Sunday, March 3, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ልናገርእርሻችን በሱስ ወይስ በማይድን በሽታ ነው የተለከፈው?

እርሻችን በሱስ ወይስ በማይድን በሽታ ነው የተለከፈው?

ቀን:

በተመስገን ታረቀ ካሳ

ዘመናችን ሱሰኝነት የገነነበት እየሆነ ነው። ሱስ ሲጀምሩት ያባብላል፣ መጨረሻው ግን በፀፀት ወደ ውድቀት መጓዝ ነው የሚሆነው። እያደገና እየተመነደገ የመጣውን ሱሰኝነት የከፋ የሚያደርገው ደግሞ፣ ሱስ የሰዎች ብቻ አለመሆኑ ነው። ከመሠረታዊ ፍላጎታችን ማሟያዎች አንዱን ምግብን ብንወስድ ምንጩ ግብርና ነው። ግብርናው መሬት በምትሰጠው ምርትና ምርታማነት ላይ የተንጠለጠለ ነው። የመሬታችንን ምርታማነት እንጨምር በሚል የእርሻ ማሳዎቻችንን የማዳበሪያ ሱሰኛ አደረግን። የእርሻው መሬት በማይድን በሽታ ተለክፎ ይሆን? የማይድኑ በሽታዎች ለሰው ልጆች የዕድሜ ልክ መከራዎች መሆናቸው እየታየ ነው።

ለብዙ ሺሕ ዓመታት ሲታረስ የነበረው የከፍተኛ ቦታ እርሻ ለም አፈሩ እየታጠበ እስከ ግብፅና ሶማሊያ የሚጓዝ ነው። በዚህ የአፈር መከላት ለዕፅዋት የሚያስፈልጋቸው ማዕድናት ተመናምነዋል ልንል እንችላለን። ይህም ቢሆን የግምት ሐሳብ እንጂ ሊታረስ የሚችለው መሬት ሁሉ የአፈር ምርመራ ተደርጎበት አይደለም። የተራቆተው የእርሻ መሬት የጎደለውን ዓይነት ማዕድን በሚፈልገው መጠን ልክ መስጠቱ ችግር ላይኖረው ይችል ይሆናል። ነገር ግን የተመናመነው ማዕድን ዘር በተዘራ ቁጥር በተመሳሳይ መጠን ለምን እንዳስፈለገን ጥናት ተደርጎ ይፋ የተደረገ ማስረጃ የለም። ብቻ የዘመቻ የክተት አዋጅ ዓይነት በጡንቸኞቹ የመገበያያ ገንዘብ ከእነሱ እየተገዛ፣ በእየእርሻ ቦታው በየዓመቱ ይደፋል። እንደ ደም ግፊት፣ እንደ ስኳር ወይም ኤችአይቪ በሽተኛ መሬቱም ዕድሜ ልኩን የማዳበሪያ መድኃኒት ወሳጅ ሆኗል። ሰውስ ዕድሜው ውስን በመሆኑ ሲሞት ሁሉ ነገር ይቆማል። መሬት ስለማይሞት የማዳበሪያ መድኃኒቱ መቼ ይሆን የሚቆመው? ለምፀዓት ጊዜ ይሆን?

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በማዳበሪያ ላይ የተንጠለጠለ የግብርና ምርት ለአምራች ከበርቴ አገሮች የማይቋረጥ የገቢ ምንጭና የበሽታ መንስዔም ነው። በሁለት መንገድ የሀብት መንጎልን ማዘጋጀት ነው የሚሆንላቸው። አንደኛው ከማዳበሪያው ሽያጭ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ለሰዎች መድኃኒትን በመቸብቸብ ይሆናል። በመድኃኒት ጥገኝነታችንም የእነሱን ሀብት ዕድሜ ዘላለማችንን እንድናደልብ ማድረጊያ መንገድ ነው። የሚገርመው ነገር ታርሶ የማያውቀውም ድንግል መሬት ሁሉ ማዳበሪያ ሲደፋበት እውነት ማዕድኑ ተመናምኖ ነው? ወይስ ዓላማው ሌላ ሆኖ? ወይስ ሲበዛበትም ምርታማ ይሆናል? ሲበዛበት ካልን ደግሞ ማዕድናቱ አልቆባቸው የሚሰጡትስ ወደፊት ሁለት፣ ሦስትና አራት፣ ወዘተ እጅ እየጨመሩ ማዳበሪያ መድፋት ሊያስፈልግ ነው?

በአገራችን ከፍተኛ ቦታዎች ማዳበሪያ ያስፈልጋቸዋል የሚል የግምት አስተሳሰብ እንቀበል ብንል እንኳን ጠቀሜታው እንዳለ ሆኖ ጎጂነቱ ምንድነው? ብለን ስንጠይቅም ልናውቅም ይገባናል። በጎጂነቱ ሁለት ትልልቅ ጉዳዮችን ማንሳት እንችላለን። አንደኛው ሰው ሠራሽ በመሆኑ ለተለያዩ ሕመሞች አጋልጦ ሊሰጥ በመቻሉ ነው። ካንሰርን ጨምሮ ልዩ ልዩ ሕመሞቸ በዚህ ምክንያት የሚበዙና የሚባዙ በመሆናቸው ለጤና አገልግሎት ከፍተኛ ወጪ እንዲወጣ ከማድረጉም ባሻገር አምራቹን የማኅበረሰብ ክፍል ሙሉ ሕይወቱን ምርታማ ሥራ ላይ እንዳይሆን ያደርገዋል። ይህ ሰው ሠራሽ ጣልቃገብነት ተደርጎበት የተገኘ ምርት ኢንኦርጋኒክ ተብሎ ባደጉት አገሮች የድሆች እንጂ የሀብታም ምግብ አይደረግም። ደሃ ቀፈቱን ሞልቶ ቢታመምና ቢሞት ለእነሱ ግድ አይሰጣቸውም።

ሁለተኛው ችግር የጡንቸኛ አገሮች ጥገኛ መሆን ነው። ጡንቸኞች የሚሰጡትን የራሳቸውን ጥቅም የማሳደድ ስግብግብነት ትዕዛዝ አገራችን ኢትዮጵያ ካልፈጸመች ማዳበሪያው ቢቆም የምግብ ዋስትናውም አብሮ የሚቆም ይሆናል። ስለዚህ ሕዝብ ይራባል። በእርግጥ ይህም እየሆነ አሁንም ረሃቡ አለ። ሦስተኛው ችግር የውጭ ምንዛሪ ጥገኝነትን ያስከትላል። ማዳበሪያው የሚገዛው በጡንቸኞች የገንዘብ ምንዛሪ ነው።  ገንዘባቸውን አንሰጥም ቢሎ እንዲሁ ረሃቡ ይከሰታል። ወደ አመፅም ሊወስድ ይችላል።

አራተኛው ችግር ጡንቸኞች በሆዳችን በቀጥታ እንደሚቆጣጠሩን የሚተማመኑ መሆናቸው ነው። ማንም ሰው ካልበላ መኖር ስለማይችል ማዳበሪያው ቢቆም ዋይታውና እሮሮው ይበዛል። ጡንቸኞችም የእባብ አዛኝ ሆነው አለንላችሁ በሚል ስላቄ ሥራቸውን መሥራት ያስችላቸዋል። አምስተኛው ችግር ጡንቸኞች በእያንዳንዳችን ላይ የክፋት ድርጊት ማድረግ ቢፈለጉ ምቹ መንገድ የሚሆንላቸው ስለሆነ ነው። ይህም ማለት በሰዎች ላይ ሊያደርጉ የሚፈልጉትን የመቆጣጠሪያ መንገድ በማዳበሪያው፣ በመድኃኒቱ፣ በመጠጦችና ምግቦች ጭምር በመቀመም አዋህደው ማሠራጨት ስለሚችሉ ነው።

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ ጸሐፊውን በኢሜይል አድራሻቸው temesgen1959@gmail.com ማግኘት ይቻላል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...