Monday, February 26, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ሸገር ከተማ በሁለት ወር ውስጥ ስድስት ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ

ተዛማጅ ፅሁፎች

በአዲስ አበባ ዙሪያ ከአንድ ዓመት በፊት የተመሠረተው ሸገር ከተማ አስተዳደር፣ በ2016 ዓ.ም. ሩብ የበጀት ዓመት 25 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ፣ የሩብ ዓመቱ ሳይደርስ ስድስት ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

ሸገር ከተማ ከመቆርቆሩ ቀደም ብሎ ከሰባት ቢሊዮን ብር ያልበለጠ ገቢ ይሰበስብ እንደነበር የተናገሩት የሸገር ከተማ ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ከንቲባው ይህንን የተናገሩት ከኢትዮ ቴሌኮም የዲጂታል መሠረተ ልማቶችን ለማቅረብ የሚያስችል፣ ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል መንግሥትና ከሸገር ከተማ ጋር ኅዳር 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ስምምነት ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡

በተለምዶ አንዱ አካባቢ ከተማ ሥር ከሆነ ተጠቃሚ ነበር፤›› ያሉት ተሾመ (ዶ/ር) ነገር ግን ሸገር ከተማ በአዲስ አበባ ሥር መሆኗ እንድትጎዳ አድርጓት ቆይቷል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዕድገት አካባቢው ያሉትን ከተሞች ከማሳደግ ይልቅ ማጨናነቅ እንደነበር አንስተው፣ የነበሩ ችግሮችን ቶሎ ለመፍታትና የሸገር ከተማን የበለጠ ለማዘመን ቴክኖሎጂን መጠቀም አስፈላጊ በመሆኑ፣ ከኢትዮ ቴሌ ጋር በጋራ ለመሥራት መስማማታቸውን አስታውቀዋል፡፡

ኦሮሚያ ክልልና ሸገር ከተማ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ያደረጉት ስምምነት መሠረታዊ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን የሚያስችሉ የዲጂታል መሠረተ ልማቶችን ተደራሽ ለማድረግ በእጅጉ አስፈላጊ ነው ተብሏል፡፡

በክልሉ የሚገኙ የወረዳና የቀበሌ አስተዳደር ያሉ የቢሮ ሥራዎች በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች በመታገዝ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችል የተገለጸ ሲሆን፣ በሸገር ከተማ በኩል ደግሞ በከተማው የሚደረጉ ማናቸውም እንቅስቃሴዎች እንዲሁም ወደ ከተማዋ የሚገቡና የሚወጡ እንቅስቃሴዎችን በካሜራ በመታገዝ ክትትል ለማድረግ እንደሚያስችል ተሾመ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ስምምነቱ የተደረገው በኦሮሚያ ክልል በኩል በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ መስከረም ደበበ እንዲሁም በሸገር ከተማ አስተዳደር በኩል የከተማዋ ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) እና የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ ጋር ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች