Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናሰላማዊ ሠልፍ እንዲደረግ ያስተባበሩ የኮሚቴ አባላት ታሰሩ

ሰላማዊ ሠልፍ እንዲደረግ ያስተባበሩ የኮሚቴ አባላት ታሰሩ

ቀን:

በኢትዮጵያ ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆምና ሰላማዊ ድርድር እንዲጀመር የሚጠይቅ ነው የተባለ ሰላማዊ ሠልፍ የጠሩ፣ የሰላማዊ ሠልፍ አስተባባሪዎች መታሰራቸው ተነገረ፡፡ እስካሁን አራት የሠልፉ አስተባባሪዎች መታሰራቸው የተረጋገጠ ሲሆን፣ ለዛሬ ኅደር 30 ቀን 2016 ዓ.ም. በአዲስ አበባ እንዲካሄድ ተጠርቶ የነበረው ሠልፍም መሰረዙ ታውቋል፡፡

ሠልፉን የጠራነው ‹‹የማንንም የፖለቲካ ኃይል ወግነንና የተለየ የፖለቲካ ፍላጎት ለማራመድ አስበን አይደለም›› ያሉት የሠልፉ አስተባባሪዎች፣ የጠሩት ሠልፍም በእስር ዘመቻው የተነሳ መሰረዙን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሊቀመንበርና ከሠልፉ አስተባባሪዎች አንዱ የሆኑት ዝናቡ አበራ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) በአጠቃላይ አራት የሠልፉ አስተባባሪዎች መያዛቸውን ለሪፖርተር አረጋግጠዋል፡፡ ‹‹የፓርቲያችን ምክትል ተቀዳሚ ሊቀመንበርና የሠልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል መጋቢ ብሉይ አብርሃም ሃይማኖትን ጨምሮ የሠልፉ አስተባባሪ የነበሩ ሌሎች ሰዎች ተይዘዋል፡፡ ከታሰሩት ውስጥ አቶ ጊዴና መድህን አስተባባሪ ኮሚቴ አባልና የሰባ እንደርት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ሲሆኑ፣ ሌላኛው ታሳሪ የሠልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ አባልና የሰባ እንደርታ ፓርቲ ፀሐፊ ካልአዩ መሀሪ፣ እንዲሁም የቀድሞ የኢዜማ ፓርቲ አባል የሆኑትና አሁን በግል የሚንቀሳቀሱት ፖለቲከኛው አቶ ናትናኤል መኮንንም ይገኙበታል፤›› ብለዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

መንግሥት እስካሁን ወደ 97 ሰዎችን አሰርኩ ማለቱን የጠቀሱት ዝናቡ (ተባባሪ ፕሮፌሰር)፣ ይህ ሁሉ እስራት የመጣው የሠልፉን ጥሪ ተከትሎ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ይህ ሁኔታ ወደ መረጋጋት እንዲመጣ የማድረግ ኃላፊነት አለብን፡፡ ስለዚህ ጠርተነው የነበረውን ሠልፍ ሰርዘነዋል፤›› ሲሉ የተናገሩት የኢሕአፓው መሪ፣ ሠልፉ የተጠራው ለአገርና ለሰላም በመቆርቆር እንጂ በፓርቲ ወይም በፖለቲካ ውግንና አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡

የመንግሥት የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ሐሙስ ኅዳር 27 ቀን 2016 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ‹‹በሰላማዊ ሠልፍ ሽፋን አዲስ አበባ ውስጥ ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ቡድኖች ሴራ ከሽፏል፤›› ሲል አስታውቆ ነበር፡፡ ግብረ ኃይሉ በዚሁ መግለጫው ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር በማሴር የተጠረጠሩ 97 ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውንም አረጋግጦ ነበር፡፡

ከሰሞኑ የፖለቲከኞች እስራት ጋር በተገናኘ አባሌ ታስረውብኛል ያለው እናት ፓርቲ፣ ዕርምጃው ተቀባይነት እንደሌው ገልጿል፡፡ የፓርቲው ሕዝብ ግንኙነት አቶ ዳዊት ብርሃኑ ለሪፖርተር እንደተናገሩት ‹‹ኅዳር 26 ቀን 2016 አራት ኪሎ ከሚገኘው ጽሕፈት ቤትችን አባላችን የሆነውን ብርሃኑ ባብዬን የፀጥታ ኃይሎች ይዘው የወሰዱት ቢሆንም መልሰው ለቀውታል፤›› ብለዋል፡፡

‹‹አቶ ብርሃኑ ከአምስት ሰዓት እስራት በኋላ ቢለቀቅም በማግስቱ ደግሞ የቀድሞ የፓርቲያችንን ፀሐፊና አሁን አባል የሆኑትን አቶ ጌትነት ወርቁን መልሰው አስረውታል›› በማለት ሕዝብ ግንኙነቱ አቶ ዳዊት አክለዋል፡፡

ይህ በፓርቲ አባሎቻቸው ላይ የተፈጸመ እስራት በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ውስጥ የሚገኙ ፓርቲዎችን ለማዳከም የተደረገ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ ይህ ዕርምጃ የሕግ የበላይነትን የሚጥስ እንደሆነ በመጥቀስም ‹‹የአገሪቱን የፖለቲካ ችግርን ቢቻል በበሰለ የፖለቲካ ውይይትና ድርድር ለመፍታት ጥረት ቢደረግ›› እንደሚበጅ ገልጸዋል፡፡

ከሰሞኑ አንድ አባሉ እንደታሰረበት የተናገረው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ፓርቲ፣ ወ/ሮ ሰላማዊት አጎናፍር የተባሉና በአዲስ አበባ በምርጫ ወረዳ 17 ውስጥ የምርጫ ክልሉ የኢዜማ ሴቶች ጉዳይ ተጠሪ የነበሩ አባሉ መታሰራቸውን አረጋግጧል፡፡

የኢዜማ የሕግና የአባላት ደኅንነት ጉዳይ መምሪያ ኃላፊው አቶ ስዩም መንገሻ ለሪፖርተር እንዳረጋገጡት፣ ‹‹ወ/ሮ ሰላማዊት ኅዳር 25 ቀን 2016 ዓ.ም. ነው በቁጥጥር ሥር የዋሉት›› ብለዋል፡፡ በኢዜማ አሠራር መሠረት አባላት ሲታሰሩና አደጋ ሲደርስባቸው ቅፅ ተሞልቶ እርሳቸው ለሚመሩት መምሪያ እንደሚመጣና የታሰሩት ሰው ማንነት ተጣርቶ ሪፖርት እንደሚደረግ አመልክተዋል፡፡ በዚህም መሠረት እስካሁን ወ/ሮ ሰላማዊት ብቻ መያዛቸውን አቶ ስዩም ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...