Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምበኮፕ 28 ትኩረት ያገኘው የጤና አጀንዳ

በኮፕ 28 ትኩረት ያገኘው የጤና አጀንዳ

ቀን:

የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖውን በመላ ዓለም እያሳረፈ ይገኛል፡፡ በተለይ በማደግ ላይ ያሉና ለአየር ንብረት ለውጥ መከሰት ኢምንት አስተዋጽኦ ያላቸው አገሮች የችግሩ ሰለባ ሆነዋል፡፡

ኢኮኖሚያቸው ባላደገበትና የፖለቲካ አለመረጋጋቶችን ባልፈቱት አገሮች ድርቅ፣ ጎርፍና አውሎነፋስ ታክሎበት በሚሊዮን የሚቆጠሩ እንዲራቡና ከቀዬአቸው እንዲፈናቀሉም እያደረገ ነው፡፡

በኢንዱስትሪ የቱንም ያህል ያልተጓዙት ከሰሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አገሮች ደግሞ ይበልጥ ለችግሩ ተጋላጭ ሆነዋል፡፡ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የሚያስችል የኢኮኖሚ ደረጃ ላይም አልደረሱም፡፡ ይህም ሕዝባቸውን ለማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ቀውስ ዳርጓል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በኮፕ 28 ትኩረት ያገኘው የጤና አጀንዳ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
በዱባይ የተካሄደው ኮፕ 28 በኮፕ ታሪክ የመጀመርያ የሆነውን ‹‹የጤና ቀን›› አስተዋውቋል

 

ዛሬም ከሰሃራ በታች የሚገኙ አገሮች በተለይም በአፍሪካ ቀንድ ያሉት በድርቅ እየተጠቁ ነው፡፡ ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ፣ በመሬት መንሸራተትና በጎርፍ ኑሮዋቸው እየተመሰቃቀለ ነው፡፡

በኢንዱስትሪ የበለፀጉ አገሮች በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የሚጎዱ አገሮችን ለመደገፍ ቃል የገቡትን ገንዘብ ሙሉ ለሙሉ ተደራሽ አለማድረጋቸውም አገሮቹ ከችግራቸው እንዳያገግሙ አድርጓል፡፡ ሕዝባቸውን ለጤና ቀውስም እየዳረገ ነው፡፡

ዘንድሮ በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የተካሄደው የኮፕ 28 ጉባዔ ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ የአየር ንብረት ለውጥ በጤናው ዘርፍ እያደረሰ ያለው ችግር ላይ መክሯል፡፡

በኮፕ ታሪክ የጤና ዘርፍ የተለየ ትኩረት ሲያገኝ የመጀመርያው ሲሆን፣ እንዲሁ የመጣም አይደለም፡፡  በዓለም በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ድርቅ፣ ጎርፍ፣ አውሎ ነፋስና መፈናቅል በመከሰቱና የጤና ቀውሱም ዓለም አቀፍ ጫና በመፍጠሩ ነው፡፡

በዱባዩ የኮፕ 28 ጉባዔ ሐሳቡን ያጋራው የዓለም ጤና ድርጅት፣ ከ40 ሚሊዮን በላይ የጤና ባለሙያዎች የአየር ንብረት ለውጡ በጤናው ዘርፍ እያስከተለ ላለው ቀውስ ጉባዔው ዕርምጃ እንዲወስድ መጠየቃቸውን ገልጿል፡፡

በኮፕ ታሪክ የመጀመርያ ነው በተባለው ‹‹የኮፕ የጤና ቀን›› የዓለም ጤና ድርጅት ባደረገው ጥሪ መሠረት የተሰባሰቡ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችና የጤና ባለሙያዎች፣ የአየር ንብረት ለውጥ በጤናው ዘርፍ እያደረሰ ያለውን ችግር ለመፍታት የኮፕ 28 ጉባዔ የጤና ጉዳይን ቅድሚያ ሰጥቶ ስምምነት ላይ እንዲደርስ ጠይቀዋል፡፡

የአየር ንብረት ለውጡ በየቀኑ የሰዎችን ሕይወት እየቀጠፈ መሆኑን፣ በዚህም የጤና ባለሙያዎች ለአየር ንብረት ለውጡ ትልቁን አስተዋጽኦ እያደረገ የሚገኘውን ድንጋይ ከሰል ከጥቅም እንዲወጣ እንዲሁም ንፁህ የኃይል አማራጭ እንዲተገበር፣ አየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም ኢኮኖሚ እንዲገነባና በአየር ንብረት ለውጡ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች ዕገዛ እንዲደረግላቸው አሳስበዋል፡፡ ‹‹ጊዜ መውሰድ አያስፈልግም፣ ተጨማሪ ማስተባበያ/ይቅርታም አያስፈልግም፣ ወደፊት ጤናማ ማኅበረሰብ ለመፍጠር አሁኑኑ ዕርምጃ መወሰድ አለበት፤›› ሲሉም በድርጅቱ በኩል አቋማቸውን ገልጸዋል፡፡

የድርጅቱ ዋና ጸሐፊ ቴድሮስ አድኃኖም (ዶ/ር) እንዳሉት፣ የሕክምና ባለሙያዎች በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ በዘርፉና በማኅበረሰቡ ላይ እያጋጠሙ የሚገኙ ችግሮችን በመቋቋም ምላሽ ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡

የአውሮፓውያኑ 2023 የአየር ንብረት ለውጡ ያስከተለው ውድመት በግልጽ የታየበት፣ የጫካ ሰደድ እሳት፣ ከመጠን ያለፈ ሙቀት/በረሃማነት፣ ድርቅ ያስከተለው መፈናቀል፣ የግብርና ምርታማነት መቀነስና የአየር ብክለት ለጤናው ቀውስ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውንም አክለዋል፡፡

የአየር ንብረት ለውጡም ኮሌራ፣ ወባና ደንጉ በሽታዎች በሰው ልጅ በጤና የመኖር መብት ላይ አደጋ እንዲጥሉ አድርጓል ብለዋል፡፡

የማኅበረሰቡን ጤና ለመጠበቅ ጠንካራና ችግሮችን የሚቋቋም የጤና ሥርዓት እንደሚያስፈልግ፣ የአየር ንብረት ለውጥ የሚቋቋምና ዝቅተኛ የካርቦን ልቀት ያለበት የጤና ሥርዓት መዘርጋት፣ የአሁንና የወደፊት ሕይወትን ለመጠበቅ ስለሚያስችል፣ በአካባቢያዊ፣ አገራዊና ዓለም አቀፋዊ ደረጃ ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባና የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያስፈልገውም አሳስበዋል፡፡

በኮፕ 28 የተሰባሰቡ የጤና ሚኒስትሮች፣ የአየር ንብረትና ጤና የኮፕ 28 ሰነድን መፈራረማቸውንና በ120 አገሮች ድጋፍ እንዳገኘም ገልጸዋል፡፡

አሁን የጤናው ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ከሚለገሰው ገንዘብ የአምስት በመቶ ድርሻ ብቻ እንዳለው፣ ሆኖም ዘርፉ ቀጣይነት ያለው ተጨማሪ ገንዘብ እንደሚፈልግም ተጠቁሟል፡፡

‹‹የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ የጤናውም ቀውስ ነው›› ያለው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ)፣ ከሦስት ቢሊዮን በላይ የዓለም ሕዝብ ለአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ በሆኑ ሥፍራዎች ውስጥ እየኖሩ መሆኑን አመልክቷል፡፡

እ.ኤ.አ. ከ2030 እስከ 2050 ባለው ጊዜ ውስጥ የአየር ንብረት ለውጥ በየዓመቱ በአሥር ሺዎች የሚቆጠር ጨማሪ ሞት እንደሚያስከትልና የዓለም ጤና ድርጅት የሚመራው ዓለም አቀፍ ፕላትፎርም ችግሩን ለመቅረፍ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደሚሠራ አስታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...