Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናአገራዊ ጉዳዮችን በአዎንታዊ አስተሳሰብ ለመፍታት መንግሥት የውይይት መድረኮችን መፍጠር እንዳለበት ተጠቆመ

አገራዊ ጉዳዮችን በአዎንታዊ አስተሳሰብ ለመፍታት መንግሥት የውይይት መድረኮችን መፍጠር እንዳለበት ተጠቆመ

ቀን:

ኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮችን በአዎንታዊ አስተሳሰብ እንድትፈታ፣ መንግሥት ከአገራዊ ምክክር በተጨማሪ ሌላ የውይይት መድረኮችን መፍጠር እንዳለበት፣ ‹‹አዎንታዊ አስተሳሰብ ለኢትዮጵያ ማኅበር›› አስታወቀ፡፡

አዎንታዊ አስተሳሰብ ለኢትዮጵያ ማኅበር ይህንን የገለጸው ማክሰኞ ታኅሳስ 9 ቀን 2016 ዓ.ም. የመጀመሪያ የምሥረታ ጉባዔውን ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡

አዎንታዊ አስተሳሰብ ለኢትዮጵያ ማኅበር (Positive Thinking For Ethiopia Association) በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሠረት መስከረም 21 ቀን 2016 ዓ.ም. ተመዝግቦ ሕጋዊ ፈቃድ ያገኘና 22 አባላቶች አሉት ማኅበር ነው፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የማኅበሩ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ በቀለ ፀጋዬ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የአዎንታዊ አስተሳሰብ ፅንሰ ሐሳብ በማኅበረሰብ ውስጥ ሰርፆ እንዲገባና ችግሮችን በውይይት መፍታት እንዲቻል የሚሠራ ማኅበር ነው፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ አዎንታዊ አስተሰሰብ ጉድለት ያሉባቸው ዜጎች ቁጥር ቀላል የሚባሉ እንዳልሆነ የገለጹት የማኅበሩ ቦርድ ሰብሳቢ፣ ይህም ከግለሰብ እከስ አገር ጉዳይ የሚፈጠሩ የሐሳብ ልዩነቶችን ለመቅረፍ አዳጋች መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በተለይ በውጭ አገር ሆነው ተምረናል የሚሉ ኢትዮጵያውያን ‹‹የትጥቅ ትግል የተሻለ ውጤት ያመጣል›› የሚል የራሳቸውን ሐሳብ ይዘው ታጣቂዎችን በገንዘብ፣ በሞራልና በማኅበራዊ ሚዲያ የፕሮፓጋንዳ ሽፋን የሚደግፉ መኖራቸውን ገልጸዋል፡፡

በዚህ መሠረት ማኅረበሰቡ የአዎንታዊ አስተሳሰብ አንዱ የሆነውን አካሄድ፣ ማለትም ያለውን ሁኔታ መቀበልና ራስን ከዚህ ጋር በማስማማት በቀጣይ በዕውቀት፣ እንዲሁም በመረጃ ላይ ተመርኩዞ በአዎንታዊ አስተሳሰብ ድባብ ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ተጨማሪ ለውጦችን ለማምጣት መለማመድ ተገቢ ነው ብሎ ማኅበሩ ያምናል፡፡

በተመሳሳይ የአዎንታዊን አስተሳሰብ ፅንሰ ሐሳብ በኅብረተሰቡ በማስረፅ፣ በማኅበረሰቡ ውስጥ የሚገኝ ዕምቅ ኃይል፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ችግር መፍቻነት መጠቀም እንደሚያስፈልግ አቶ በቀለ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

መንግሥት አዎንታዊ አስተሳሰብን በተመለከተ የውይይት መድረኮችን መፍጠር ከቻለ፣ የትኛውም ሰው በፖለቲካዊ ሐሳብ ልዩነት ሊታሰር፣ ሊገደል፣ ወይም ጦርነት ውስጥ ሊገባ እንደማይችል የማኅበሩ አባላቶች ገልጸዋል፡፡

አዎንታዊ አስተሳሰብ ለኢትዮጵያ ማኅበር የተቋቋመበት ዋና ዓላማ አሉታዊ አስተሳሰቦችን ለማቀጨጭና አዎንታዊ አስተሳሰቦችን ለማበልፀግ ሲሆን፣ አዎንታዊ አስተሳሰብን በኅብረተሰቡ ውስጥ ከማስረፅ በተጨማሪ ዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ለማገዝ የውይይትና ድርድር መድረኮችን ማመቻቸት፣ እንዲሁም በልማት ዙሪያ ምክረ ሐሳቦችን መስጠት የማኅበሩ አንድ አካል መሆኑን አባላቶቹ ጠቁመዋል፡፡

በሌላ በኩል በአብዛኛው ከውጭ የሚሠራጩ አሉታዊነት ያላቸው፣ ሕዝብን የሚከፋፍሉ የጥላቻና የሐሰት ፕሮፓጋንዳዎች፣ አገርን አደጋ ላይ የሚጥሉና ለውጭ ጣልቃ ገብነት ጭምር የሚያጋልጡ መሆኑን በማመን መንግሥት የተሻለ አሠራርን መዘርጋት ይኖርበታል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ አንዳንድ ምዕራባውያን አገሮች የኢትዮጵያን ታሪክና አገሪቱ ከያዘችው ሥፍራ ጋር በተገናኘ በጂኦ ፖለቲካ ምክንያት ራሷን የቻለች ጠንካራና ተፅዕኖ ፈጣሪ አገር እንዳይኖር ተግተው እየሠሩ ነው የሚሉት አባላቶቹ፣ ይህንን ኃይል መቋቋም የምንችው ውስጣዊ ችግሮቻችንን በመፍታትና አንድነታችንን በማስረፅ መሆን አለበት ብለው ተናግረዋል፡፡

የአሉታዊ አስተሳሰብ ከሚጎሉት ውስጥ ደኅነትና ሥራ አጥነት፣ ያልተመቻቸ የሥራ ሁኔታዎችና የመሳሰሉት እንደሆኑ ማኅበሩ የሚያምን ሲሆን፣ እነዚህንም ችግሮች ለመቅረፍ በአዎንታዊ አስተሳሰብ ዓውድ ውስጥ የመተሳሰብና የመተጋገዝ እሴቶችን በመጠቀም የተሻለ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ አካላትን በችግር ውስጥ የሚኖሩ ዜጎችን እንዲደግፉ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፡፡     

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...