Sunday, March 3, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊለአገር ሰው የተሰናዳው ‹‹የኛ ምርት››

ለአገር ሰው የተሰናዳው ‹‹የኛ ምርት››

ቀን:

በኢትዮጵያ በተለያዩ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶች ለአገር ውስጥ የሚያቀርቧቸው ዕቃዎች ላይ የጥራት ችግር አለ የሚል ዕሳቤ በመኖሩ ምርቶቻቸውን በአገር ውስጥ ለመሸጥ ይቸገራሉ፡፡

በዋጋ ውድነታቸውም ሆነ በገበያ ትስስር እጥረት ምክንያት ምርቶቻቸውን በልፋታቸው ልክ መሸጥ ያልቻሉትን ኢንዱስትሪዎች ለመደገፍ መንግሥት ተደጋጋሚ ጥረቶችንና ማበረታቻዎችን አድርጓል፡፡

የአገር ውስጥ ምርት በአገር ገበያ ይሸጥ ዘንድም በተለያዩ መድረኮች ግንዛቤ ሲፈጠር ቆይቷል፡፡ ሆኖም የኅብረተሰቡ አመለካከት እምብዛም አልተቀየረም፡፡ በተለይ ከተሜው አልባሳቱንም ሆነ መጫሚያውን፣ ብሎም የቤት ውስጥ ቁሳቁሱን ከአገር አገር አማርጦ፣ መለያ (ብራንድ) ዓይቶ የሚሸምት መሆኑን መታዘብ ይቻላል፡፡ ኢትዮጵያም በብዛት ከውጭ በሚገቡ ምርቶች የተጥለቀለቀች ናት፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ኢትዮጵያውያን በአገር ውስጥ ምርት ይጠቀሙ ዘንድና የዘርፉን ኢንዱስትሪዎች ለማበረታታት ከሚሠሩ ሥራዎች አንዱ ምርቶችና አገልግሎቶችን በተለያዩ መንገዶች ማስተዋወቅ ነው፡፡ ከታኅሳስ 3 እስከ 7 ቀን 2016 ዓ.ም. በስካይ ላይት ሆቴል የተከናወነው ‹‹የኛ ምርት›› የአምራች ኢንተርፕራይዞች አገር አቀፍ ኤግዚቢሽንና ባዛርም የዚሁ አካል ነው፡፡  

‹‹የአገር ውስጥ ምርት በዚህ ልክ በጥራት ይመረታል ብዬ አስቤ አላውቅም፤›› ሲሉ በዓውደ ርዕዩ ያገኘናቸው ሻምበል በየነ (ዶ/ር) ይናገራሉ፡፡

ለአገር ውስጥ ምርት የነበራቸው ዝቅተኛ አመለካከት ከፍ እንዲል ያደረገው ደግሞ፣ ‹‹የኛ ምርት›› ኤግዚቢሽንና ባዛር ላይ ተገኝተው ያደረጉት ምልከታ ነበር፡፡

ከጓደኞቻቸው ጋር በመሆን በባዛሩ የቀረቡ ምርቶችን ለመመልከት እንደመጡ የሚናገሩት ሻምበል (ዶ/ር)፣ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚፈልጉትን ዕቃ መግዛታቸውንና በቀጣይም ምርቶቹን ባሉበት አካባቢ በመሄድ ለመግዛትና ለሌሎችም ለመጠቆም መነሳሳታቸውን ተናግረዋል፡፡

የአገር ውስጥ ምርቶች በስፋትና በጥራት እንዲመረቱ ማበረታታት፣ የውጭ ምንዛሪን ከማስቀረት ባሻገር ራስን ሆኖ ለመገኘት ያግዛል፣ በተቃራኒው ሲታይ ደግሞ እንደ ትልቅ ኪሳራ ይቆጠራል ሲሉ ሻምበል (ዶ/ር) ይናገራሉ፡፡

ለአብነትም የህንድ ዜጎችን የጠቀሱት አስተያየት ሰጪው፣ ‹‹የህንድ ዜጎች ለሥራ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ከጫማቸው ጀምሮ የሚለብሱት ልብስ በአገራቸው የተመረተና የአገራቸውን ባህል የሚያንፀባርቅ ነው፤›› ይላሉ፡፡

በዓውደ ርዕዩ በርካታ አምራች ኢንተርፕራይዞች ያመረቷቸውን ምርቶች ለዕይታና ለሽያጭ ያቀረቡ ሲሆን፣ በግብይቱ ወቅትም ተጠቃሚዎች የተለያዩ አስተያየቶችን ሰጥተዋል፡፡ የአገር ውስጥ ምርት መጠቀም ለኢኮኖሚ ዕድገትም ሆነ ባህልን ጠብቆ ለማቆየት ከሁሉም የተሻለ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል ምርቶቹ አገር ውስጥ ተመርተው ሳለ፣ ነገር ግን ዋጋቸው ተመጣጣኝ እንዳልሆነላቸው አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎቹ ገልጸዋል፡፡

አምራች ኢንተርፕራይዞች በበኩላቸው፣ ከመሠረተ ልማቶች፣ ከውኃና ከመብራት ጀምሮ የውጭ ምንዛሪ እጥረትና የቦታ ጥበት በሥራቸው ላይ ፈተና እንደሆነባቸው ገልጸው፣ በኤግዚቢሽኑና በባዛሩ ላይ ደግሞ ብዙ ደንበኞችን ማፍራት እንደቻሉና ምርታቸውም በብዙዎች ዘንድ እንደተወደደላቸው ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

አቶ ካሳሁን እሸቱ ከአዳማ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ የተለያዩ ልብሶችን በኤክስፖው ላይ ይዘው ተገኝተዋል፡፡ ባዛሩ ብዙ ደንበኞች የሚገኙበትና የሚታደሙበት ከመሆኑም በላይ፣ ሰፊ የገበያ ትስስር እንደሚፈጥር አቶ ካሳሁን ይናገራሉ፡፡

የአገር ውስጥ ምርት ሲባል ብዙ ጊዜ የጥራትና የተደራሽነት አቅም እንደሌለ የሚወስዱ ሰዎች እንዳሉም ገልጸዋል፡፡ የደንበኞችን ጥያቄ ለመመለስ ባዛሩ የበለጠ ማስረዳት እንደሚችል የሚናገሩት አቶ ካሳሁን፣ ከዚህ ባለፈ አምራች ኢንዱስትሪዎችም እርስ በርስ ለመተዋወቅና ከግብዓት አቅራቢዎች ጋር ትስስር ለመፍጠር እንደረዳቸው አክለዋል፡፡

መንግሥት ለአገር ውስጥ አምራቾች ቅድሚያ ሰጥቶ ቢሠራና አምራች ኢንዱስሪዎች ጥራት ላይ በርትተው ከሠሩ ለአገር ውስጥ ገበያ ተጽእኖ እያሳደረ ያለው የውጭ ምርት የማይቆምበት ምክንያት የለም ሲሉ ያብራራሉ፡፡

የአምራች ኢንዱስትሪዎች ችግር የሚፈታው፣ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ኢንዱስትሪው ለአገር ኢኮኖሚ ዕድገትና ለሕዝብ ጥቅም የሚያበረክተውን ፋይዳ ተረድተውና ተቀራርበው ሲረዳዱ ነው የሚሉት የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር አለባቸው ንጉሤ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

ለማምረት እንቅፋት የሆኑ ችግሮች መወገድ አለባቸው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ማምረት ብቻ በቂ አለመሆኑን፣ የተመረቱ ምርቶች ተጠቃሚ ሊኖራቸው እንደሚገባም ያክላሉ፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...