Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የሰሞኑ እስር አሳስቦኛል አለ

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የሰሞኑ እስር አሳስቦኛል አለ

ቀን:

ከሰሞኑ በመንግሥት ኃይሎች የተወሰደው በተቃዋሚ ፖለቲከኞች ላይ ያተኮረው የእስር ዘመቻ እንደሚያሳስበው፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አስታወቀ፡፡ ገዥው ብልፅግናን ጨምሮ 61 የፖለቲካ ድርጅቶች ያሉበት የጋራ ምክር ቤት ዕርምጃው የመድበለ ፓርቲ ሥርዓቱን ይጎዳል ብሏል፡፡

በጉዳዩ ላይ አስተያየት የተጠየቁት የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢና የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ዋና ጸሐፊ አቶ ደስታ ዲንቃ፣ ምክር ቤቱ የእስር ዘመቻውን በሚመለከት ተሰብስቦ አንድ የሆነ የጋራ አቋም ለመያዝ ጊዜ እንዳላገኘ ተናግረዋል፡፡ ይሁን እንጂ በግላቸው የሰሞኑ ዕርምጃ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን እንደሚያምኑ አስረድተዋል፡፡

በኦፌኮም ሆነ በመድረክ ውስጥ ረዥም ዓመታት ሲታገሉ የቆዩ፣ በእስራት የተፈተነ የትግል ሕይወት ያላቸውና የሕግ ባለሙያም ጭምር የሆኑ ፖለቲከኛ መሆናቸውን የጠቀሱት አቶ ደስታ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል በሠልፍ፣ በተቃውሞና በመግለጫ እንደሚካሄድ ጠንቅቀው እንደሚያውቁ ገልጸዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

‹‹አሁን ግን የተለመደውን ዓይነት የፖለቲካ ትግልም እንኳ ማካሄድ ያልቻልንበት ሁኔታ (ለውጥ) ላይ ነው ያለነው፤›› ብለዋል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገዥው ፓርቲን ጨምሮ 61 ድርጅቶች ያሉበት ነው ይላሉ፡፡ መጋቢት 11 ቀን 2011 ዓ.ም. በፀደቀው የቃል ኪዳን ሰነድ ላይም ኃላፊነቱ በአግባቡ መቀመጡን ያወሳሉ፡፡ ምክር ቤቱ አንዱን ወገን ለማስደሰት ሌላውን ለማስከፋት እንደማይሠራ በማስታወስም፣ በአገሪቱ ባሉ የፖለቲካ ኃይሎች መካከል መግባባት እንዲፈጠር እንደሚሠራ ገልጸዋል፡፡ ይሁን እንጂ በአገራዊና አሳሳቢ ጉዳዮች ላይ እንኳ የጋራ አቋም ለመያዝ እንደሚቸገር ነው የተናገሩት፡፡

ያም ቢሆን ግን ‹‹የፖለቲከኞች መታሰር፣ የጋዜጠኞች መታሰርም ሆነ የመንግሥት ወገንን ጨምሮ በየቦታው የዜጎች መሞት በእጅጉ ያሳስበናል፤›› በማለት ነው ያስረዱት፡፡

በሌላ በኩል ለእሑድ ኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ተጠርቶ የነበረው የሰላማዊ ሠልፍ እንደማይመለከተው ቅዳሜ ዕለት በመግለጫ ይፋ ያደረገው የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት፣ ተቃውሞ ማድረግና ሰላማዊ ሠልፍ መጥራት የሁሉም መብት መሆኑን አስታውቋል፡፡

ብልፅግናን ጨምሮ ከ15 ያላነሱ ፓርቲዎችን ያቀፈው የአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሠልፉን የጠሩ ወገኖች ወደ 13 ፓርቲዎች ደግፈውታል ማለታቸው የተሳሳተ መሆኑን ገልጿል፡፡ ለዚህ ምላሽ ለመስጠት ሲባል አስቸኳይ ስብሰባ በመጥራት የጋራ መግለጫ መስጠቱን ነው የምክር ቤቱ ሥራ አስፈጻሚ አባል አቶ ዘሪሁን ገብረ እግዚአብሔር የተናገሩት፡፡

‹‹ከዚህ ውጪ እከሌ እንደዚህ ይሁን እከሌ እንደዚያ ነው ብለን የጋራ አቋም አልያዝንም፡፡ የሰዎቹን ጉዳይ የሚያጣራው ፖሊስ እንጂ እኛ አይደለንም፡፡ በአስቸኳይ ስብሰባችን የተሰማማነውም ሆነ ባንፀባረቅነው የጋራ አቋም ያሰመርንበት ተቃውሞ ማካሄድም ሆነ ሰላማዊ ሠልፍ መጥራት ለማንም ቢሆን መብት መሆኑን ነው፤›› በማለት ተናግረዋል፡፡

አቶ ዘሪሁን አክለውም ምንም ይሁን ምን ሰዎች ከሕግ አግባብ ውጪ መታሰራቸውን ምክር ቤቱ እንደሚቃወምና በአስቸኳይ ተጣርቶም ለሕግ እንዲቀርቡ እንደሚፈልግ ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...