Sunday, March 3, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ሒጅራ ባንክ ባለፈው የሒሳብ ዓመት ከሰበሰበው ተቀማጭ ገንዘብ 80 በመቶውን ማበደሩን አስታወቀ

ተዛማጅ ፅሁፎች

ሙሉ ለሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት እየሰጡ ካሉ አራት ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው ሒጅራ ባንክ በ2015 የሒሳብ ዓመት ካሰባሰበው ተቀማጭ ገንዘብ ውስጥ 80 በመቶውን ፋይናንስ (ብድር) ማድረጉን አስታወቀ፡፡

ባንኩ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔው ላይ ባቀረበው ሪፖርት በሒሳብ ዓመቱ ያሰባሰበው ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘብ 4.84 ቢሊዮን ብር ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ ሦስት ቢሊዮን ብር ወይም 80 በመቶው ያህል ማበደሩን (ፋይናንስ ማድረጉን) አስታውቋል፡፡ ባንኩ በሒሳብ ዓመቱ የሰጠው ብድር መጠንም ከቀዳሚው ዓመት በ776 በመቶ ዕድገት ያሳየ ነው፡፡

ሒጅራ ባንክ በሒሳብ ዓመቱ የሰጠውን ብድር ከአጠቃላይ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት አንፃር ሲታይ በተለየ የሚታይ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ ይህንንም ሲያብራሩ በመስኮት ደረጃ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሚሰጡ ባንኮች ከሰበሰቡት ተቀማጭ ገንዘብ ለብድር ያዋሉት በአማካይ 39.8 በመቶ በመሆኑ ሒጅራ ባንክ ግን ከሰበሰበው ተቀማጭ ገንዘብ 80 በመቶውን ለብድር በማዋል በሒሳብ ዓመቱ ስኬታማ ሥራ መሥራቱን የሒጅራ ባንክ ቦርድ ሰብሳቢ አብዱሰላም ከማል ገልጸዋል፡፡

የተቀማጭ ገንዘብ ከማሰባሰብ አንፃርም ስኬታማ እንደሆነ የሚያመላክተው የቦርድ ሊቀመንበሩ ሪፖርት መጠን ከቀዳሚው ዓመት የ263 በመቶ ጭማሪ ያሳየ እንደሆነም ተገልጿል፡፡ ባንኩን አስቀማጮች ቁጥር በ160 ሺሕ (119 በመቶ) በማሳደግ በሒሳብ ዓመቱ መጨረሻ አጠቃላይ አስቀማጮቹን ቁጥር 295 ሺሕ ማድረስ ችሏል፡፡

የሒጅራ ባንክ በሒሳብ ዓመቱ 411.8 ሚሊዮን ብር የተጣራ ገቢ ማግኘታቸውንና የ2014 የሒሳብ ዓመት ከነበረው 23.2 ሚሊዮን ብር ጋር ሲነፃፀር የ1675 በመቶ ጭማሪ እንዳለው አመልክተዋል፡፡ የባንኩ ጠቅላላ ወጪ 384 ሚሊዮን ብር እንደነበር ያመለከቱት የቦርድ ሰብሳቢው ይህም ባንኩን ለመጀመርያ ጊዜ ወደ ትርፋማነት ያሸጋገረ ባንካቸው በተቋቋመ በሁለተኛው ዓመት ላይ ከግብር በፊት ያስመገበው 27.8 ሚሊዮን ብር ትርፍ ሊያገኝ ችሏል፡፡ ባንኩ የ2015 የሒሳብ ዓመት አፈጻጸሙን በተመለከተ ኦዲት ያልተደረገ ሪፖርቱ ባንኩ ከመጠባበቂያ ከልዩ ልዩ ተቀናሾችና ከግብር በፊት 70 ሚሊዮን ብር ማትረፉን አይዘነጋም፡፡

በባንኩ ሌሎች የወሰዱ አፈጻጸሞችን በተመለከተ የባንኩ ቦርድ ሰብሳቢ ባንካቸው ጠንካራ የፋይናንስ አቅም ላይ መድረሱ አስረድተዋል፡፡ በኢንዱስትሪው አንዳንድ ባንኮች ባጋጠማቸው የጥሬ ገንዘብ ፍሰት እጥረት ሲያጋጥማቸው ባንካቸው ያልገጠመው ስለመሆኑም ጠቅሰዋል፡፡ ‹‹ባለን ጥንቃቄ የተሞላበት የገንዘብ አያያዝና ካስቀማጮች ጋር ባለን ጠንካራ ግንኙነት ያለንበት የገንዘብ አቅም ከጠንካሮች ጎራ እንድንሰለፍ ረድቶናል፡፡

ባንኩ በሒሳብ ዓመቱ ምንም ዓይነት የተበላሸ ፋይናንስ ያላስመዘገበ ስለመሆኑም የጠቀሱት የቦርድ ሰብሳቢው ይህ አፈጻጸም ትልቅ ውጤት ስለመሆኑ ጠቅሰዋል፡፡ ‹‹በተለይ ካለፈው ፈታኝ የኢኮኖሚ ሁኔታ አኳያ ሲታይ ይህ ስኬት የጎላ ሲሆን የሥጋት ሪስክ ማኔጅመንታችን ጤናማ የፋይናንስ ሥርዓት ያለው መሆኑን ያሳያል ተብሏል፡፡

ባንኩ በቀጣይነት እተገብራቸዋለሁ ካላቸው ተግባራት መካከል ካፒታሉን ማሳደግ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመርያ መሠረት በቀጣይ ሦስት ዓመታት ካፒታላችንን ወደ አምስት ቢሊዮን ብር ማሳደግ ይጠበቅብናል፡፡ ባለአክሲዮኖች ይህንን ካፒታል ለመሙላት ተጨማሪ አክሲዮን በመግዛት ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ባንኩ የሀብት መጠኑን 78 በመቶ በማሳደግ 6.2 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡ ይህም የ176 በመቶ ዕድገት ያሳየ ነው፡፡ ሒጅራ ባንክ በሒሳብ ዓመቱ አጠቃላይ ቅርንጫፎች 71 መድረሳቸው ታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች