Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምበአሜሪካ ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት የተስተጓጎለው የእስራኤል ፍልስጤም ተኩስ አቁም

በአሜሪካ ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት የተስተጓጎለው የእስራኤል ፍልስጤም ተኩስ አቁም

ቀን:

በፍልስጤም ጋዛን የሚያስተዳድረው ሃማስ በእስራኤል ውስጥ ድንገተኛ የሮኬት ጥቃት ከፈጸመ ሁለት ወራት አልፈዋል፡፡ ጥቃቱን ተከትሎም እስራኤል ጋዛን የጦር ምድር አድርጋታለች፡፡ ሃማስ ድንገት ባስወነጨፋቸው ከአራት ሺሕ በላይ ሮኬቶች ከእስራኤል ወገን 1200 ፣ ጦርነቱ ከተጀመረ ካለፉት ሁለት ወራት ወዲህ ደግሞ በጋዛ 17400 ፍልስጤማውያን ተገድለዋል፡፡

አሶሽየትድ ፕሬስ እንደሚለውም፣ ከሞቱት ፍልስጤማውያን መካከል 70 በመቶው ሴቶችና ሕፃናት ናቸው፡፡ ከዚህ ባለፈም 46 ሺሕ ፍልስጤማውያን ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፣ ቁጥራቸው ያልታወቀ ደግሞ ከፍርስራሽ ስር ቀርተዋል፡፡

ይህን በተለይ በጋዛ ሰብዓዊ ቀውስ ያስከተለውንና ንፁኃን ሰለባ የሆኑበትን የእስራኤል የአየር ድብደባ ለማስቆም፣ ብሎም የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ በተለይ በዓረብ አገሮች ጥረት ሲደረግ ቢቆይም አልተሳካም፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ከሳምንታት በፊት በኳታር አደራዳሪነት የተደረሰው የስድስት ቀናት ተኩስ አቁም ስምምነት በረሃብ፣ በመፈናቀልና በተለያዩ ችግሮች ውስጥ የወደቁ ፍልስጤማውያንን ለመድረስ ለሰብዓዊ ዕርዳታ አቅራቢዎች ዕድል ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም፣ የቀኑን ማለቅ ተከትሎ ጋዛ ዳግም የጦር ዓውድማ ሆናለች፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬስ፣ በጋዛ እየደረሰ ያለውን ሰብዓዊ ውድመት በማንሳት፣ የፀጥታውን ምክር ቤት ውሳኔ እንዲያሳልፍ ጠይቀውም ነበር፡፡

ጉተሬስ ሰብዓዊ ውድመት ሲሉ የገለጹት የእስራኤል ፍልስጤም ጦርነት ያበቃ ዘንድና ተኩስ አቁም እንዲደረግ ባለፈው ሳምንት ማብቂያ የተቀመጠው የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት ተኩስ አቁም ለመወሰንም ተስኖታል፡፡

ከ15ቱ የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባላት 13ቱ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ስምምነታቸውን ባሳዩበትና እንግሊዝ ድምፅ ተአቅቦ ባደረገችበት የምክር ቤቱ ስብሰባ፣ አሜሪካ ድምፅን በድምፅ የመሻር (ቬቶ) መብቷን ተጠቅማ የ13ቱን አገሮች ድምፅ መና አስቀርታዋለች፡፡

ቀድሞውንም ከዓረብ አገር መሪዎች ጋር የመከሩት የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን፣ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ አሜሪካ ግፊት እንድታደርግ ለቀረበላቸው ጥያቄ የተኩስ አቁም ስምምነት ማድረጉ እየተበታተነ ላለው የሃማስ ቡድን ዳግሞ የመሰባሰብና በጦርነት ተጠናክሮ የመምጣት ዕድል ይሰጣል በሚል ምላሽ መሰጠታቸው ይታወሳል፡፡

ለተመድ ዋና ጸሐፊ ከተሰጡና ብዙም ጥቅም ላይ ሲውሉ ከማይታዩ መብቶች አንዱ የሆነውን ተጠቅመው ለፀጥታው ምክር ቤት ማስጠንቀቂያ አዘል ደብዳቤ የጻፉት ዋና ጸሐፊው ጉተሬስ፣ ጋዛ ከሁለት ወራት ጦርነት በኋላ የመሸመድመድ አደጋ ውስጥ ገብታለች ብለዋል፡፡

ጦርነቱ የሰው ስቃይ፣ ውድመትና በአጠቃላይም አሰቃቂ ሁኔታን ፈጥሯል ያሉት ዋና ጸሐፊው፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ያለውን አቅም ሁሉ ተጠቅሞ ጦርነቱ እንዳይባባስና እንዲቆም ኃላፊነት እንዳለበት አሳውቀው ነበር፡፡

ጉተሬስ ለ15ቱ የፀጥታው ምክር ቤት አባላት የእስራኤል ጋዛ ጦርነትን ለማስቆም ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ከማሳሰባቸው አስቀድሞ፣ በተመድ የ22 ዓረብ አገሮች ተወካዮች የተኩስ አቁም ስምምነትን እንደሚደግፉ አስታውቀው ነበር፡፡

በተመድ የፍልስጤም አምባሳደር ሪያድ መንሱር በተመድ ትልቅ አቅም ያለው አካል ጦርነቱ እንዲቆም መሥራት አለበት ብለውም ነበር፡፡ ሆኖም የእስራኤል የቀኝ እጅ አሜሪካ፣ ፀጥታው ምክር ቤት ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ የተቀበለውን ተኩስ አቁም፣ ድምፅን በድምፅ የመሻር መብቷን ተጠቅማ አምክናዋለች፡፡

እንደ ተመድ፣ ጋዛ በሰብዓዊ ቀውስ ቅዠት ውስጥ ናት፡፡ በእስራኤል በኩል ከአየር፣ ከባህርና ከእግረኛ በሚተኮስ መሣሪያ 339 የትምህርት ተቋማት፣ 26 ሆስፒታሎችና 56 የጤና ተቋማት፣ 88 መስጊዶችና ሦስት ቤተ ክርስቲያኖች ተመትተዋል፡፡

በጋዛ ከሚገኙ ቤቶች 60 በመቶ ወድመዋል፣ 85 በመቶ ነዋሪ ደግሞ ቤቱን ትቶ ተሰዷል፡፡ እንደ ጉተሬስም፣ ‹‹ማንኛውም የጋዛ አካባቢ ደኅንነቱ የተጠበቀ አይደለም፤››

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...