Sunday, March 3, 2024
Homeስፖንሰር የተደረጉየጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

Published on

- Advertisment -

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች 6ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤና 3ኛ  አስቸኳይ  ጠቅላላ ጉባኤ ቅዳሜ ታህሳስ 20 /2016 ዓ.ም ቀን ከጠዋቱ 2፡30 በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክ/ክተማ በኢሊሊ ኢንትርናሽናል ሆቴል አዳራሽ ስለሚካሄድ ባለአክሲዮኖች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተጠቀሰዉ ቀን፤ ሰዓትና ቦታ በስብሰባዉ ላይ እንዲገኙ የዳሬክተሮች ቦርድ ጥሪዉን ያቀርባል፡፡ የማህበሩ የተከፈለ ካፕታል 40,010,000.00 ሲሆን የማህበሩ የንግድ ምዝገባ ቁጥር NL/AA/3/0012632/200 ነዉ።

        የ3ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

 1. የጉባኤዉን አጀንዳ ማፅደቅ
 2. የጉባኤዉን ድምፅ ቆጣሪዎች መምረጥ
 3. የማህበሩ መመስረቻ ፅሁፍ በአዲሱ የንግድ ህግ 1243/2013 መሰረት ማሻሻል
 4. የማህበሩ መመስረቻ ፅሁፍ ዉስጥ አንቀፆችን ማሻሻል
 5. የጉባኤዉን ቃለ ጉባኤ ማፅደቅ

 

  የ6ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

 1. የጉባኤዉን ድምፅ ቆጣሪዎችን መሰየም፤
 2. የጉባኤዉን አጀንዳ ማፅደቅ ፤
 3. እስከ 6 መደበኛ ጉባኤ ድረስ የተከናወኑ የአክሲዮን ግዢና ዝዉዉርን በማፅደቅ አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበል፤
 4. እ.ኤ.አ የ2022/2023 የማህበሩን የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ረፖርት ማዳመጥ፣ መወያየት፣
 5. የውጪ ኦዲተሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ለጠቅላላ ጉባኤ ያቀረበውን ሪፖርት በተመለከተ ለጠቅላላ ጉባኤው አሰተያየት እንዲሰጥ በማድረግ ጉባኤው እንዲያፀድቀው መጠየቅ
 6. እ.ኤ.አ የ2022/2023 የውጭ ኦዲተሮችን ሪፖርት ፣ የሀብትና እዳ ሚዛን እና ትርፍና ኪሳራ መግለጫ ማዳመጥ ፣ መወያየት እና ማፅደቅ ፣
 7. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት እ.ኤ.አ የ2023/2024 አመታዊ የድካም ዋጋ መወሰን፤ 
 8. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ምርጫ ማከናወን ፣
 9. የጠቅላላ ጉባኤዉን ቃለ ጉባኤ ማፅደቅ

ማሳሰቢያ

በጉባኤው ላይ በአካል መገኘት ለማትችሉ ባለአክሲዮኖቸ ከስብሰባው እለት ሶስት ቀናት በፊት መካኒሳ ኤስ ሳራ ህንፃ ስድስተኛ ፎቅ በሚገኘዉ በዋናዉ መ/ቤት በመቅረብ ማህበሩ ባዘጋጀው የውክልና ቅጽ ላይ በመሙላት ተወካዮቻችሁን ማሳተፍ ትችላላችሁ ወይም ተወካዮቻችሁ አግባብ ካለው የፌዴራል ወይም የክልል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የተሰጠ በስብሰባ ለመሳተፍና ድምፅ ለመስጠት የሚያስችል የውክልና ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ከፒውን ይዘው በመቅረብ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እናስታውቃለን፡፡

ባለአክሲዮኖችም ሆናችሁ ወኪሎች ወደ ስብሰባው ቦታ ስትመጡ ማንነታችሁን የሚያረጋግጥ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ይዛችሁ እንድትቀርቡ፤ እንዲሁም ተወካዮች የወካያችሁን ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ  መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ በተጨማሪ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡

ሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ

የዲሬክተሮች ቦርድ

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር  011 36 98441/09 75 07 05 03/09 75 06 49 03 ይጠቀሙ

የቅርብ ጊዜ መጣጥፎች

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ የሚይዙትና በተለምዶ ‹‹ሚኒባስ›› የሚባሉ ታክሲዎች...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ ማግሥት ጀምሮ እንደሆነ በርካታ የታሪክ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣ በንግድ ምክር ቤቱ ታይተዋል የተባሉ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች...

ተመሳሳይ

የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት እንቅስቃሴ በፋው የቤስቲዩን ኢ05 ናት (BESTUNE E05) የኤሌክትሪክ መኪና ይቀላቀሉ

በኢትዮጵያ የትራንስፖርትና የኤሌክትሪክ ዘርፍ በመሰማራ ቀዳሚው የንግድና የአቅርቦት አጋር ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ ኃላፊነቱ የተወሰነ...

የ ጃሲሪ ታለንት ኢንቬስተር ፕሮግራም 6ኛ ዙር ማመልከቻ | ጋዜጣዊ መግለጫ | ጥር 6, 2016 ዓ.ም

ጋዜጣዊ መግለጫ | ጥር 6, 2016 ዓ.ም ማስታወቂያ የ ጃሲሪ ታለንት ኢንቬስተር ፕሮግራም 6ኛ ዙር ማመልከቻ 6ኛው ዙር የ ጃሲሪ ታለንት ኢንቬስተር ፕሮግራም ማመልከቻ አሁን ተጀምሯል። ጃሲሪ...

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና ላለፉት አመታት ዘመናዊ እና ጥራት...