብረር ታደስኩ

በእሳት-ዳር ዙሪያ ትምህርት

መሞቅ፣ ማካፈል፣ መማር፣

አዋቂው የእሳቱ ፍም ነበልባል መጪውን ይገልጣል  

ራዕይን እያደሰልኝ  

‹‹የእሳት ልጅ አመድ›› ብለው እንዳልወቀሱኝ

የአርበኛው አባቴ ዝምታም ብዙ ቅጽ ታሪክ እያወጋኝ

በጉልምስናዬ እያጽናናኝ

የተሰደደ ዝምታም ተመለሰልኝ

የአርምሞ ሲኒማ

ቅጽ በቅጽ ይተርካል

የሕይወቴ ምሰሶ

የኔ ቫይታሚን

ዓድዋ የኔ መድኅን

የአያቴን ዕድሜ ጠገብ ሽብሽባት

ገጿን ብቻ በማዬት

እኔው ከደዌዬ ተጠገንኩባት

በምርት ሦስት ሺሕ ዓመት

የሞቱት በሕይወት ያሉትን ሲቀሰቅሱ

እንዲህ አሉ

‹‹ሕያው ሙታን ተነሱ

ታሪካችሁን ውረሱ!››

ቃላዊ ተረኩን (ፎክሎሩን) ደጋግሜ አደመጥኩኝ

በተረኩ የሰው ልጅ ሲያንሰራራ ተመለከትኩኝ

እኔ ታሪክ ተናጋሪው

ስለምኖር፣ እተርካለሁ

እተርካለሁ፣ ስለዚህም እኖራለሁ።

  • በተክለጻድቅ በላቸው

በፊልም ሠሪውና በተራኪው በፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ ፊልሞች ንሸጣ የተጻፈና ተመልሶ ለጋሽ ኃይሌ የተበረከተ

spot_img
Previous article
Next article
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...