Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልየዕርስ በርስ ጦርነት ተቃውሞ በ‹‹ሸማ›› የሥዕል ዓውደ ርዕይ

የዕርስ በርስ ጦርነት ተቃውሞ በ‹‹ሸማ›› የሥዕል ዓውደ ርዕይ

ቀን:

‹‹ሸማ ሸማ ሆኖ  ከመሠራቱ በፊት ትንሽ የጥጥ ፍሬ ነበር፡፡ ይህ የጥጥ ፍሬ ወደ ጥጥነት ተቀይሮ፣ ተፈትሎና ተደውሮ እንዲሁም ተሸምኖ የሰው ልጆችን ገመና ሸፍኗል፡፡ በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ ገመና በአደባባይ ታይቷል፣ ገመናዋም በዝቷል ብዬ አስባለሁ፡፡ ይህንን የተገላለጠ ገመናዋን የሚሸፍን ትውልድ ያስፈልጋታል››፡፡

የዕርስ በርስ ጦርነት ተቃውሞ በ‹‹ሸማ›› የሥዕል ዓውደ ርዕይ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

ይህንን የተናገረው ሠዓሊ በረከት አንዳርጌ፣ የኢትዮጵያን የፈጠጠ ገመና የሚሸፍነው በዋናነት የኪነ ጥበቡ ሰው እንደሆነ ያክላል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

‹‹ሸማ›› የተሰኘ የሥዕል ዓውደ ርዕይ በሳፋየር አዲስ ሆቴል ለዕይታ ባቀረበበት ወቅትም፣ የሥዕል ኤግዚቢሽኑ ለ64ኛ ጊዜ የቀረበ መሆኑንና በዓውደ ርዕዩም 35 ሥዕሎች መቅረባቸውን ተናግሯል፡፡

ከሥዕል ሥራዎቹ 26 የሚሆኑት በጥቁርና ነጭ ቀለም የተሠሩ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ ደግሞ በተለያየ ቀለም የተሠሩ ናቸው፡፡ በብዛት የእርስ በርስ ጦርነትን የሚቃወሙ ሥዕሎች የቀረቡበት የሥዕል ዓውደ ርዕይ፣ በተከፈተ በመጀመሪያዎቹ  ሁለት ቀናት ውስጥ 4,600 ሰዎች ጎብኝተውታል፡፡

‹‹የጦር መሣሪያዎች የሰው ልጅን ከሚያጠፉ ራሳቸውን ቢያጠፉ እንዲሁም ገዳይ የሆኑ ክላሾችና ሞርታሮች ጥይቶችን ከሚተፉ ሰላምን ቢረጩ›› የሚለው ሐሳብ ምርጫ የሌለው ምርጫ እንደሆነ በጥበብ ሥራዎቹ አንፀባርቋል፡፡

ከሥዕሎች ውስጥ ቀጥ ብሎ የቆመ ክላሽ ጫፉ ላይ ታጥፎ ጥይቶችን ወደ ራሱ ሲተኩስ ይታያል፡፡ ስለዚህ ሥዕል ሠዓሊው ሲያብራራ፣ ‹‹እኔ ሰው ሲጠፋ ከማይ ክላሽ ራሱን ሲያጠፋ ባይ ደስ ይለኛል፣ ይህ ደግሞ ጦርነትን እየተቃወምኩበት ያለው ጥበቤ ነው፤›› ይላል፡፡

‹‹ኢትዮጵያ ሰላምና ፍቅር ሆና ማየት ምኞቴ ነው፤›› የሚለው ሠዓሊ በረከት፣ የሚተኮሱት ጥይቶች እሳት ሳይሆን እንደ ርችት ፍቅር፣ ሰላምና ደስታ እንዲረጩ ምኞቱ መሆኑን ገልጿል፡፡

የዕርስ በርስ ጦርነት ተቃውሞ በ‹‹ሸማ›› የሥዕል ዓውደ ርዕይ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

አንድ አገር መከላከያ ኢትዮጵያን ሊወጋ የመጣ ጠላትን ሲከለከል ማየት እንጂ፣ በእርስ በርስ ጦርነት ስንጋደል ማየት ከባድ እንደሆነ፣ ሥራዎቹም ወደ ቀድሞው አንድነትና መተሳሰብ እንድንመለስ የሚል መልዕክት እንዳላቸው ሠዓሊው አብራርቷል፡፡

የዕርስ በርስ ጦርነት ተቃውሞ በ‹‹ሸማ›› የሥዕል ዓውደ ርዕይ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

በሌላ በኩል ከሥዕሎቹ እናቶችና እህቶች ከታሰሩበት የተለያዩ የባህል ውጥንቅጥ ይወጡ ዘንድ እንታደጋቸው የሚል አንድምታ ያላቸው አሉ፡፡

እንደ ሠዓሊው፣ ሥዕሎቹ ስለሴተኛ አዳሪዎች የተሠሩ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ሴትነት እየረከሰና እየወደቀ ነው፡፡ በብዙ ችግርና መከራ ውስጥ ሆነው ላሳደጉን እናቶቻችን አሁንም ልንደርስ አልቻልንም ይላል፡፡

የሴተኛ አዳሪዎች ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ በመምጣቱ፣ በሴቶች ላይ እያደረሰ ያለውን ተፅዕኖ ማስወገድ ይገባል የሚል ሐሳብም አለው፡፡

በጦርነት የፈረሱ ከተሞችን ስለሚያሳይ ሥዕል ገለጻ ያደረገው ሠዓሊ በረከት፣ ‹‹በእነዚህ በፈረሱ ከተሞች ውስጥ መልካም ፍቅሮች ነበሩ፣ አንድነትና መዋደዶች ነበሩ፣ ደረቅ እንጀራ ይዘው ከጎረቤት ወጥ ጨምረው በጋራ የሚበሉ ሰዎች ነበሩ፣ አሁን ግን ፈርሰዋል፣ የሉም፣ መረዳዳትና መተጋገዞች ጠፍተዋል፡፡ አብሮ የመብላትና የመጠጣት እሴት ተሸርሽሯል ብሏል፡፡

እነዚህና በርካታ የታጨቁ ሐሳቦችን በአንድነት የያዙ መልዕክቶች ባተላለፈበት ዓውደ ርዕይ፣ ከ17 በላይ አምባሳደሮች ተገኝተው እንደነበር ሠዓሊ በረከት ተናግሯል፡፡

ዓውደ ርዕዩ በቀጣይ አሜሪካ ችሊ ውስጥ ለዕይታ የሚበቃ ሲሆን፣ የችሊ አርቲስቶች ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ሠዓሊው ተናግሯል፡፡

ከኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ለተከታታይ ሰባት ቀናት በተዘጋጀው ዓውደ ርዕይ መዝጊያ ፕሮግራምም፣ በሸማ አልባሳት ብቻ የተዘጋጀ ፋሽን ሾው የቀረበበት ነበር፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...