Sunday, March 3, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ኢትዮጵያና ሩሲያ በራሳቸው ገንዘብ ለመገበያየት የሚያስችላቸውን ምክክር መጀመራቸው ተነገረ

ተዛማጅ ፅሁፎች

በቅርቡ ብሪክስ የሚባለውን ስብስብ የምትቀላቀለው ኢትዮጵያና የሩሲያ ፌዴሬሽን፣ በራሳቸው ገንዘብ ለመገበያየት የሚያስችል ምክክር መጀመራቸው ተገለጸ፡፡

የሩሲያ ፌዴሬሽን የማዕድን ሀብት ልማት ኤጀንሲ ኃላፊ ፔትሮቪ ኢቬንጊ፣ የሁለቱ አገሮች ብሔራዊ ባንኮች በምክክሩ መግባባት ላይ ሲደርሱ የመጨረሻ ውሳኔያቸውን ይፋ ያደርጋሉ ብለዋል፡፡

ኃላፊው አክለውም የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ የኢትዮጵያ ባንኮች ከሩሲያ ባንኮች ጋር የመረጃ ልውውጥ የሚያደርጉበት ሥርዓት እንደሚዘረጋ አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮ-ሩሲያ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽንና ቢዝነስ ፎረም ከታኅሳስ 9 እስከ 10 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ለሁለት ቀናት እየተካሄደ ሲሆን፣ የሁለቱ አገሮች የመንግሥት ኃላፊዎችና የንግድ ማኅበረሰቦች እየተሳተፉ ነው፡፡

እ.ኤ.አ. ከ2024 ጀምሮ በኢትዮጵያ በነዳጅ ማዕድን ፍለጋና ማውጣት ለመሰማራት፣ ከሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ጋር ምክክር እንደሚደረግ ሚስተር ኢቬንጊ ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከሩሲያው የላዳ አምራች ኩባንያ ጋር፣ የላዳ ተሽከርካሪዎችን ኢትዮጵያ ውስጥ ለማምረት የሚያስችለውን የመጀመሪያ የፍላጎት ስምምነት መግለጫ ፊርማ ተፈራርሟል፡፡

የላዳ ኩባንያ የውጭ ገበያ ዳይሬክተርና የሽያጭና ገበያ ማፈላለግ ምክትል ዳይሬክተር ኢሊያ ሳቪኖቪ፣ ከኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሱሌማን ደደፎ (አምባሳደር) ጋር ስምምነት አድርገዋል፡፡

በስምምነቱ መሠረት የላዳ ተሽከርካሪዎች የመገጣጠም ሥራ በመጪዎቹ ጥቂት ወራት ለማስጀመር ቦታ መለየቱን፣ ቢያንስ ሁለት ሞዴሎችን የማምረት ዕቅድ እንዳለ ሱሌማን (አምባሳደር) ተናግረዋል፡፡

በጊዜ ሒደት ከመገጣጠም አልፎ ሙሉ በሙሉ በአገር ውስጥ ለማምረት የሚያስችል አቅም በመፍጠር፣ ለጎረቤት አገሮችም ለመላክ ይቻላል ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች