Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበዲሲፕሊን ጥሰቶች የታጀበው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቀጣይ ማረፊያው ድሬዳዋ ሆኗል

በዲሲፕሊን ጥሰቶች የታጀበው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቀጣይ ማረፊያው ድሬዳዋ ሆኗል

ቀን:

  • በአንድ ሳምንት አራት ቀይ ካርዶች ተመዘዋል

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እየተከናወነ የሚገኘው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ቀጣይ ማረፊያው ድሬዳዋ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

እሑድ መስከረም 20 ቀን 2016 ዓ.ም. በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የጀመረው ውድድሩ፣ ከስምንተኛ ሳምንት በኋላ በድሬዳዋ ስታዲየም እንደሚከናወን ታውቋል፡፡

በዚህም መሠረት ዘጠነኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ ግብር ከታኅሣሥ 24 ቀን ጀምሮ በድሬዳዋ ይከናወናል፡፡ የፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ከዘጠነኛ ሳምንት ጀምሮ እስከ 15ኛው ሳምንት በድሬዳዋ ከተማ እንደሚከናወን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ያወጣው መርሐ ግብር ያመለክታል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ዓምና ፕሪሚየር ሊጉን ያስተናገደው የድሬዳዋ ስታዲየም በዝናብ ምክንያት ጨቅይቶ ውድድር ጨዋታ ማስተናገድ ተስኖት መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ሆኖም ዘንድሮ ሳይቆራረጥ ማስተናገድ እንዲቻል የከተማ አስተዳደሩ 50 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ የመጫወቻ ሜዳውን ሰው ሠራሽ ሳር አልብሷል፡፡

በዚህም መሠረት ስታዲየሙ የዘንድሮውን ውድድር ያለማቋረጥ ማስተናገድ እንደሚችል ይጠበቃል፡፡ በሌላ በኩል ሊጉ በከፍተኛ የዲሲፕሊን ጥሰቶች ታጅቦ እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን፣ በስድስተኛ ሳምንት በርካታ ጥሰቶችን ማስተናገዱን አክሲዮን ማኅበሩ ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ሥነ ሥርዓት ኮሚቴ ኅዳር 24 ቀን ባደረገው ስብሰባው የተደረጉ የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዎች ከዳኞችና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

በዚህም መሠረት በሳምንቱ በተደረጉ ጨዋታዎች ስድስት በመሸናነፍ ቀሪ ሁለቱ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቁ፣ 16 ጎሎች በ15 ተጫዋቾች ተቆጥረዋል። በአጠቃላይ 34 ቢጫና ቀይ ካርዶዎች ተመዘዋል፡፡

በሳምንቱ አራት ተጫዋቾች ላይ የዲሲፕሊን ውሳኔ መተላለፉ የተጠቀሰ ሲሆን፣ የሀምበሪቾ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ተጫዋቹ ቴዎድሮስ በቀለ ክለቡ ከፋሲል ከነማ ጋር ባደረገው ጨዋታ በስምንተኛ ደቂቃ ላይ የተጋጣሚውን ቡድን ግልጽ ግብ ዕድል በማበላሸት ከጨዋታ ሜዳ መታገዱ ተገልጿል፡፡

በዚህም ለፈጸመው ጥፋት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን መመርያ መሠረት ሦስት ጨዋታ እንዲታገድና የገንዘብ ቅጣት 3,000 ብር እንዲቀጣ ተላልፎበታል፡፡ ሌላው የወልቅጤ ከተማው ተስፋዬ መላኩ ክለቡ ከሻሸመኔ ከተማ ጋር ባደረገው ጨዋታ በ67ኛ ደቂቃ ላይ የተጋጣሚውን ተጫዋች በመማታት ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ሲሆን፣ ተጫዋቹ ለፈጸመው ጥፋት፣ አራት ጨዋታ እንዲታገድና የገንዘብ ቅጣት ብር 3,000 ብር እንዲከፍል መወሰኑን አክሲዮን ማኅበሩ አስታውቋል፡፡

በተጠባቂው የባህር ዳርና ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ፣ የቅዱስ ጊዮርጊሱ ሞሰስ ኦዶ፣ በስድስተኛ ሳምንት ጨዋታ በሰባተኛው ደቂቃ ላይ የተጋጣሚውን ተጫዋች በመማታት ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ሲሆን፣ ተጫዋቹ ለፈጸመው ጥፋት መሠረት አራት ጨዋታ እንዲታገድና የገንዘብ ቅጣት 3,000 ብር እንዲቀጣ ተወስኖበታል፡፡ 

በሌላ በኩል በስድስት ክለቦች ላይም የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎች ተላልፈዋል፡፡  መቻል (አራት ተጫዋቾች)፣ አዳማ ከተማ (አምስት ተጫዋቾች)፣ ባህር ዳር ከተማ (ስምንት ተጫዋቾች)፣ ወልቂጤ ከተማ (አራት ተጫዋቾች) በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ፣ ክለቦቹ የገንዘብ ቅጣት 5,000 ብር እንዲከፍሉ ተወስኗል፡፡ በተጨማሪም ቅዱስ ጊዮርጊስ ከባህር ዳር ከተማ ጋር በነበረው ጨዋታ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች የዕለቱ ዳኞችን ስለመሳደባቸውና የውኃ መጠጫ ፕላስቲክ ጠርሙስ ወደ ሜዳ ስለመወርወራቸው ሪፖርት  ቀርቧል፡፡

በዚህም መሠረት ቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎቹ ስለተሳደቡ 50,000 ብር፣ እንዲሁም ቁሳቁስ ወደ ሜዳ በመወርውራቸው 25,000 ብር፣ በድምሩ 75,000 ብር እንዲከፍል ተወስኖበታል፡፡

ሌላው ቅጣት አዳማ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በነበረው ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች የዕለቱ ዳኞችን ስለመሳደባቸው ሪፖርት የቀረበበትና ደጋፊዎች ከዚህ በፊት በመሳደብ ከተቀጡት ቅጣት ሊታረሙ ባለመቻላቸው፣ አዳማ ከተማ 75,000 ብር እንዲከፍል፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎችም የራሳቸውን ቡድን ተጫዋቾችና የቡድን አመራሮች ስለመሳደባቸውና ለመደባደብና የኃይል ጥቃት ለማድረስ ስለመሞከራቸው ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፣ የክለቡ ደጋፊዎች በተደጋጋሚ አፀያፊ ስደብ በመሳደብ ከተቀጡት ቅጣት ሊታረሙ ባለመቻላቸው በዲሲፕሊን መመርያ መሠረት ኢትዮጵያ ቡና 100,000 ብር እንዲከፍል መወሰኑ ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...