Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበሕገ መንግሥቱ የተደነገጉ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን በአግባቡ ያለመተግበር ችግር መኖሩ ተጠቆመ

በሕገ መንግሥቱ የተደነገጉ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን በአግባቡ ያለመተግበር ችግር መኖሩ ተጠቆመ

ቀን:

ሕገ መንግሥቱ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲሁም ለኅብረ ብሔራዊነት የፌዴራል ሥርዓቱ የግንባታ መሠረት የሆኑ ማዕቀፎችን ቢያስቀምጥም፣ በተገቢው መንገድ ሥራ ላይ ያለመዋል ችግር መኖሩ ተገለጸ፡፡

ለፌዴራል ሥርዓት ዋስትና የሆኑ ተቋማት በሚፈለገው ደረጃ አለማደግና ያለመዳበር ችግር የፌዴራል ሥርዓቱ በሚፈለገው መንገድ ተግባራዊ እንዳይሆንና የብሔረሰቦች አስተሳሰብና እሴቶች በተገቢው ሁኔታ እንዳይፈጸሙ ተግዳሮት መሆናቸውን፣ የፍትሕ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና ሪፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ ኤርሚያስ የማነ ብርሃን (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

ኅዳር 29 ቀን 2016 ዓ.ም. የተከበረውን የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ምክንያት በማድረግ የፍትሕ ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን ኅዳር 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ውይይት አካሂዷል፡፡ በውይይቱ ንግግር ያደረጉት ሚኒስትሩ በየደረጃው የሚያጋጥሙ ችግሮችን የፌዴራል ሥርዓቱ በሚፈቅደው አግባብ በንግግርና በውይይት የሚፈታበት ሥርዓት ደካማ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የመወያየትና የመነጋገር ባህል አለማጎልበት እንዲሁም የፌዴራል ሥርዓቱን ለሁሉም ችግሮች መፍትሔ ሰጭ አድርጎ መገንዘብ፣ ለፌዴራሊዝም ተግባራዊነት እንደ ትልቅ ችግር ተደርገው ሊወሰዱ የሚችሉ ጉዳዮች ናቸው ሲሉ ኤርሚያስ (ዶ/ር) አብራርተዋል፡፡

‹‹የሁሉም ችግሮች ምንጭ ፌዴራሊዝም ነው ብሎ መውሰድ ሌላኛው ተግዳሮት ነው፤›› ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፣ ከፌዴራል ሥርዓት የሚጠበቀውንና አጠቃላይ ፖለቲካዊ ባህላችን ከአስተዳደር ሥርዓት ተሞክሮ ጋር የማያያዝ ችግሮችን በትክክል ለይቶ አለመረዳት፣ እንዲሁም የረጅም ጊዜና የአጭር ጊዜ ችግሮችን ተቀራራቢ የሆነ አረዳድ አለመፍጠር ለኅብረ ብሔራዊና ፌዴራሊዝም ሥርዓት ግንባታ እንቅፋቶች ናቸው ተብሏል፡፡

ኅብረ ብሔራዊነትን የተላበሰ የፌዴራል ሥርዓት ግንባታ ትኩረትን ይፈልጋል ያሉት ኤርሚያስ (ዶ/ር)፣ የብሔር ማንነት ከአገራዊ ማንነት ጋር ተጣምሮ የሚታይበትን መንገድ መገንዘብን እንዲሁም የልማትና አቅምና ፍላጎትን አጣምሮ ማየት አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

የፍትሕ ሚኒስቴር በፌዴራሊዝምና በብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት ላይ ያተኮረ የመግባቢያ ሰነድ ያቀረበ ሲሆን፣ ቀደም ሲል የነበረው የፌዴራሊዝም ሥርዓት የብሔር ማንነት ላይ ብቻ ያጋደለና ሚዛኑን የሳተ እንደነበር ተመላክቷል፡፡

በቀጣይ የነበሩ ችግሮችን በመፍታት የትኩረት አቅጣጫ ሊሆኑ ይገባሉ የተባሉ ጉዳዮች በሰነዱ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

በብዝኃነትና በአገራዊ አንድነት ዙሪያ ሚዛንን መጠበቅ ኅብረ ብሔራዊነትን መሠረት ያደረገ አገራዊ አንድነት ለመገንባት እንደሚያስፈልግ በሰነዱ ላይ ተመላክቷል፡፡

አሃዳዊነትን ሙሉ በሙሉ በመቀበል ልዩነቶችን መዘንጋት እነዲሁም አሀዳዊነትን ሙሉ በሙሉ በመተው ብዝኃነት ላይ ብቻ ማተኮር የየራሳቸው ተግዳሮቶች ስለሚኖሯቸው፣ በልዩነት ሚዛን እያስጠበቁ መሄድ ለአገር ግንባታ መሠረታዊ ጉዳይ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ሰላምን ለመገንባት ብሔራዊ ፌዴራሊዝምን በተሟላ መንገድ ተግባራዊ ማድረግ እንደ መፍትሔ ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚገባና እንዲሁም የግጭቶችን ምክንያት ጠለቅ ብሎ መፈተሸ እንደሚያስፈልግ ተጠቅሷል፡፡

‹‹ልዩነቶች አለመግባባቶች እንዲሁም ያልተማመንባቸው ጉዳዮች ቢኖሩም፣ በመነጋገርና በመወያየት መፍታት ተገቢ ነው፤›› ያሉት ደግሞ በፍትሕ ሚኒስቴር የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሐሚድ ካኒሶ ናቸው፡፡

ችግሮችን ለመፍታት የመደማመጥ ችግር መኖሩን የጠቀሱት አቶ ሐሚድ፣ ‹‹የእኔ ትክክል ነው›› ተቀበሉ የሚለው ሐሳብ በፌዴራሊዝም ውስጥ አስቸጋሪ ነው ብለዋል፡፡

‹‹ብዝኃነትና እኩልነት ለአገራዊ አንድነት›› በሚል ለ18ኛ ጊዜ የሚከበረው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዓል ትናንት ኅዳር 29 ቀን 2016 ዓ.ም. በሱማሌ ክልል ጂግጂጋ ከተማ ተከብሯል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...