Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየሰብዓዊ ዕርዳታን ከለጋሽ አካላት ጥገኝነት ለማላቀቅ የሚያስችል ጥናት መጀመሩን ኮሚሽኑ አስታወቀ

የሰብዓዊ ዕርዳታን ከለጋሽ አካላት ጥገኝነት ለማላቀቅ የሚያስችል ጥናት መጀመሩን ኮሚሽኑ አስታወቀ

ቀን:

  • ከዕርዳታ ማጭበርበር ጋር በተገናኘ በ375 ዜጎች ላይ ምርመራ መጀመሩ ተገልጿል

የአደጋ ሥጋት አመራርን ከለጋሽ አካላት ጥገኝነት ሙሉ ለሙሉ ለማላቀቅ የሚያስችል ጥናት ተዘጋጅቶ ለኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት አመራር ምክር ቤት መቅረቡ ተገለጸ፡፡

የተዘጋጀው ጥናት በምክር ቤቱ ግብዓት ተሰጥቶበት ክልሎች ባሉበት በውይይት እየዳበረ መሆኑን የገለጹት የአደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽነር ሽፈራው ተክለማርያም (አምባሳደር)፣ የጥናት ሰነዱ ለመንግሥት ቀርቦ በሚሰጠው ውሳኔ መሠረት ቀጣይ ዕርምጃዎች እንደሚወሰዱ ተናግረዋል፡፡ ኮሚሽነሩ ይህን የተናገሩት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን፣ የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት ባሄደበት ዕለት ነው፡፡

ሽፈራው (አምባሳደር) በማብራሪያቸው፣ ‹‹የአደጋ ሥጋት አመራር ሥራን እየተፈታተኑ ነው›› ያሏቸውን ጉዳዮች የዘረዘሩ ሲሆን በዚህም የተረጂነትና ተረጂዎች ፍላጎትና ቁጥር መናር፣ ተጨማሪ ምርት አምርቶ ራስን አለመቻልና ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅምና ምርት አለመሸፈን እንዲሁም ለሁለቱ ፍላጎቶች የሚሆን ሀብት በአገር ውስጥ ማሰባሰብ አለመቻል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በቀጣይ የተረጂነት ቤት ለቤት ልየታ በተገቢውና በተሟላ መንገድ ሊሠራ እንደሚገባ ጠቁመው፣ ተረጂን በድጋሚ ከዕርዳታ በሚያስወጣ መንገድ ስሌት ሥራ መሠራቱን ተናግረዋል፡፡

አገሪቱ እያስፈለጋት ያለው የምርት መጠን በመጠባበቂያ ክምችት ደረጃ አምስት ሚሊዮን ኩንታልና በአስቸኳይ የዕለት ደራሽ ላይ 15 ሚሊዮን ኩንታል ብቻ መሆኑን የተናገሩት ኮሚሽነሩ፣ ይህን አጠቃላይ ሁለት ሚሊዮን ኩንታል ለማምረት በፌዴራልና በክልሎች በአንድ ላይ የሚያስፈልገው 250 ሺሕ ሔክታር መሬት ብቻ ነው ብለዋል፡፡

ለዚህም ይረዳ ዘንድ በደቡብ ኦሞ ዳሰነች አካባቢ በስኳር ኮርፖሬሽን እየለማ የነበረና ወደ ተግባር መሸጋገር ያልቻለ 250 ሺሕ ሔክታር መሬት ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡ በቀጣይ ይህን ወደ መሬት በማልማት የሰብዓዊ ዕርዳታን ፍላጎት ማሟላት እንደሚቻል አስረድተዋል፡፡

 ዕሳቤው በአደጋ ሥጋት አመራር ምክር ቤት ቀርቦ ውሳኔ እንደሚሰጥበት ገልጸው፣ ከእርሻ አምርቶ በመጠባበቂያ ክምችት በማስቀመጥ ለገበያ ማረጋጊያ፣ ለውጭ ገበያ፣ አልፎ አልፎ እንደየአስፈላጊነቱ በ‹‹ኢትዮጵያን ኤይድ›› አማካይነት ለተቸገሩ አካላት ለመለገስ የሚያስችል አቅም ማግኘት እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡

በላፈው ዓመት ከአጋሮች ጋር በነበረው የሰብዓዊ ዕርዳታ መቆም የተደረገውን ምክክር ተከትሎ ኮሚሽኑ ላይ በተደረገ ፍተሻ ወደ 375 የሚደርሱ ተጠርጣሪዎች ከየአካባቢው መለየታቸውንና ምርመራ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

የተጠየቁት ተጠርጣሪዎች ተገቢ ባልሆነ መንገድ የሰብዓዊ ድጋፍ ቁሳቁስ ላይ እጃቸው ላይ የታየና የተደረሰባቸው በሒደት ሊረጋገጡ የሚችሉ ናቸው ብለዋል፡፡

ከተጠረጠሩት መካከል ከሥልጣን የተባረሩ፣ ክስ የተመሠረተባቸው መሆራቸውን የገለጹት ኮሚሽነሩ፣ የፍትሕ ሚኒስቴር ከፌዴራል ወንጀል ምርመራ ጋር በመሆን ወደ ዘጠኝ ቡድን ተዋቅሮ አገራዊ የሆነ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽነሩ እንደገለጹት በ2015 ዓ.ም. ወደ 20.1 ሚሊዮን ዜጎች ድጋፍ ይሹ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ በበልግ ወራት በተደረገ ጥናት ቁጥሩ ወደ 15.4 ሚሊዮን መውረዱን ተናግረዋል፡፡

በ2016 ዓ.ም. የቅድሚያ ቅድሚያ ያስፈልጋቸዋል የተባሉት ዜጎች 8.1 ሚሊዮን ሲሆኑ፣ ቁጥሩ የተፈናቀሉትን፣ ድርቅና ጎርፍ የጎዳቸውንና ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ዜጎች ያካትታል፡፡

ኮሚሽነሩ የአጋር አካላት ድንገተኛ ዕርዳታ ማቋረጥ ፈታኝ እንደሆነባቸው ተናግረዋል፡፡

 በቅርቡ የዓለም ምግብ ድርጅትና የአሜሪካ የልማት ተራድኦ አቋርጠውት የነበረውን ድጋፍ ለመመለስ በነበረው ውይይትና ምክክር፣ ዳግም ወደ ሥራ እንዲመለስ ቢደረግም፣ ይህ ውሳኔ ለአንድ ዓመት የሙከራ ጊዜ ብቻ ከመሆኑም በላይ ድጋፉ ከዚህ በፊት ይቀርብ ከነበረው 20 በመቶ በመቀነስ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ስለሆነም ዕርዳታው ወደ ነበረበት ተመልሷል የሚል እሳቤ መወሰድ እንደሌለበት ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽነሩ የተለያዩ መጋዘኖችን እየገነባ መሆኑን የተገለጸ ሲሆን በተለይም የሆሳዕና መጋዘን በ2.5 ቢሊዮን ብር፣ ቀብሪደሃር መጋዘን በ320 ሚሊዮን ብር፣ ፍኖተሰላም መጋዘን በ6.5 ቢሊዮን ብር ግንባታ እየተካሄደላቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንድ የግንባታ ሒደቶች የዋጋ ማስተካከያ እንደተጠየቀባቸው ተናግረዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ኮሚሽኑ በአገሪቱ የሚገኙ ወደ ስምንት የሚደርሱ ያረጁ መጋዘኖችን እድሳት ለማድረግ ወደ አሥር ቢሊዮን ብር የሚጠጋ እንደሚያስፍልገው መዘገባችን ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...