Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

‹‹ሠራተኛ ስቀጥር ካለመሠልጠናቸውም በላይ ስንት ይከፈለኛል ብለው ሲጠይቁ እደነግጥ ነበር›› ወ/ሮ ቅድስት ጌታቸው፣ የሶጋ ትሬዲንግና ፖላር ፕላስ ኤክሰለንስ ሀብ መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ

በኢትዮጵያ የሚገኙ ቀጣሪ ድርጅቶች የሚፈልጉት የሠለጠነ የሰው ኃይልና የሥ ፈላጊው ብቃት በብዛት አይጣጣምም፡፡ በዚህም ቀጣሪዎች ብቁ የሰው ኃይል አለማግኘታቸውን፣ ሠራተኞችም የሚፈልጉትን የሥራ ዓይነት አጥተው ሥራ አጥ መሆናቸውን ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡ ክፍተቱን አጠበዋለሁ በሚልሳቤ የተመሠረተው ፖላር ፕላስ ኤክሰለንስ ሀብዘመናዊ የሥልጠና፣ የምርምርና የማማከር ማዕከል ገንብቶ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡ የጎልደን ቴስቲ ሶያ ምርትን በማሠራጨት የሚታወቀው ሶጋ ትሬዲንግ መሥራችና ሥራ አስኪያጅ በሆኑት / ቅድስት ጌታቸው የተመሠረተው ማዕከል፣ የተለያዩ አጫጭር ሥልጠናዎችን፣ የጥናትና ምርምር አገልግሎትን እንዲሁም በተለያየ የሥራ ዘርፍ ለተሰማሩና ለመሠማራትዝግጅት ለሚገኙ ግለሰቦችና ተቋማት የማማከርና የገበያ ጥናት ይሠራል፡፡ፖላር ፕላስ ኤክሰለንስ ሀብ መሥራችና በንግድለም ከአሥርመታት በላይ ልምድላቸውን / ቅድስት፣ በሚመሩት ድርጅቶች የሥራ እንቅስቃሴ ዙሪያ ሰላማዊት መንገሻ አነጋግራቸዋለች፡፡

‹‹ሠራተኛ ስቀጥር ካለመሠልጠናቸውም በላይ ስንት ይከፈለኛል ብለው ሲጠይቁ እደነግጥ ነበር›› ወ/ሮ ቅድስት ጌታቸው፣ የሶጋ ትሬዲንግና ፖላር ፕላስ ኤክሰለንስ ሀብ መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

ሪፖርተር፡- የንግድ ሥራን እንዴት ጀመሩት?

ወ/ሮ ቅድስት፡- በንግድ ዓለም አሥር ዓመታት ያህል ቆይቻለው፡፡ የንግድ ሥራ የጀመርኩት 2006 ዓ.ም. ነው፡፡ ከዚያ በፊት በተለያዩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ ሠርቻለሁ፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የንግድ ሥራ ትምህርት ቤት በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን የመጀመሪያ ዲግሪና በተለያዩ ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ዘርፍ በተለያዩ ጊዜያት ተምሬያለሁ፡፡ ቤተሰቦቼ ነጋዴዎች ነበሩ፡፡ ቤታችን ውስጥ ስለንግድ እየሰማን ስላደግን ወደ ንግድ ለመግባት አልከበደኝም ነበር፡፡ ቤተሰቦቼ በጣም ሥራ ይወዱ ስለነበር ደከመኝ አያውቁም፡፡ የእነሱ ጥንካሬ ተፅዕኖ ፈጥሮብኛል፡፡ ክህሎት ያስፈልገኝ ስለነበር ትንሽ ጊዜ ተቀጥሬ መሥራት ነበረብኝ፡፡ አንድ ቦታ ስቀጠር የተለያዩ ሥራዎች በጎን እሠራ ነበር፡፡ አካውንታንት፣ ማርኬቲንግ (ሴልስ) እና የጉምሩክ ሥራዎች፣ እሠራ ነበር፡፡ ማረፍ አልፈልግም ነበር፡፡ በፊት የምሠራውን ያህል አሁን ለራሴ ድርጅት ሠርቻለው ብዬ አላስብም፡፡ ቢሮ ጠዋት 1፡00 ሰዓት ገብቼ ማታ 3፡00 ሰዓት እወጣለው፡፡ በወቅቱ ስለክፍያ እያሰብኩ፣ ድርጅቱን ለማስደስት ወይም የትርፍ ሰዓት እንዲከፈለኝ ሳይሆን ሥራውን ለመልመድ ብቻ ነበር የምሠራው፡፡

ሪፖርተር፡- የመጀመሪያውን ንግድ በምን ጀመሩ?

ወ/ሮ ቅድስት፡- የተሻለ ደመወዝ ያለው ሥራ እየሠራሁ ስለነበር ወደ ቢዝነስ ስገባ ቤተሰቦቼ ለስድስት ወራት ያህል አያውቁም ነበር፡፡ የአብዛኛው ቤተሰብ ፍላጎት ተምሮ ተመርቆ በጥሩ ደመወዝ ሥራ መያዝ ነው፡፡ ቢዝነስ ልጀምር ብዬ ስጠይቅ ‹ምን አውቃው ነው› ይላሉ፡፡ ሥራ የጀመርኩት ከአንድ ድርጅት ጋር በመዋዋል ምርታቸውን በማሠራጨት ነው፡፡ ምርቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ሲገባ አዲስ ነበር፡፡ ያልተለመደ ስለሆነ በጣም አስቸጋሪ ነበር፡፡ ጎልደን ቴስቲ ሶያ ይባላል፡፡ ከእንዲህ ዓይነት ትልቅ ድርጅት ጋር ስምምነት ሲፈጸም፣ የራሱ የሆነ መሥፈርት ነበረው፡፡ አዲስ ነገር ስለሆነ በጣም ፈታኝ ነበር፡፡ ምርቱ ኢትዮጵያ ውስጥና ሌሎች ዓለማት ያለውን ልምዶች በማጥናት ሥራውን ጀመርኩ፡፡ ምርቱን ለማስተዋወቅ እንዲያግዘኝ በክልሎች በርካታ አካባቢዎች እየሄድኩ ሰዎች ተዋወቅኩኝ፡፡ የዛሬ አሥር ዓመታት የለፋሁበት ሥራ አሁንም ድረስ አብሮኝ ቆይቷል፡፡ ንግድ በዋናነት የሚያስፈልገው እምነት ነው፡፡ ምንም ምርት በእምነት ነው የሚሸጠው፡፡ አባቴ ተመርቄ እንደወጣሁ መንቀሳቀሻ የሚሆን ቪታራ መኪና ተሰጥቶኝ ነበር፡፡ በዚህ ቪታራ ነበር ምርቶቹን እየዞርኩ ማሻሻጥ የጀመርኩት፡፡ በወቅቱ ትርፍ ሳገኝ ቅንጡ ሕይወት ለመኖር ብፈልግ እዚህ ደረጃ አልደርስም ነበር፡፡ ጥሩ ሕይወት መኖር አልወድም ማለት አይደለም፡፡ ግን ለመቀናጣትና ለታይታ የሆነ ነገር አልፈልግም፡፡

ሪፖርተር፡ ፖላር ኤክሰለንስ ሀብን ለምን መክፈት አሰቡ?

ወ/ሮ ቅድስት፡- ከቢዝነስ የመጣ ሰው የሥልጠና ተቋም መክፈት የማይታሰብ ነበር፡፡ ፖላር ፕላስን ስጀምር መጀመሪያ ምን ምን እንደሚያስፈልገኝ ጥናት ሠርቼ ነበር፡፡ በሶጋ ትሬዲንግ በተለያየ ጊዜ ሠራተኞችን እቀጥራለሁ፡፡ በዚህ ወቅት ትልቁ የተቸገርኩት ሰው ስቀጠር የሠለጠኑ ካለመሆናቸውም በላይ ገና ሥራውን ሳይጀምሩና ሳያውቁት ‹‹ምን ያህል ነው የሚከፈለን› የሚለው ነበር፡፡ ስለሥራው ሳያውቁ ስንት ነው የምትከፍሉኝ ሲሉኝ እደነግጥ ነበር፡፡ ለሶጋ ትሬዲንግ ትልቁ ስኬት ጥሩ የሥራ ባልደረቦቼ ናቸው፡፡ የሠራተኞቹን የቡድን ሥራ ለሌሎች ድርጅቶች ማጋራት ፈለግኩኝ፡፡ በተለያዩ መሥሪያ ቤት፣ ሕክምና ቦታ፣ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሠራተኞች አገልግሎት አሰጣጥ አርኪ አይደለም፡፡ ጉዳይ ለማስፈጸም የገባሽበት ቢሮ ባለ ጉዳይ አስቀምጠው ፀሐይ ሲሞቁ ታያለሽ፡፡ የባለጉዳይ መንገላታት ምንም አይመስላቸውም፡፡ በተጨማሪም በሆቴልና ሆስፒታሊቲ ዘርፍ ሠራተኞች እንደ ቀድሞ ባህላችን ሰውን ማክበር ትተዋል፡፡ የውጭ አገር ልምድን ስመለከት በኢትዮጵያ ሥልጠና የወሰዱ ሠራተኞችን ማብቃት ያስፈልጋል ብዬ ተነሳሁ፡፡ የሠለጠነ ባለሙያ፣ ጠንካራና የእኔ ድርጅት የሚል ስሜት ያለው ሠራተኛ ማብቃት ስለምፈልግ አማካሪ ቀጥሬ ነበር፡፡ ከአማካሪዬ ጋር የተሳካ ቢዝነስ ፕላን አወጣን፣ ሥራው ተጀመረ፡፡ ሥልጠናዎቹ በአምስት ዘርፎች የተከፋፈሉና በውስጡ 96 አጭር የሥልጠና ኮርሶችን የያዘ ነው፡፡ አካውንቲንግ፣ ማርኬቲንግ፣ የሰው ኃይል ማኔጅመንት፣ ሥነ አመራርና ስትራቴጂካዊ እንዲሁም የሆቴልና ሆስፒታሊቲ ዘርፍ ከሥልጠናዎቹ ይገኙበታል፡፡ ሥልጠናው በአገር ውስጥና በውጭ አገሮች የማሠልጠን ልምድና ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች 70 በመቶ በተግባር፣ 30 በመቶ በንድፈ ሐሳብ ይሰጣል፡፡ ለመንግሥታዊና መንግሥታዊ ላልሆኑና ለግል ድርጅቶች ብቁ የሰው ኃይል አሠልጥነን እናቀርባለን፡፡ ከታች ያሉ ሠራተኖች ጋር ብቻ ሳይሆን ትልልቅ የሥራ ኃላፊነት ቦታ ላይ ባሉ ሰዎችም ችግር ሊኖር ስለሚችል ኃላፊዎች መሠልጠን አለባቸው፡፡ በዚህም በቅርቡ የሚዘጋጅ ያንግ ሲኢኦ ፎረም ዋይኤስኤፍ ከሚባል የማማከር የሥልጠና ድርጅት ጋር ለመሥራት አስበናል፡፡ ፎረሙ ወጣት ዋና የሥራ አስፈጻሚ ወይም ሥራ አስኪያጆች ሥራቸውን ከሕይወት ጋር አቻችለው መሥራት አለባቸው በሚል የሚሠራ ይሆናል፡፡ ከሥራ አመራርነት ውጪ የቤተሰብ፣ የሥራና የሕይወት ጉዞ እንዴት ተቻችሎ ይጓዛል፣ መንፈሳዊና ዓለማዊ ሕይወታቸው እንዴት መስተካከል አለበት የሚለው ላይ ያተኩራል፡፡ ሥልጠናው ቀድመው እንዲዘጋጁ የሚያደርግ ነው፡፡ ሶጋ ትሬዲንግን በ43 ሺሕ ብር መነሻ ካፒታል ጀምሬው በአሁኑ ወቅት ትልቁ የገቢ ምንጭ ሆኖልኛል፡፡ በአጠቃላይ 15 ቋሚና በርካታ ኮንትራት ሠራተኞች አሉት፡፡ የአሁኑ ድርጅቴ ሶላር ኤክሰለንስ ሀብ በ30 ሚሊዮን ብር የተመሠረተ ሲሆን፣ 30 ሠራተኖች አሉት፡፡ በ43 ሺሕ ብር የጀመርኩት ድርጅት አሁን ለደረስኩበት የ30 ሚሊዮን ብር ድርጅት አስተዋጽኦ አለው፡፡

ሪፖርተር፡- በሥራዎ ምን ችግር ገጠመዎት?

ወ/ሮ ቅድስት፡- ፖላር ፕላስ ድርጅትን ስጀምር ሦስተኛ ልጄን ወልጄ የሁለት ወር አራስ ነበርኩ፡፡ ድርጅቱን ሳቋቁም ለቤተሰቤ መስጠት የነበረብኝን ጊዜ ወስዶብኛል፡፡ አሁን በተወሰነ መንገድ መስመር እያየዘ ስለሆነ ወደ ቤተሰብ ደግሞ ትኩረት እያደረኩ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ምን ዓይነት የበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ ይሳተፋሉ?

ወ/ሮ ቅድስት፡- በሜልቪን ጆንስ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቋቋመው፣ በኢትዮጵያ ደግሞ ከ58 ዓመታት በፊት የተመሠረተው ላየንስ ክለብ ኢትዮጵያ ውስጥ ላለፉት ስምንት ዓመታት ሠርቻለሁ፡፡ እንደ አንዱ ድርጅቴ አየዋለሁ፡፡ አሁን ላየንስ ክለብ አዲስ አበባ ሆስት ለሚባል ክለብ ፕሬዚዳንት ነኝ፡፡ ድርጅቱ ጊዜና ጥሩ ልብ ብቻ ነው የሚፈልገው፡፡ በተጨማሪም በግል የምሠራቸው በጎ አድራጎት አሉ፡፡ ከንፈር ከመምጠጥ የቻልኩትን ያህል አደርጋለሁ፡፡

ሪፖርተር፡- የወደፊትቅድዎ ምንድነው?

ወ/ሮ ቅድስት፡- ፖላር ፖላስን ትልቅ ደረጃ ደርሶ ማየት፣ በክልሎች ቅርንጫፍ መክፈት ነው፡፡ ኬንያን ብናይ ከ200 በላይ የሥልጠና ማዕከላት አሉ፡፡ እኛም ማሳደግና ማስፋፋት አለብን፡፡ በተጨማሪም የስቶክ ማርኬት ሥልጠና ለመስጠት ዝግጅት እያደረኩ ነው፡፡ ወደፊት የራሴን ፋብሪካ ለመክፈት ዝግጅት ላይ ነኝ፡፡  

ተዛማጅ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች ለማግኘት

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

ተዛማጅ ፅሁፎች

ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እስከ ግለሰቦች የሚደርሰው ወገን ፈንድ

ወገን ቴክኖሎጂ ሶሉሽንስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ ሕጋዊ ዕውቅና በማግኘት ከኢትዮጵያና ከተለያዩ አገሮች ልገሳን ለማሰባሰብ ‹‹ወገን ፈንድ›› የሚባል የበይነ መረብ (ኦንላይን) የድጋፍ ማሰባሰቢያ ድረ...

ግዴታን መሠረት ያደረገ የጤና መድኅን ሥርዓት

የኢትዮጵያ ጤና መድኅን ተቋቁሞ ወደ ሥራ ከገባ ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ ማኅበረሰብ አቀፍና የማኅበራዊ ጤና መድኅን ሥርዓቶችን መሠረት አድርጎም ይሠራል፡፡ የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን ሥርዓት በኢመደበኛ...

የመሠረተ ልማት ተደራሽነት የሚፈልገው የግብርና ትራንስፎርሜሽን

የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ተቋም አርሶ አደሩን የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ በማድረግ የግብርና ክፍለ ኢኮኖሚውን የማሳደግ ዓላማ ይዞ የተመሠረተ ነው፡፡ ተቋሙ የግብርናውን ዘርፍ ሊያሳድጉ የሚችሉ ጥናቶችን...