Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊወጣቶች የክህሎት ሥልጠና የሚያገኙበት ‹‹የኔ ፕሮዳክት›› ይፋ ሆነ

ወጣቶች የክህሎት ሥልጠና የሚያገኙበት ‹‹የኔ ፕሮዳክት›› ይፋ ሆነ

ቀን:

ሰዎች ማንነታቸውን አውቀው የትምህርት ዘርፍ እንዲመርጡ የሚያስችል ‹‹የኔ ፕሮዳክት›› የተባለ አራት ሺሕ ዓይነት የክህሎት ሥልጠናዎች የሚገኝበት የበይነ መረብ የሥልጠና ሥርዓት ይፋ ሆነ፡፡

ብሬክስሩ ትሬዲንግ አክሲዮን ማኅበር ፕሮጀክቱን ይፋ ሲያደርግ እንዳስታወቀው፣ ‹‹የኔ ፕሮዳክት›› በተለይም ከዘጠነኛ ክፍል በላይ ያሉ ተማሪዎችና ማንኛውም ሰው የሰብዕናውን ዓይነት (ፐርሰናሊቲ ታይፕ) በማወቅ፣ በየትኛው የትምህርትና ክህሎት ዘርፍ ቢማርና ቢሠለጥን ውጤታማ መሆን ይችላል የሚለውን ለማወቅ የሚረዳ ነው፡፡

የብሬክስሩ ትሬዲንግ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ነፃነት ዘነበ፣ ኩባንያቸውና የኬንያው ጆብ ክሬሽን ከደቡብ አፍሪካው የንዛ ያገኙትን ልምድ ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት በሁለተኛ ደረጃ ውስጥ ያሉ ተማሪዎች ማንነታቸውን እንዲያውቁ፣ ምን ዓይነት ትምህርትና ሥራ መምረጥ እንዳለባቸው እንዲረዱና ክህሎት እንዲያዳብሩ የሚያግዝ ሥርዓት መዘርጋታቸውን አክለዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ሥርዓቱ በአማርኛ፣ በእንግሊዝኛና በኦሮምኛ የተዘጋጀ ሲሆን፣ በተቻለ መጠንም የኢትዮጵያን ባህልና አኗኗር የሚመጥን ለማድረግ ተሞክሯል ብለዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በራሱ መደበኛ ትምህርት ሳይሆን ተማሪዎች የትምህርት ምርጫቸውን ባላቸው ዕውቀት ልክ እንዲመርጡ የሚያስችል መሆኑንም አክለዋል፡፡

ትልቁ ነገር ራሳቸውን አውቀው ትምህርትና የሥራ ዘርፋቸውን እንዲመርጡ ማስቻል ነው የሚሉት አቶ ነፃነት፣ ሰዎች በክህሎታቸው ተሰማርተው ሥራ አጥነትን እንዲቀርፉና ደስተኛ ሆነው እንዲሠሩ ያግዛል ብለዋል፡፡

ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በአሁኑ ሰዓት የወደፊት የትምህርት ዘርፍና የሙያ ክህሎት ግንባታ ላይ ሊያግዛቸው የሚችል አገልግሎት የለም ማለት ይቻላል ያሉት አቶ ነፃነት፣ በዚህም ምክንያት ብዙ ተማሪዎች ምን ዓይነት ሰብዕና እንዳላቸው ሳይንሳዊ በሆነ ዘዴ እንደማያውቁ፣ ምን ዓይነት የሥራ ባህሪ በተፈጥሮ እንዳላቸው እንደማይገነዘቡ፣ ይህም ትምህርታቸው ውጤት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚፈጥር፣ ተምረው ከተመረቁ በኋላም እንደ አገር የጊዜ፣ የዕውቀትና የገንዘብ ብክነት እንደሚያመጣ ገልጸዋል፡፡

ከጥቂቶች በስተቀር ብዙዎች ‹‹ዕድሜህ ወደኋላ ተመልሶ ድጋሚ ኮሌጅ ገብተህ የመማር ዕድል ቢኖርህ የምትማረው ትምህርት ምን ይሆን ነበር?›› ለሚለው ጥያቄ የተለየ የትምህርት ዘርፍ እንደሚፈልጉ፣ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ላይ ያሉ ወጣቶች ይህ ችግር እንዳይገጥማቸው የእኔ ትልቅ መፍትሔ ሊሆናቸው እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

እንደ አቶ ነፃነት፣ የእኔ በዓለም አቀፍ ደረጃና በአገር ውስጥ ባሉ ኩባንያዎች ውስጥ ተቀጥሮ የመሥራት ብቃትን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የሚያጠናክር የበይነመረብ አጋር መሣሪያ ነው፡፡

የኔ ፕሮዳክት ከዘጠነኛ ክፍል ጀምሮ ላሉ ተማሪዎች ብቻ ሳይሆን፣ ለማንኛውም ሰው በሳይንሳዊ ዘዴ የሰብዕናቸውን ዓይነት (ፐርሰናሊቲ ታይፕ) እና ምን ዓይነት ሠራተኛ እንደሆኑ ለመለየት በሆላንድ ኮድ በመጠቀም የሚያሳውቅ አጋዥ ቴክኖሎጂ ሲሆን፣ ተማሪዎች ስኮላርሺፖችን፣ የተለያዩ የኮሌጆችንና የዩኒቨርሲቲዎችን መረጃዎችን በየኔ ኦንላይን መድረክ ላይ ለማግኘት ያስችላል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...