Sunday, March 3, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበጎንደር ከተማ የሚገኙ ተፈናቃዮች ወደ ቀዬአቸው ካልተመለሱ ዕርዳታ አያገኙም መባላቸውን ተናገሩ

በጎንደር ከተማ የሚገኙ ተፈናቃዮች ወደ ቀዬአቸው ካልተመለሱ ዕርዳታ አያገኙም መባላቸውን ተናገሩ

ቀን:

በአማራ ክልል በጎንደር ከተማ ቀበሮ ሜዳ ተፈናቃዮች ወደ መጡበት ቀዬ ካልተመለሱ ምንም ዓይነት ዕርዳታ እንደማያገኙ ከክልሉ መንግሥት እንደተነገራቸው፣ የጎንደር ከተማ አስተዳደር የተፈናቃዮች አስተባባሪ አቶ አቶ መላኩ ገብሬ ለሪፖርተር ተናገሩ፡፡

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከጎንደር ከተማ አቅራቢያ አዘዞ ቀበሮ ሜዳ እየተባለ በሚጠራው የተፈናቃዮች የመጠለያ ጣቢያ የሚገኙ 2,703 መሆናቸውን፣ ይሁንና ወቅቱን ጠብቆ ዕርዳታ እየቀረበላቸው እንዳልሆነና ተፈናቃዮቹ ወደ ቀዬአቸው መመለስ እንደማይፈልጉ አስተባሪው አስረድተዋል፡፡

በተለያዩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶችና የመንግሥት አካላት ተፈናቃዮችን ወደ ቀዬአቸው የመመለስ ፍላጎት ላይ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት፣ 90 በመቶ ያህሉ ወደ ነበሩበት አካባቢ መመለስ የማይፈልጉ መሆናቸው መረጋገጡን ገልጸዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ተፈናቃዮቹ ወደ ነበሩበት ከመመለስ ይልቅ ምዕራብ አርማጭሆ መስፈር እንደሚፈልጉ የገለጹት አስተባባሪው፣ ነገር ግን በመንግሥት በኩል ፈቃደኛ ወይም ተቀባይነት እንዳላገኙ አስረድተዋል፡፡ ተፈናቃዮቹ ምዕራብ አርማጭሆ እንደነበሩ በመግለጽ፣ በተለያዩ ችግሮች ሳቢያ ከአካባቢው መልቀቃቸውን መናገራቸውን አቶ መላኩ ገልጸዋል፡፡

የዓለም የምግብ ፕሮግራም የምግብ ዕርዳታ እንዲያቀርብላቸው ጥያቄ ማቅረባቸውን የገለጹት አቶ መላኩ፣ ይሁን እንጂ የክልሉ መንግሥት ፈቃደኛ አለመሆኑንና ሰሜን ዳባት ዕርዳታ እንዲያቀርብ ብቻ እንደተፈቀደላት ተናግረዋል፡፡

እንደ አስተባባሪው ገለጻ፣ በሰሜኑ ኢትዮጵያ ጦርነት ሳቢያ ተፈናቅለው በቀበሮ ሜዳ መጠለያ ጣቢያ የደረሱ 3,050 እንደነበሩ፣ ይሁን እንጂ ከጊዜ ወደ ጊዜ በገጠማቸው የምግብ ዕጦትና የተለያዩ ምክንያቶች ወደ ተለያዩ ቦታዎች ሄደው አሁን የቀሩት 2,703 ናቸው፡፡

ኢትዮጵያ ተቀብላ ካፀደቀችው ዓለም አቀፍ ሕጎች አንዱ የካምፓላ ኮንቬንሽን መሆኑን የገለጹት አቶ መላኩ፣ መንግሥት ለተፈናቀሉ ዜጎች የምግብ፣ የመጠለያ፣ የጤናና ሌሎች መሠረታዊ ግብዓቶችን የማሟላት ግዴታ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

ተፈናቃዮቹ ከስድስት ወራት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ወደ ነበሩበት የመመለስ፣ ወይም ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም ለተፈናቃዮች ዘላቂ መፍትሔ ማበጀት የመንግሥት ኃላፊነት መሆኑን አክለዋል፡፡ ከዚህ ባለፈ መንግሥት ተፈናቃዮችን ወደ አካባቢያቸው የመመለስ፣ አሊያም ማቋቋሚያ በመስጠት ሌላ ቦታ የማስፈር እንደሚገባው በተለያዩ የሕግ ማዕቀፍ እንደተቀመጠ ያስረዳሉ፡፡

ይሁን እንጂ ‹‹በቀበሮ ሜዳ›› የሚገኙ ተፈናቃዮች በሕግ አግባብ መሠረት ከላይ የተጠቀሱ መሠረታዊ ጉዳዮች ያልተሟላላቸው በመሆናቸው፣ ለከፋ ረሃብ መጋለጣቸውን አስተባባሪው አስረድተዋል፡፡

በመንግሥት ለተፈናቃዮቹ የተሰጠው በ2015 ዓ.ም. ሐምሌና በጥቅምት 2016 ዓ.ም. የተወሰነ ዕርዳታ መቅረቡን፣ ከዚያ በኋላ ምንም ዓይነት ዕገዛ እንዳላገኙ ተናግረዋል፡፡

አሁን ተፈናቃዮች የሚበሉት እንዳጡና የሚተኙት መሬት በመሆኑ በትል ሰውነታቸው እየተበላ እንደሚገኝ ገልጸው፣ ያለውን ችግር ለጤና ቢሮና ለሚመለከተው አካል ጉዳዩን ቢያቀርቡም መፍትሔ አልተገኙም ብለዋል፡፡

ዓለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት ተንቀሳቃሽ ክሊኒክ ቢያቋቁሙም አቅርቦቶቹ ፓናዶልና ሌሎች ቀላል መድኃኒቶች መሆናቸውን፣ ከዚያ ውጪ ያሉትን ወደ አዘዞ ጤና ጣቢያ ሪፈር እንደሚጻፍላቸው ተናግረዋል፡፡

ከአዘዞ ጤና ጣቢያ አቅም በላይ የሆኑ ችግሮች ወይም ውስብስብ የጤና እክል ያለባቸው ተፈናቃዮች ወደ ተለያዩ ሆስፒታሎች ሄደው ለመታከም የአቅም ውስንነት እንዳለባቸው፣ በዚህ ምክንያት ሟቾች ቁጥራቸው መጨመሩን ገልጸዋል፡፡

በመጠለያ ጣቢያው የክልሉ፣ የፌዴራል መንግሥትና የዓለም የምግብ ፕሮግራም ጭምር የከፋ ረሃብ ውስጥ እንደሚገኙ ማየታቸውን ያስረዱት አቶ መላኩ፣ በ45 ቀናት መፍትሔ ይሰጣል ተብሎ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

ይሁን እንጂ በጎንደር ከተማ የሚገኘው የዓለም የምግብ ፕሮግራም የሚሰጠውን ዕርዳታ የክልሉ መንግሥት በቦታ እንደገደበው፣ ሰሜን ዳባት ብቻ ዕርዳታ እንዲያቀርብ እንደተነገረው አስተባባሪው ገልጸዋል፡፡

በዚህም ምክንያት የዓለም የምግብ ፕሮግራም ለቀበሮ ሜዳ ተፈናቃዮች ዕርዳታ ማድረስ አለመቻሉን ገልጸዋል፡፡

ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ተቀናጅተው ተፈናቃዮች የሚያስፈልጓቸውን በፍጥነት ምግብ፣ መጠለያና ሌሎች መሠረታዊ ፍላጎቶች እንዲያቀርቡላቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...