Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበሩብ ዓመት ከ100 ሺሕ በላይ ኢትዮጵያውያን የውጭ ሥራ ያገኙበት ሕጋዊ አሠራር

በሩብ ዓመት ከ100 ሺሕ በላይ ኢትዮጵያውያን የውጭ ሥራ ያገኙበት ሕጋዊ አሠራር

ቀን:

በዓለም ውስጥ ከ53 ሚሊዮን በላይ ሴቶች በቤት ሠራተኝነት ተቀጥረው እየሠሩ እንደሚገኙ የዓለም ሥራ ድርጅት መረጃ ያሳያል፡፡ በተለይ በባህረ ሰላጤ አገሮች ማለትም በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች፣ ኩዌት፣ ባህሬን፣ ኦማንና ሳዑዲ ዓረቢያ በርካታ የቤት ሠራተኞች ሕይወታቸውን ለመቀየር ሲሉ በሕገወጥም ሆነ ሕጋዊ በሆነ መንገድ ይጓዛሉ፡፡

ወደ እነዚህ አገሮች የሚጓዙት ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የሌሎች አገሮች የቤት ሠራተኞች የተለያየ የመብት ጥሰቶች ሲደርስባቸው መስማትም የተለመደ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የቤት ሠራተኞች የመብት ጥሰትና የደመወዛቸው የመጨረሻ ጣሪያ እንዲታወቅ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አዲስ አሠራር ተግባራዊ እያደረገ ነው፡፡

ከአገሮች ጋር ከሚደረገው የሁለትዮሽ ስምምነት ውስጥ ከሚካተቱ ስምምነቶች የደመወዝ ምጣኔ አንዱ መሆኑንና በ2016 ዓ.ም. ባለፉት አራት ወራት ውስጥም ከ108 ሺሕ በላይ ዜጎችን ወደ ውጭ ሥራ እንዲሰማሩ መደረጉን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ደኤታ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ወደ ውጭ አገር ሄደው እንዲሠሩ ከተደረጉት ውስጥ 99 በመቶ ያህሉ የቤት ውስጥ ሠራተኞች እንደሆኑ ገልጸው፣ ይህንን አሠራር ሚኒስቴሩ ዋነኛ የሥራ ዕድል መፍጠሪያ መንገድ አድርጎ እየሠራበት ነው ብለዋል፡፡

ወደ ውጭ አገሮች የሚሠማሩ የቤት ሠራተኞች ክህሎታቸውና አመለካከታቸው ተቃኝቶውና ተቀርፀው መሆን ስላለበት፣ የውጭ አገር የሥራ ሥምሪት በሥርዓተ ትምህርት ውስጥ ተካቶ እንዲተገበር ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎች እንዳሉ አስረድተዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የቤት ሠራተኞች የራሳቸውን ማኅበር ማቋቋማቸውን የተናገሩት ሚኒስትር ደኤታው፣ ማኅበር የተቋቋመበት ዋና ዓላማ በየትኛውም ወቅት ለሚደርስባቸው ችግር ተቆርቋሪ እንዲሆኑና ኃይል እንዲኖራቸው ለመርዳት መሆኑን አክለዋል፡፡

ከቤት ሠራተኞች አብዛኛዎቹ ብዙም በትምህርት ያልገፉ፣ በኑሮ ሁኔታቸው የተጎዱና በዝቅተኛ ደረጃ የሚገኙ ናቸው ያሉት አቶ ንጉሡ፣ እነዚህን በማደራጀትና ማኅበራቸውን በማጠናከር ሚኒስቴሩ የበኩሉን ይወጣል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል እነዚህን የቤት ሠራተኞች ከአሠሪዎች ጋር የሚያገኛኑ ኤጀንሲዎች እንዳሉ፣ እነዚህም ኤጀንሲዎች ለሠራተኞቹም ሆነ ለመንግሥት ሥራ የሚያቃልሉ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

ከደቡብ ጎንደር ደብረ ታቦር ዞን አንድነት የቤት ሠራተኞች ኅብረት ሰብሳቢ የሆነችው ወጣት እሌኒ ጓዳኤ ለሪፖርተር እንደገለጸችው፣ ከአገር ውጭም ሆነ አገር ውስጥ የሚሠሩ የቤት ሠራተኞች በርካታ ችግር ይደርስባቸዋል፡፡

በዝቅተኛ ቤተሰብ ውስጥ ያደገችው ይህች ወጣት ገና በለጋ ዕድሜዋ የቤት ሠራተኛ ሆና በምታገኘው ገንዘብ ቤተሰቧን ትረዳ እንደነበር ታስረዳለች፡፡

በቤት ውስጥ እሷን ጭምሮ አራት ልጆች መኖራቸውን፣ ኑሮ አቅላቸውን ሲያስታቸው እናታቸው፣ እሷንና ታላቅ እህቷን የቤት ሠራተኛ እንዲሆኑ መፍቀዳቸውን ገልጻለች፡፡

በወቅቱ ለቤት ሠራተኝነት አቅም እንዳልነበራት የምትናገረው ወጣቷ፣ አሠሪዎቿ የሚፈልጉት ሥራ ባለመቻሏ ከቦታ ቦታ እየተቀያየረች መሥራቷን ትናገራለች፡፡

ከብዙ ትግል በኋላ አንድ ጥሩ የሚባል አሠሪ ማግኘቷንና አሠሪዋ አንደኛ ክፍል እንዳስገባቻት ገልጻለች፡፡

ይሁን እንጂ ከመልካም አሠሪዋ ጋር ብዙም እንዳልቆየችና የአንደኛ ክፍል ትምህርቷን ካጠናቀቀች በኋላ ሌላ ቤት መግባቷን ታስረዳለች፡፡

ቀጥታ ወደ ሌላ ቦታም ከገባች በኋላ የተሻለ አሠሪ ማግኘቷንና ከሁለተኛ እስከ ስድስተኛ ክፍል በደብረ ታቦር ዞን የመጀመርያ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ መማሯን ያስታወሰችው ወጣቷ፣ አሁንም በድጋሚ አሠሪዋ ከአገር ወጥታ በመሄዷ ሌላ ቤት ለመግባት መገደዷን ታስታውሳለች፡፡

ነገሩም አሠልቺ ሲሆንባትና ከአንዱ ቤት ወደ ሌላው ቤት መቀያየር ሲያደክማት የተመላላሽ ሥራ መጀመሯን ገልጻ፣ የኑሮ ውድነትና የሥራ ጫና ከአቅሟ በላይ ሲሆን፣  ከትምህርት ቤት የምትቀርበት ወቅት እንደነበር ትገልጻለች፡፡

በወቅቱ ትምህርት የሚማሩት በፈረቃ ስለሆነ ከአሠሪዋቿ ጋር በመነጋገር ትምህርቷን ትከታተል እንደነበር፣ ከስምንተኛ ክፍል ጀምሮ ኑሮዋን ለብቻዋ መግፋት እንደጀመረች ታስረዳለች፡፡

ከበፊት ጀምሮ ነገሩ አልጋ በአልጋ ስላልሆነላት የአሥራ ሁለተኛ ክፍል ውጤት ሳይመጣላት እንደቀረና ትምህርቷንም ለመከታተል ብዙ ትቸገር እንደነበር ታብራራለች፡፡

የአሥራ ሁለተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት እንዳልመጣላትና አሁን ላይ ተመላላሽ እየሠራች ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የአካውንቲንግ ትምህርቷን እየተከታተለች መሆኑን ታስረዳለች፡፡

በአሁኑ ወቅት ከተመላላሽ ሥራ በተጨማሪ የጥልፍ ሥራ በመሥራት ራሷን እያስተዳደረችና ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ከዚህ በፊት ትኖርበት ከነበረው የተሻለ ኑሮ ለመኖር ጥረት እያደረገች መሆኑን ተናግራለች፡፡

የትምህርት ቤት ክፍያ፣ የኑሮ ውድነትና ሌሎች ነገሮች ትምህርቷ ላይ ጫና እየፈጠረ መሆኑን፣ በቀጣይም መንቀሳቀሻ ገንዘብ ካገኘች የጥልፍ ሥራ ላይ ትኩረት ሰጥታ ለመሥራት ሐሳብ እንዳላት ታስረዳለች፡፡

የቤት ሠራተኞች የሥራ ሁኔታቸው የሕግ ጥበቃ የሌለው በመሆኑ፣ እየደረሰባቸው ያለውን የመብት ጥሰትና ልዩ ልዩ አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት ለማስቀረት በአሠሪና በሠረተኛ አዋጅ የተቀመጠው ደንብ እንዲወጣ መንግሥት የበኩሉን መወጣት አለበት ብላለች፡፡    

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...