Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበመገናኛ ብዙኃን የሥርዓተ ፆታ ፖሊሲ እንደሚያስፈልግ ተገለጸ

በመገናኛ ብዙኃን የሥርዓተ ፆታ ፖሊሲ እንደሚያስፈልግ ተገለጸ

ቀን:

በኢትዮጵያ በመገናኛ ብዙኃን ውስጥ የሚሠሩ ሴቶችን ሚና ለማጉላትና የሚደርስባቸውን ፆታዊ ጥቃት ለመከላከል መገናኛ ብዙኃን የሥርዓተ ፆታ ፖሊሲ እንደሚያስፈልጋቸው ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያ ሴቶች ማኅበር ከአጋሮቹ ጋር በመሆን በመገናኛ ብዙኃን ውስጥ የሥርዓተ ፆታ ፖሊሲ መኖርን በተመለከተ ያስጠናውን ጥናት ይፋ ሲያደርግ እንደተገለጸው፣ በጥናቱ ከተሳተፉ 16 የሚዲያ ተቋማት ውስጥ የሥርዓተ ፆታ ፖሊሲ ያለው አንዱ ብቻ ነው፡፡

በመገናኛ ብዙኃን የሥርዓተ ፆታ ፖሊሲ እንደሚያስፈልግ ተገለጸ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና
ዳይሬክተር አቶ መሐመድ ኢድሪስ

ጥናቱ ሲካሄድ በኤዲቶሪያል ፖሊሲ ውስጥ ሥርዓተ ፆታን ያካተተ ሐረግ ያላቸው ተቋማት ቢኖሩም፣ በአፈጻጸሙ በኩል ክፍተት መኖሩን ጥናቱ አሳይቷል፡፡ የማኅበሩ የቦርድ አባል ወ/ሮ መሠረት ከበደ እንዳሉት፣ በሚዲያ ውስጥ የሥርዓተ ፆታ ፖሊሲ አለመኖር፣ በሥርዓተ ፆታ ዙሪያ ያለው የግንዛቤ እጥረት እንዳለ ሆኖ፣ በተለይ ሴት ጋዜጠኞች ከወንዶች እኩል ሚናቸውን እንዳይወጡና የሚገባቸውን የሥራ ቦታና ክፍያ እንዳያገኙ አድርጓል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የመገናኛ ብዙኃን ማኅበረሰብን የመቅረፅ፣ የመወያያ ሐሳብ የማቅረብ፣ መረጃ የመስጠትና ሌሎችም ኃላፊነቶች እንዳሉባቸውና የሴቶችንም ሆነ የወንዶችን ድምፅ በእኩል መተግበር እንደሚገባቸው በመግለጽ፣ ይህ ባለመሆኑ አሠራሩን ለማሻሻል የሥርዓተ ፆታ ፖሊሲ በማውጣት መደገፍ እንደሚያስፈልግም አክለዋል፡፡

የሥርዓተ ፆታ ፖሊሲ ለማዘጋጀት የሚረዱ ግብዓቶች ለማሰባሰብና የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስ ማኅበሩ ባዘጋጀው መድረክ፣ በመገናኛ ብዙኃን የሴቶች ቁጥር ከወንዶች እንደሚያንስ፣ መገናኛ ብዙኃን በአብዛኛው የሴቶች ድምፅ የሚሰማባቸው አለመሆናቸው፣ የሥርዓተ ፆታ እኩልነት እንደማይተገበር፣ ሴቶች ወደ አመራር ሰጪነትና አመራር ቦታ እንደማይደርሱ፣ ፆታዊ ጥቃትን ጨምሮ የተለያዩ ጥቃቶች እንደሚፈጸምባቸው ተጠቁሟል፡፡

ሴቶች በኃላፊነት ደረጃ በማይገኙባቸውና የኤዲቶሪያል ስብሰባ በከፍተኛ ኃላፊዎች ብቻ በሚደረጉባቸው የሚዲያ ተቋማት፣ ሴቶች በኤዲቶሪያል ስብሰባም ሆነ ውሳኔ በሚፈልግ ጉዳይ እንደማይሳተፉ፣ ይህም ሴቶች የተሟላ ድምፅ እንዳይኖራቸው ማድረጉን በመግለጽ፣ ችግሩን ለመቅረፍ የሥርዓተ ፆታ ፖሊሲ ያስፈልጋል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ በበኩላቸው፣ ቀና ብለው የሚሠሩ ሴት ጋዜጠኞች ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ከሚዲያው ሲጠፉ እንደሚስተዋል፣ ለዚህም አሠራሩን በፖሊሲና በሥርዓት በመደገፍ ማገዝ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ባለሥልጣኑ፣ የአቅም ግንባታ ሥራዎቻችን ከማኅበሩ ጋር ከዓምና ጀምሮ በመተባበር ሴቶችን ክህሎት ዕውቀት ለማዳበር ሥራ መጀመሩንና ይህንንም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

ከምንም በላይ እንደተቆጣጣሪ አካል በሚዲያ ኢንዱስትሪ ውስጥ ሴቶችን የሚያጎለብቱ ፖሊሲዎች እንዲኖሩ፣ ኢንዱስትሪው ለሴቶች ምቹ እንዲሆን፣ ሴቶች ወደ አመራርነት እንዲመጡና የአቅም ግንባታ ሥራ እንዲከናወን የሚያግዝን የአሠራር ሥርዓት፣ መመርያና ማዕቀፍ በማዘጋጀት ኢንዱስትሪው ላይ መሥራት እንደሚገባ ተረድተናል ብለዋል፡፡

የሴቶች ተፈጥሯዊ ስጦታ ሚዲያው ላይ የሚኖራቸውን ሚና ለመወጣት ብቁ እንደሚያደርግና በሚዲያ ኢንዱስትሪው ውጤታማ መሆናቸውን ብንረዳም፣ ይህ በፖሊሲ ካልተደገፈና የሚታገዝበት መንገድ ካልተመቻቸ ችግሩን መቅረፍ እንደማይቻል ተናግረዋል፡፡

 የሚዲያ ኢንዱስትሪው በፖሊሲ ታግዞ ለሴቶች ምቹ ከጥቃት የሚጠብቅ፣ ሲወልዱ አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያደርግ፣ ልጅ እያሳደጉ ሥራ መሥራት የሚችሉበትን አሠራር መፍጠር ይገባዋልም ብለዋል፡፡

ይህንን በፖሊሲ ለመደገፍ ባለሥልጣኑ የተጀመሩትን ሥራዎች የሥራ አካል ያደርገዋል፣ በፖሊሲ እንዲደገፍም ከማኅበሩ ጋር በመተባበር፣ ለሁሉም የሚሆን የፖሊሲ ማዕቀፍ በማዘጋጀት ሥራ ይሠራል፣ ይህንን መሠረት አድርጎም የግንዛቤ ማሳደግ፣ የመከታተልና የማስፈጸም ሥራዎች እንደሚሠሩ አክለዋል፡፡     

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...