Friday, March 1, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

[ክቡር ሚኒስትሩ ከአማካሪያቸው ጋር ስለባህር ወደብ ባለቤትነት መሳካት እያወሩ ነው]

 • ሚዲያው በሙሉ በዚህ ጉዳይ ላይ ተጠምዷል።
 • በምን ጉዳይ ላይ?
 • የወደብና የባህር በር ጥያቄ ላይ።
 • እህ…
 • በተለይ የመንግሥት ሚዲያው…
 • እ…?
 • ሌት ተቀን እየሠራ ነው።
 • ጥሩ አድርገዋል።
 • ቢሳካማ ታሪካዊ ድል ነው ክቡር ሚኒስትር።
 • ትጠራጠራለህ እንዴ?
 • ምን ላድርግ ክቡር ሚኒስትር? ወድጄ አይደለም እኮ።
 • ለምን?
 • ነገሩ እንዴት ሊሳካ እንደሚችል ባወጣ ባወርድ ሊመጣልኝ አልቻለም።
 • አትጠራጠር ይሳካል፡፡
 • መቼም በጉልበት ለመንጠቅ አንሞክርም አይደል?
 • ምን?
 • የጎረቤቶቻችንን ወደብ?
 • መንግሥትን የሠፈር ጎረምሳ አድርገህ ነው እንዴ የምታስበው?
 • ኧረ በፍጹም ክቡር ሚኒስትር?
 • እና…?
 • ግራ ግብት ቢለኝ ነው።
 • ለምን ግራ ይገባሃል?
 • በኃይል ካልሆነ እንዴት የባህር በር ልናገኝ እንችላለን? ለዚያውም ቀይ ባህርን? አስቸጋሪ ነው።
 • ለምን አስቸጋሪ ይሆናል ብለህ አሰብክ?
 • ኃያላኑ አገሮች አሜሪካን ጨምሮ ትኩረታቸው ቀይ ባህር ላይ ነው ብዬ ነዋ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ቢሆንስ?
 • እዚህ አካባቢ የሚፈጠር ግጭትን ፈጽሞ እንደማይታገሱ በይፋ እየተናገሩ እኮ ነው፡፡
 • እኛም የወደብና የባህር በር ባለቤት ለመሆን ብለን ወደ ቀይ ባህር የመሄድ ፍላጎት የለንም።
 • ዕቅዳችን በህንድ ውቅያኖስ በኩል ነው እንዴ?
 • አይደለም፣ በቀይ ባህር በኩል ነው።
 • ታዲያ ዕቅዱ እንዴት ነው የሚሳካው?
 • ይሳካል፡፡
 • እንዴት?
 • ቀይ ባህርን እናመጣዋለን።
 • ምን? 
 • አዎ፣ ወደ ቀይ ባህር ሳንሄድ ቀይ ባህርን እናመጣዋለን። 
 • እንዴት?
 • ቦይ ቆፍረን።
 • እ…?
 • አዎ፣ ቀይ ባህር ከድንበራችን ያለው ርቀት 54 ኪሎ ሜትር ብቻ እንደሆነ አታውቅም?
 • እሱማ ከዚያም ያነሰ ርቀት ያለው የድንበር አካባቢ መኖሩን አውቃለሁ። 
 • ስለዚህ ቦይ ቆፍረን እናመጣዋለን።
 • ይቻላል?
 • አዎ፣ ባህሩ እኮ ዓለም አቀፍ የውኃ አካል ነው።
 • መሬቱስ?
 • የቱ መሬት?
 • ቦዩን የምንቆፍርበት?
 • እሱማ የጎረቤት አገር ግዛት ነው። 
 • ታዲያ ይፈቅዱልናል?
 • ምን ለማድረግ?
 • መሬቱን ለማምጣት።
 • ምን ያደርግልናል?
 • ቦይ መቆፈር መሬቱን ማምጣት አይደለም እንዴ?
 • አፈሩን መውሰድ ይችላሉ።
 • እ…?
 • አዎ፣ እኛ የምንፈልገው አፈሩን አይደለም።
 • እ…?
 • ቀይ ባህርን ነው።
 • አሃ… ስለዚህ ስለባህር ወደብ ባለቤትነት መወያየት እንድንጀምር ነዋ የተፈለገው?
 • ማለት?
 • ዕቅዱ በቅርብ ጊዜ የሚፈጸም አልመሰለኝም። 
 • በመጀመሪያ ስለዕቅዱ በሰፊው መወያየትና ጉዳዩን የብሔራዊ ጥቅማችን ወሳኝ አጀንዳ ማድረግ ይኖርብናል።
 • ከዚያስ?
 • ከዚያ በኋላ ደግሞ እንዴት ተግባራዊ ሊሆን ይችላል በሚለው ላይ ሰፊ ውይይት ማድረግ ይኖርብናል። 
 • እንደገና ውይይት?
 • የግድ ያስፈልጋል።
 • ከዚያስ?
 • በመቀጠል ደግሞ እንዴት እንጀምረው በሚለው ላይ እንወያያለን። 
 • ውይይቶቹን አንድ ላይ ማድረግ አይቻልም?
 • አይቻልም፣ ምክንያቱም አጀንዳዎቹ የተለያዩና ጥልቀት ያለው ውይይት የሚፈልጉ ናቸው። 
 • እሺ ከዚያስ?
 • ከዚያ እንጀምረውና…
 • እ…?
 • መጪው ትውልድ ያጠናቅቀዋል!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...

የጋራ ድላችን!

ከፒያሳ ወደ ቄራ ልንጓዝ ነው። ለበርካታ ደቂቃዎች ሠልፍ ይዘን...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ ነው የሚደንቀው? የልደታ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ሕዝባዊ ውይይት ላይ ምን ጉዳዮች ተነሱ? በአስማት ነው የምንኖረው ሲሉ ቅሬታቸውን...

[ክቡር ሚኒስትሩ የካቤኔ አባል የሆኑት አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያዳመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል አግኝቼ ላነጋግርዎት የፈለግኩት። ጥሩ አደረክ። ምን አሳሳቢ ነገር ገጥሞህ ነው? ክቡር ሚኒስትር ተወያይተንና ተግባብተን ያስቀመጥናቸው አቅጣጫዎች፣ በተለይም...

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት ሞባይል ስልካቸው ላይ አተኩረው ሲመለከቱ ቆይተው፣ በድንገት ካቀረቀሩበት ቀና ብለው ባቤታቸውን ጠየቁ]

ምን ጉድ ነው የማየው? ምን ገጠመሽ? የመንግሥት ሚዲያዎች የሚያሠራጩት ምንድነው? ምን አሠራጩ? አልሰማህም? አልሰማሁም፣ ምንድነው? ዳግማዊ አፄ ምኒልክ መልዕከት አስተላለፉ እያሉ ነው እኮ። እ... እሱን ነው እንዴ? አዎ። የምታውቀው ነገር አለ? አዎ። የዓድዋ...