Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየፓሪስ ኦሊምፒክና የኢትዮጵያ ቅድመ ዝግጅት

የፓሪስ ኦሊምፒክና የኢትዮጵያ ቅድመ ዝግጅት

ቀን:

በፈረንሣይ ፓሪስ ከተማ የሚሰናዳው የኦሊምፒክ ጨዋታ ወራቶች   ቀርተውታል፡፡ በኦሊምፒክ ጨዋታው የሚሳተፉ አገሮችም ዝግጅታቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡ ከሜልቦርን ኦሊምፒክ ጀምሮ ንቁ ተሳትፎ ያላት ኢትዮጵያ በዘንድሮው የፓሪስ ኦሊምፒክ ለመሳተፍ ከወዲሁ ዝግጅት ተጀምሯል፡፡

በአኅጉር አቀፍና በዓለም አቀፍ ውድድሮች እንዲሁም የኦሊምፒክ ተሳትፎ ማግኘት በክርክር ታጅቦ የሚጠናቀቀው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ዘንድሮ መሰል ችግሮች እንዳይገጥሙት ከወዲሁ ዝግጅቱን አጠናክሮ መጀመሩ እየተገለጸ ይገኛል፡፡

የፓሪስ ኦሊምፒክ ዝግጅቶችን ከወዲሁ ለመጀመር የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ መጀመሩን የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ገልጿል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

እሑድ ኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከፓሪስ ኦሊምፒክ ቅድመ ዝግጅት በተመለከተ ከሌሎች ከተማ አስተዳደሮችና የባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡

በዚህም መሠረት በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አሸብር ወልደጊዮርጊስ (ዶ/ር) ኦሊምፒክ ጨዋታው ከመጀመሩ አስቀድሞ በክልሎች የኦሊምፒክ ችቦ ማዞር መርሐ ግብር ለማስጀመርና ከየትኛው ክልል ይጀምር የሚለውን ለመወሰን፣ በቀጣይ መርሐ ግብሮች ላይ ለመመካከር የተሰናዳ ዝግጅት መሆኑን አብራርተዋል፡፡

 እንደ ፕሬዚዳንቱ ማብራርያ ስፖርቱ ያለበት ሁኔታ አስቻጋሪ መሆኑንና በተለይ ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች እንዲበተኑ ተደርጎ፣ በጀታቸው ተቋርጦ በቆመበት ወቅት ላይ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በአንፃሩ ኦሊምፒክ ኮሚቴው ለብሔራዊ ፌዴሬሽኖቹ የተቻለውን ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ኦሊምፒክ ኮሚቴው ለፓርስ ኦሊምፒክ ጨዋታ የተለያዩ ብሔራዊ ኮሚቴዎች ተቋቁመው የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በውይይት መድረኩ የኢትዮጵያ ዝግጅትና ተሳትፎ፣ የፓሪስ ኦሊምፒክ ዕቅድና ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በኢትዮጵያ ኦሊምክ ኮሚቴ ጸሐፊ አቶ ገዛኸኝ ወልዴ ቀርበዋል፡፡ ይኼም ኦሊምፒክ ኮሚቴው ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ከተለያዩ የባለድርሻ አካላትና ይሳተፋሉ ተብለው ከሚገመቱ ተቋማት ጋር በጋራ በመመካከር የተሰናዳ መሪ ዕቅድ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በመድረኩ በቀረበው ዕቅድ መሠረት ሦስት ጉዳዮች እንደ መነሻነት የተጠቀሱ ሲሆን፣ አንደኛ ኢትዮጵያ ኦሊምፒክን ለመደገፍ በተለያየ ጊዜ ያሳዩት ተነሳሽነትና ተሳትፎ ባለፉት አራት ዓመታት የተከናወኑ አኅጉር አቀፍና አገር አቀፍ ውድድሮች ላይ ኢትዮጵያ የነበራት ጠንካራ ጎን እንዲሁም ደካማ ጎኖች ተመላክተዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ከቀረቡት ጉዳዮች መካከል ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ሲሆኑ፣ እነዚህም በአትሌቶች፣ አሠልጣኞች፣ በሙያተኞች እንዲሁም በአመራሮች መካከል ያለው ግንኙነት መደማመጥና መከባበር ያለበት መሆን እንደሚገባው ተጠቅሰዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም በተለይ አገርን ወክለው የሚወዳደሩ አትሌቶችና ባለሙያዎች ጥቅማቸው እንዲከበርና በኦሊምፒክ ጨዋታ የሚኖራቸው ውጤት የተሻለ እንዲሆን በትኩረት መሥራት እንደሚገባ አቶ ገዛኸኝ አብራርተዋል፡፡

ከዚህም ባሻገር አትሌቶች እንዲሁም አሠልጣኞች በቂ የሥልጠና ጊዜ ያስፈልጋቸዋል የሚል አስተያየት ቀርቧል፡፡

በኦሊምፒክ ቅድመ ዝግጅት መርሐ ግብር ውስጥ ታዋቂና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ማሳተፍ፣ የአሠራር ሥርዓት መዝርጋት፣ ደረጃውን የጠበቀ የአትሌቶች የልምምድ ቦታ ማሰናዳት፣ እንዲሁም ለአትሌቶች ምቹ የሆነ የአየር ሁኔታ ያሉበት ሥፍራ ማመቻቸትን ሠፍሯል፡፡

ሌላው ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አዘጋጅ ጋር በውጭ አገር ከሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመቀናጀት፣ ከዓምና ጀምሮ ሥራ ሲሠራ መቆየቱ ተብራርቷል፡፡ እነዚህን ተግባራት ለማከናወን ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ ዓብይ ኮሚቴ አዋቅሮ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም የገቢ አሰባሳቢ፣ የጉዞና የሎጂስቲክስ ኮሚቴ፣ የምዝገባና አክርዲቴሽን ኮሚቴ፣ የባህልና የገጽታ ግንባታ ኮሚቴና የቴክኒከና የሕዝብ ግንኙነት ኮሚቴ ማደራጀቱን አቶ ገዛኸኝ አብራርተዋል፡፡

ሌላው በቅድመ ኦሊምፒክ ዝግጅት በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የአሊምፒክ ችቦ በማዘዋወር ገንዘብ ማሰባሰብ፣ አትሌቶችን ማበረታታትና አትሌቶችን የመሸኘት ሥራ ይሠራል ተብሏል፡፡ በዚህም መሠረት ከዝግጅቱ ጀምሮ እስከ ውድድር መጠናቀቂያው ድረስ ያለውን ዝግጀት ለማከናወን 213,463,000 ብር በጀት የተያዘ ሲሆን፣ ይህም ከመንግሥት፣ እንዲሁም የተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መንገዶችን በመጠቀም ለመሰብሰብ መታቀዱን አቶ ገዛኸኝ አስረድተዋል፡፡

ኦሊምፒክ ኮሚቴ ባለፈው ዓመት ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ደራርቱ ቱሉ (ረዳት ኮሚሽነር)፣ እንዲሁም ኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አሸብር (ዶ/ር) ጋር በጋራ በመሆን ወደ ኔዘርላንድ በማቅናት በውጭ አገር የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተገናኝተው በፓሪስ ኦሊምፒክ ዝግጅት እያደረጉ፣ ግንዛቤ የማስጨበጥና የማስተባበር ሥራ መሠራቱን ተገልጿል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም ብሔራዊ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንና ኦሊምፒክ ኮሚቴ በጋራ በመሆን አትሌቶች ከውድድር አስቀድመው ዝግጅት የሚያደርጉበትን ካምፕ፣ ከፓሪስ በቅርበት የምትገኝ አንቶኒ ከተማ የማዘውተሪያ ሥራ መሠራቱን ገልጸዋል፡፡

ከተለያዩ ክልልና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ የውይይት መድረኩ ተሳታፊዎች፣ በተለይ ኦሊምፒክ ኮሚቴውና በአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ መካከል የነበረው አለመግባባት በሰላማዊ መንገድ መፈታት መቻሉ እንዳስደሰታቸው ሲገልጹ ነበር፡፡ ከዚህም ባሻገር ሁሌም የክርክር መንስዔ ሲሆን፣ የሚስተዋለው የአትሌቶችና የአሠልጣኞች ምርጫ ከወዲሁ ሊታሰብበት እንደሚገባ የመድረኩ ተካፋዮች አንስተዋል፡፡

በውይይት መድረኩ አዳዲሶቹን ክልሎች ጨምሮ የተሳተፉ ሲሆን፣ ችቦ የሚዞርባቸው ቀናቶች በዕጣ አወጣጥ ሥርዓት ተከፋፍለዋል፡፡

በዚህም መሠረት የመጀመርያውን የኦሊምፒክ ችቦ የትግራይ ክልል ጥር 18 ቀን 2016 ዓ.ም. የሚረከብ ሲሆን፣ የመጨረሻው ሐምሌ 8 ቀን 2016 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ማጠቃለያ ይደረጋል ተብሏል፡፡

በቅርቡ በሕዝብ ውሳኔ መሠረት የተቋቋሙት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰኔ 8 ቀን፣ እንዲሁም ማዕከላለዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰኔ 22 ቀን የኦሊምፒክ ችቦ ይረከባሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...