Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊቴክኒክና ሙያ የደካማ ተማሪዎች መሰባሰቢያ ነው የሚለው አስተሳሰብ መቀረፍ አለበት ተባለ

ቴክኒክና ሙያ የደካማ ተማሪዎች መሰባሰቢያ ነው የሚለው አስተሳሰብ መቀረፍ አለበት ተባለ

ቀን:

በኢትዮጵያ እየተሰጠ ያለው የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና 70 በመቶው ተግባር ተኮርና 30 በመቶው በቀለም ሥልጠና ላይ ያተኮረ መሆኑንና የደካማ ተማሪዎች መሰባሰቢያ ነው የሚለው አስተሳሰብ የተሳሳተ መቀረፍ ያለበት መሆኑን የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡ ብሩክ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፣ አገር በቀል የሆኑ ነባር የዕውቀት መሠረቶችን ያማከለ እንዲሆን እየተሠራ መሆኑንና የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ፖሊሲ፣ ስትራቴጂም ሆነ ካሪኩለም ዝግጅትና አተገባበር፣ አገር በቀል ዕውቀቶችን ያቀፈና አገር ወዳድነትንም ያማከለ እንዲሆን እየተሠራ ነው፡፡

ቴክኒክና ሙያ ብሔራዊ ፈንድ እንደሚያስፈልገው፣ እንዲሁም ተገቢውን ክብር ማግኘት እንዳለበት በመጠቆም፣ በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት ደካማ ውጤት ያላቸው ተማሪዎች መሰብሰቢያ ናቸው መባሉ የተሳሳተ አስተሳሰብና መቀረፍ ያለበት አመለካከት እንደሆነና ‹‹የአገር ፍቅር መንፈስ፣ ሥልጠናው በሙያና ሥነ ምግባር መታነፅን፣ እንዲሁም ብሔራዊ አገልግሎት ሰጪነትን ጭምር ያቀፈ›› መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ብሩክ (ዶ/ር) ማብራሪያውን የሰጡት በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ታኅሳስ 3 ቀን 2016 ዓ.ም. በተካሄደው የአገር አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ቲንክ ታንክ ምሥረታ ይፋ ማድረጊያ ሥነ ሥርዓት ላይ ነው፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ብሩክ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍን አጀማመርና ዕድገት በጥልቀት የዳሰሰ ጥናት ያቀረቡ ሲሆን፣ የቆይታውን ያክል ዘርፉ አለማደጉን ገልጸዋል፡፡

ቴክኒክና ሙያ በኢትዮጵያ አጀማመሩ ከመደበኛ ትምህርት ብዙም እንዳልዘገየና እ.ኤ.አ. ከ1920ዎቹ ጀምሮ በሚሽነሪዎች በተከፈቱ ተቋማት አማካይነት መሆኑን ብሩክ (ዶ/ር) አንስተዋል፡፡ ‹‹ይሁን እንጂ ዘርፉ ተገቢውን የማኅበረሰብ ከበሬታ ባለማግኘቱና አስፈላጊውን ድጋፍ በማጣቱ ማደግ በሚጠበቅበት ልክ ሳያድግ ቀርቷል፤›› ብለዋል፡፡

የህንድ ባንዲራ የእንቅስቃሴ ምልክት ሆኖ መሠራቱን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ይህም ህንዶች ለሥራ፣ ለሙያና ለእንቅስቃሴ የሚሰጡትን ግምት የሚያሳይ ስለመሆኑ አንስተዋል፡፡

የቴክኖክና ሙያ መስክ የኢኮኖሚ ዕድገት ሁነኛ መሣሪያ እንዲሁም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ምንጭ ስለመሆኑ ብሩክ (ዶ/ር) ይገልጻሉ፡፡ ‹‹በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ አንድ በመቶ ኢንቨስት ማድረግ፣ በአገር ዕድገት ላይ የሦስት በመቶ ለውጥ ያመጣል፡፡ በቴክኒክና ሙያ፣ በኢንቨስትመንትና በልማት መካከል ጥብቅ ቁርኝት ነው ያለው፤›› በማለትም ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በመነሳት የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና የፖሊሲ ግቦችን የተመለከቱት ዳይሬክተሩ ‹‹ክህሎትና አስተሳሰቡ የዳበረ ዜጋ መፍጠር፣ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት፣ ጥራትና ተገቢነትን ማረጋገጥ፣ የዘርፉን ገጽታ ማሳደግ እንዲሁም አገር በቀል ዕውቀትን ማበልፀግ፤›› የመሳሰሉ ግቦችን እንደሚያጠቃልል አስረድተዋል፡፡

የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት የዘርፉ የፖሊሲ ክንፍ ሆኖ እያገለገለ መሆኑን የገለጹት ብሩክ (ዶ/ር) ቲንክ ታንክ ከመፍጠር ባለፈ በቀጣይም ፎረሞችን ለመፍጠር እየተሠራ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

በቀድሞ መጠሪያው ኢትዮ ቻይና ቴክኒክና ሙያ በአሁኑ የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት ባዘጋጀው በዚህ መድረክ የተገኙት የሥራና ክህሎት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል፣ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍን በጥልቀት ፈትሾ አገር ሊለውጥ በሚችል መንገድ መቃኘት እንዳለበት አንስተዋል፡፡

‹‹ከዜሮ መጀመር ሳይሆን አዳዲስ ዕሳቤዎችን አካተን ዘርፉን ማሳደግ አለብን፤›› ሲሉ የተናገሩት ሚኒስትሯ፣ ከአገር ወዳድነት ስሜት ጀምሮ ዘርፉ ጠቃሚ ዕሴቶችን እንዲያካትት እንደሚደረግ ጠቁመዋል፡፡ ቴክኒክና ሙያ መስክ አዳዲስ ባለተሰጥኦ፣ አዳዲስ ባለሙያና አዳዲስ ባለክህሎት ማፍሪያ መሆን እንዳለበትም ገልጸዋል፡፡

የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ከሥራና ክህሎት ገበያው ጋር በጥብቅ የተሳሰረ መሆኑን ያመለከቱት ወ/ሮ ሙፈሪያት ዘርፉ በሚገባው መጠን መታገዝ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...