Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናለጦርነት የታየው ተነሳሽነት ለሰላም ግንባታ አለመታየቱን የተሃድሶ ኮሚሽን ገለጸ

ለጦርነት የታየው ተነሳሽነት ለሰላም ግንባታ አለመታየቱን የተሃድሶ ኮሚሽን ገለጸ

ቀን:

የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ የማስፈታቱና መልሶ የማቋቋሙ ሥራ በተጠበቀው ልክ ድጋፍ አለማግኘቱን ብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን ገለጸ፡፡ በጦርነቱ ወቅት የነበረው የሕዝብ ድጋፍና ተነሳሽነት የሰላም ግንባታ አካል በሆነው የተሃድሶ ሥራ ላይ አለመንፀባረቁን ነው ኮሚሽኑ ያስታወቀው፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎችን ያሰባሰበና የተሃድሶ ሥራውን በግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራዎች እንዲያግዙ ለማድረግ ያለመ የሁለት ቀናት የምክክር መድረክ፣ ከማክሰኞ ታኅሳስ 2 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ ላይ የተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነሩ ተሾመ ቶጋ (አምባሳደር) ኮሚሽናቸው ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ስላደረጋቸው የሥራ እንቅስቃሴዎች ለፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች አብራርተዋል፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት የሚቻልበትን ዓውድ በመፍጠር እንዲያግዙና ለተሃድሶ ኮሚሽኑ ሥራዎች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በጀርመኑ ኢልኮ ፋውንዴሽንና በተሃድሶ ኮሚሽኑ ትብብር በተዘጋጀው ዓውደ ጥናት፣ በተሃድሶ ሥራዎች ረገድ የተሻለ ልምድ ለማስጨበጥ እንዲያግዝ የሞዛምቢክ ተሞክሮ መቅረቡ ታውቋል፡፡

ሪፖርተር ያነጋገራቸው የተሃድሶ ኮሚሽኑ የኮሙዩኒኬሽንና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ልዑልሰገድ በላይነህ፣ ኮሚሽኑ የተቋቋመበትን ዓላማ ለማሳካት የፖለቲካ ፓርቲዎችን ብቻ ሳይሆን የሚዲያ፣ የማኅበረሰብ ወኪሎች፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችንና የሁሉንም አካላት ድጋፍ እንደሚፈልግ አስረድተዋል፡፡

ኢትዮጵያ የረዥም ጊዜ የጦርነት  ልምድ ያላት አገር መሆኗን የገለጹት አቶ ልዑልሰገድ፣ በሰላም ግንባታ ረገድ ግን ለተሃድሶ ኮሚሽን ሥራ ልምድ የሚሆን ነገር የላትም ብለዋል፡፡ ማኅበረሰቡ ችግርን ተቋቁሞ የመኖር አቅሙ ከፍተኛ መሆኑን ብዙ ርቀት አልፎ ዛሬ ላይ መድረሱን ጠቁመዋል፡፡

ኮሚሽኑ የጀመረው ተዋጊዎችን ትጥቅ በማስፈታት ወደ ሰላማዊ ሕይወት የመመለስ ሥራ፣ ‹‹ኢትዮጵያ እንደ አገር አትበተንም ትቀጥላለች ብለን ለዓለም የምናሳይበት ትልቅ አገራዊ ኃላፊነት ነው፤›› ብለውታል፡፡

ይሁን እንጂ የፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነት ሲፈረም ለዚህ ሥራ ሁሉንም ዓይነት ትብብር ለማድረግ ቃል ገብተው የነበሩ የውጭ መንግሥታትና ለጋሾች ቃል በገቡት ልክ እየደገፉ አለመሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የአገር ውስጥ ዕርዳታና ድጋፍም ቢሆን እንደጠበቁት አለመሆኑን የገለጹት ዳይሬክተሩ፣ ‹‹ለጦርነት የነበረውን ድጋፍና ተሳትፎ ያህል የሰላም ግንባታ አካል በሆነው የተሃድሶ ሥራ ላይ አልታየም፤›› ብለዋል፡፡

የተሃድሶ ሥራው አስፈላጊውን ድጋፍ ከሁሉም ወገን አግኝቶ በቶሎ መካሄድ ካልቻለና በጥናት የተለዩ በመላ አገሪቱ ያሉ ወደ 371 ሺሕ የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ ማቋቋም ካልተቻለ፣ እየተደራረቡ ከቀጠሉ የግጭት ችግሮች ጋር ተደምሮ አገሪቱን ወደባሰ ቀውስ ሊከታት እንደሚችልም ጠቅሰዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...