Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምበውጭ ዕርዳታ እጥረት ወታደራዊ እንቅስቃሴዋን ለመቀነስ የተገደደችው ዩክሬን

በውጭ ዕርዳታ እጥረት ወታደራዊ እንቅስቃሴዋን ለመቀነስ የተገደደችው ዩክሬን

ቀን:

በሩሲያና በዩክሬን መካከል በየካቲት 2014 ዓ.ም. የተጀመረው ጦርነት፣ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ያላገገመውን የዓለም ኢኮኖሚ ጎድቶታል፡፡ በሩሲያና በዩክሬን በኩል ደግሞ በአጠቃላይ 500,000 ያህል ወታደሮች ሞት ወይም ጉዳት እንዲደርስባቸው ምንያት ሆኗል፡፡

ሁለት ዓመታት ሲሞላው የሁለት ወራት ያህል ዕድሜ በቀረው ጦርነት፣ ከወታደርና ንፁኃን ሞት ባለፈ፣ በተለይ የዩክሬን መሠረተ ልማቶች ወድመዋል፣ ዜጎቿም ተሰደዋል፡፡

በውጭ ዕርዳታ እጥረት ወታደራዊ እንቅስቃሴዋን ለመቀነስ የተገደደችው ዩክሬን | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
ዩክሬንና ሩሲያ በገቡበት ጦርነት ዩክሬን የ108 ቢሊዮን ዶላር መሠረተ ልማት ወድሞባታል

በአገራቱ መካከል ተኩስ አቁም እንዲደረግ የተሞከሩ ጥረቶችም አልተሳኩም፡፡ በምዕራባውያኑ ድጋፍ ጦርነትን ከሩሲያ የገጠመችው ዩከሬን ለዜጎቿም ዕፎይታ፣ ለመሬቷም ዋስትና አላገኘችም፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በእስራኤልና በሐማስ መካከል ከሁለት ወራት በፊት ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ፣ በዓለም አቀፍ መገናኛ ተቋማት እምብዛም ቀዳሚ አጀንዳ ያልሆነችው ዩክሬን፣ ዛሬ ላይ ‹‹ከውጭ የሚደረግልኝ የመሣሪያ ድጋፍ በመቀነሱ ወታደራዊ እንቅስቃሴዬን ለመቀነስ ተገድጃለሁ፤›› ስትል አስታውቃለች፡፡

እንደ ቢቢሲ፣ ዩክሬን ከሩሲያ ጋር በገባችበት ጦርነት ከምዕራባውያኑ ወታዳራዊ ቁሳቁስን ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎች ማግኘቷ፣ ሩሲያን ተቋቁማ እንድትዘልቅ አስችሏት የነበረ ቢሆንም፣ አሁን በይፋ የመሣሪያ እጥረት እንደገጠማትና ወታደራዊ እንቅስቃሴዋን እንደቀነሰች ገልጻለች፡፡

የዩክሬን ከፍተኛ ጄኔራል ኦሌክሳንደር ታርናቪስኪ እንዳሉትም፣ በሁሉም ግንባሮች የሚገኙ ወታደሮቻቸው የመሣሪያ እጥረት ገጥሟቸዋል፡፡ ይህም ለኬቭ መንግሥት ከፍተኛ ችግር ፈጥሯል፡፡

አሜሪካና የአውሮፓ ኅብረት ለዩክሬን የሚለግሱትን በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር በፖለቲካ አለመግባባት ምክንያት ማገዳቸውን ተከትሎ ችግር ውስጥ መግባቷን ያስታወቀችው ዩክሬን፣ የራሷን የጦር መሣሪያ ኢንዱስትሪ ለማጠናከር የምዕራባውያኑን ዕርዳታ ተስፋ ማድረጓንም ገልጻለች፡፡

በአብዛኛው ከምዕራባውያን በሚቀርቡላት የጦር መሣሪያዎች ተመርኩዛ ከሩሲያ ጦርነት የገባችው ዩክሬን፣ በተለይ የረዥም ርቀት ተወንጫፊ ሚሳይልና የአየር መቃወሚያ ቴክኖሎጂን ከእነሱው ታስገባ ነበር፡፡

ጄኔራል ታርናቪስኪ ለሮይተርስ እንደገለጹት፣ ዩክሬን የተተኳሽ ጥይት እጥረት የገጠማት ሲሆን፣ በተለይ በሶቪየት ኅብረት ዘመን ለተሠሩ መሣሪያዎች የሚሆን ተተኳሽ አጥታለች፡፡

ዩክሬን ከሚያስፈልጋት የጦር መሣሪያ ሲነፃፀር፣ በቂ ያልሆነ ተተኳሽ በእጇ እንደቀረና የቀረውንም እያከፋፈሉ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ከውጭ የወታደራዊ ቁሳቁስ ዕርዳታ መቀነስ ተፅዕኖው እየታየ በመሆኑ፣ በአንዳንድ ቦታዎች ራሳቸውን ለመከላከል ብቻ እንደተገደዱ የገለጹት ጄኔራሉ፣ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ደግሞ እያጠቁ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በተያዘው ወር መጀመሪያ በአሜሪካ ኮንግረስ ሪፐብሊካኑ ለዩክሬን ሊሰጥ የነበረውን የ60 ቢሊዮን ዶላር ወታደራዊ ዕርዳታ ማገዳቸውን ተከትሎ፣ የአውሮፓ ኅብረትም 55 ቢሊዮን ዶላር ወታደራዊ ድጋፉን ማገዱን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

የአውሮፓ ኅብረት ኃላፊዎች ‹‹ዩክሬን ያለ ድጋፍ አትቀርም›› የሚል ማፅናኛ ሰጥቶ፣ ኅብረቱ እ.ኤ.አ. በመጋቢት 2024 ለዩክሬን ተተኳሽ ጥይት እንደሚልክ ቃል ገብቷል፡፡

ዩክሬን በምዕራባውያኑ ለተሠሩ መሣሪያዎች የሚያገለግል ተተኳሾች ከአሜሪካ ብታገኝም፣ በየወሩ 200 ሺሕ ተተኳሾች እንደሚያስፈልጋት የኢስቶኒያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ዩክሬን የዘመኑ መሣሪያዎችን ለማምረት ከበርካታ የአሜሪካ መሣሪያ አምራች ድርጅቶች ጋር ስምምነት ፈጽማለች፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ከሩሲያ ጋር በሀብትም ሆነ በሰው ኃይል የማትመጣጠን በመሆኗ፣ የቴክኖሎጂ የበላይነት ለመቆናጠጥ ነው፡፡

ቀድሞውንም ጤናማ ያልነበረውን የምዕራባውኑና የሩሲያ ግንኙነት ያሻከረው የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት፣ ለዓለም ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮችን አስከትሏል፡፡

በዓለም 30 በመቶ የሚሆነውን ስንዴ የሚያመርቱት ሩሲያና ዩክሬን ናቸው፡፡ ሁለቱም አገሮች በዓለም የምግብ ገበያ ዋና ሚና ያላቸው ሲሆን፣ በተለይ ለአብዛኛው የዓለም ሕዝብ ወሳኝ ምግብ የሆኑትን ስንዴ፣ በቆሎ፣ ገብስ እንዲሁም በዓለም በአብዛኛው ሕዝብ ጥቅም ላይ የሚውለውን የሱፍ ዘይት በማምረትና በመላክ የዓለምን የምግብ ኢኮኖሚ የሚደግፉ ናቸው፡፡

የዓለምን 30 በመቶ የስንዴ ምርት የሚያቀርቡት ሩሲያና ዩክሬን ጦርነት በገቡ ማግሥት ነበር ዓለም በምግብ ዋጋ ንረት የተመታው፡፡ ከዚህ ባለፈ በድርቅ የተጎዱ የዓለም ሕዝቦች ይበልጥ ለችግር እንዲጋለጡ አድርጓል፡፡ ሆኖም ለዩክሬን በወገኑት በምዕራባውያኑ ዘንድም ሆነ በሩሲያ በኩል ጦርነትን የማቆም ኮቴ አልተሰማም፡፡

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲንም ‹‹ጦርነቱ የሚቆመው ሩሲያ ግቧን ስትመታ ብቻ ነው፤›› ሲሉ የተናገሩት ባለፈው ሳምንት ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...