Monday, February 26, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ ቢሯቸው ሲገቡ ፀሐፊያቸው ሞባይሏን እየተመለከተች ሰትስቅ አገኟት]

 • በጠዋት ምን የሚያስቅ ነገር አግኝተሽ ነው?
 • ውይ ገብተዋል እንዴ ክቡር ሚኒስትር? 
 • ምንድነው እንደዚያ ሲያፍለቀልቅሽ የነበረው?
 • ወድጄ አይደለም ክቡር ሚኒስትር።
 • እንዴት?
 • ወዶ አይስቁ ሆኖብኝ ነው።
 • በምን ምክንያት?
 • ፌስቡክ ላይ የሚቀለደውን አይቼ… ነው ክቡር ሚኒስትር። 
 • ምን ተቀልዶ ነው?
 • አይ… ይቅርብዎት ክቡር ሚኒስትር?
 • ለምን?
 • ቢቀርብዎት ይሻላል ክቡር ሚኒስትር? 
 • ለምን? ጉዳዩ እኔን የሚመለከት ነው እንዴ? 
 • ኧረ በጭራሽ። እርስዎን በቀጥታ አይመለከትም። ቢሆንም ግን…
 • ቢሆንም ምን?
 • ብዙ አይርቅም?
 • ማለት?
 • አባል በሆኑበት የጋራ ኮሚቴ ውስጥ ከሚከታተሉት ጉዳይ ጋር ይገናኛል።
 • የትኛው ጉዳይ?
 • የመሬት ጉዳይ።
 • ምንድነው የተባለው?
 • ስላቅ ነው፡፡
 • በማን ላይ?
 • ሰሞኑን ስለመሬት ወረራ አስተያየት በሰጡት ኃላፊ ላይ።
 • ኃላፊው ምንድነው ያሉት?
 • የመሬት ወረራን ሙሉ በሙሉ አስቁመናል ነው ያሉት። 
 • እና …ፌስቡክ ላይ ምንድነው የተባለው?
 • ወረራውን ሙሉ በሙሉ ማስቆም አንድ ነገር ነው። ነገር ግን ደግሞ ይላሉ…
 • እ… ነገር ብለው ምን አሉ?
 • የተወረረውስ?

[ክቡር ሚኒስትሩ ከፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት ጋር በአገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው]

 • ክቡር ሚኒስትር ባለፈው ሊያወያዩን ሲመጡ ለአገራችን የፖለቲካ ችግር መፍትሔው አንድና አንድ እንደሆነ ነግረንዎት ነበር። ያስታውሳሉ?
 • አላስታወስም።
 • ባለፈው የመጡ ጊዜ መፍትሔው የሽግግር መንግሥት ነው ብለን ነበር።
 • እሺ፡፡
 • በድጋሚ ሲመጡም ድሎችን ማጽናትና ፈተናዎችን መሻገር ላይ እንወያይ በማለትዎ ስብሰባውን ረግጠን ወጥተን ነበር።
 • አዎ።
 • አሁን ግን የሽግግር ፍትሕ ሐሳብ ይዘው በመምጣትዎ ተደስቻለሁ።
 • ለምን?
 • ምክንያቱም እኛ ቀደም ብለን ያቀረብነው ጥያቄ ስለሆነ።
 • እናንተ የጠየቃችሁት የሽግግር መንግሥት አይደለም እንዴ?
 • ልክ ነው። እሱን የጠየቅነው።
 • ታዲያ የሽግግር ፍትሕ እኮ ሌላ ነገር ነው።
 • ቢሆንም አንድ ዕርምጃ ወደ እኛ ቀርባችኋል።
 • እንዴት?
 • ከእኛ ጥያቄ አንዱን ቃል መርጣችሁ ማከተታችሁን እያየን አይደለም እንዴ ክቡር ሚኒስትር?
 • የትኛውን ቃል?
 • የሽግግር የሚለውን። 
 • ግን እኮ…?
 • ግን የሚለውን ቃል አይጠቀሙት ክቡር ሚኒስትር?
 • ለምን?
 • አፍራሽ ነው ክቡር ሚኒስትር።
 • እናንተ ካመናችሁበት ምን አደርጋለሁ? ይሁን።
 • መደመር የምትሉት ፖሊሲ ላይም ማሻሻያ ብታደርጉ ጥሩ ነው ክቡር ሚኒስትር።
 • ምን ዓይነት ማሻሻያ?
 • የሽግግር ፍትሕ እንዳላችሁት መደመር የሚለው ላይም ከእኛ በኩል አንድ ቃል ወስዳችሁ ብታካትቱ ጥሩ ነው።
 • እሱን እንኳ እኛ መለወጥ አንችልም።
 • ለምን?
 • ኮፒ ራይት አለው። 

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...

ሕወሓት በትግራይ ጦርነት ወቅት በፌዴራል መንግሥት ተይዘው ከነበሩት አባላቱ መካከል ሁለቱን አሰናበተ

በሕወሓት አባላት ላይ የዓቃቤ ሕግ ምስክር የነበሩት ወ/ሮ ኬሪያ...

የኤሌክትሪክ ኃይል ለታንዛኒያ ለመሸጥ የሚያስችል ስምምነት ለመፈጸም የመንግሥት ውሳኔ እየተጠበቀ ነው

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ለማከናወን የሚያስችለውን...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ የካቤኔ አባል የሆኑት አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያዳመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል አግኝቼ ላነጋግርዎት የፈለግኩት። ጥሩ አደረክ። ምን አሳሳቢ ነገር ገጥሞህ ነው? ክቡር ሚኒስትር ተወያይተንና ተግባብተን ያስቀመጥናቸው አቅጣጫዎች፣ በተለይም...

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት ሞባይል ስልካቸው ላይ አተኩረው ሲመለከቱ ቆይተው፣ በድንገት ካቀረቀሩበት ቀና ብለው ባቤታቸውን ጠየቁ]

ምን ጉድ ነው የማየው? ምን ገጠመሽ? የመንግሥት ሚዲያዎች የሚያሠራጩት ምንድነው? ምን አሠራጩ? አልሰማህም? አልሰማሁም፣ ምንድነው? ዳግማዊ አፄ ምኒልክ መልዕከት አስተላለፉ እያሉ ነው እኮ። እ... እሱን ነው እንዴ? አዎ። የምታውቀው ነገር አለ? አዎ። የዓድዋ...

[ክቡር ሚኒስትሩ  የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አባላትን በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች እያዞሩ እያስጎበኙ ከአንድ ዲያስፖራ ጋር እየተወያዩ ነው]

ክቡር ሚኒስትር የዛሬ ሁለት ዓመታት ገደማ ወደ አዲስ አበባ መጥቼ ከተማዋን ጎብኝቼ ነበር። እውነት? አዎ። ታዲያ ልዩነቱን እንዴት አዩት? በጣም ይደንቃል። ሌላ ከተማ እኮ ነው የመሰለችው። አይደል? አዎ። እንዴት ነው...