Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበአዲስ አበባ የሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎች 80 በመቶ ተጎጂዎች እግረኞች መሆናቸውን የሚገልጽ ጥናት...

በአዲስ አበባ የሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎች 80 በመቶ ተጎጂዎች እግረኞች መሆናቸውን የሚገልጽ ጥናት ይፋ ሆነ

ቀን:

በናርዶስ ዮሴፍ

በአዲስ አበባ ከተማ የሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎች 80 በመቶ ያህሉ በእግረኞች ላይ መሆናቸውን የሚገልጽ ጥናት ይፋ ተደረገ፡፡

ጥናቱ ይፋ የተደረገው ማክሰኞ ኅዳር 25 ቀን 2016 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን፣ ከፍጥነት ወሰን በላይ በማሽከርከር የሚደርሱ አደጋዎችን ለመቀነስ ለስድስት ወራት የሚካሄድ የሥራ ዕቅዱን ባስተዋወቀበት መርሐ ግብር ላይ ነው፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የባለሥልጣኑ አጋር የሆነው ብሉምበርግ ፊላንትሮፒስ የመረጃ አስተባባሪ (surveillance Coordinator) ሜሮን ጌታቸው፣ በአዲስ አበባ ከተማ የተሽከርካሪ አደጋዎች ላይ የተደረገውን ጥናት አቅርበዋል።

በከተማዋ በተሽከርካሪ አደጋዎች ምክንያት ሕይወታቸው ያለፈ እግረኞች ቁጥር ባለፉት አሥር ዓመታት በየዓመቱ ከፍተኛው 400፣ እንዲሁም ዝቅተኛው 334 ሆኖ ከፍና ዝቅ እያለ በመቆየት በ2015 ዓ.ም. በአጠቃላይ በተሽከርካሪ አደጋዎች ከሞቱ 408 ሰዎች 350 ያህሉ እግረኞች መሆናቸውን በጥናቱ ተካቷል፡፡

ሕይወታቸው ካለፈ ግለሰቦች ውስጥ 77 በመቶ ወንዶች መሆናቸውን፣ ዕድሜያቸው ከ20 እስከ 39 ድረስ ያሉት ተጠቂዎች እንደሚበዙም በጥናቱ ተገልጿል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የተሽከርካሪ አደጋ የሚከሰተው ቅዳሜ ቀን በተለይም ከምሽት 12 እስከ ሁለት ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ መሆኑን፣ በዓመቱ ከደረሱ አደጋዎች 70 ያህሉ በዚህ ዕለት የተመዘገቡ ናቸው ተብሏል።

በሰዎች ላይ ሞት ያስከተሉ አደጋዎች በአብዛኛው የተከሰቱት በከባድ ተሽከርካሪዎች እንደሆነ፣ ከ12 እስከ 16 ሰዎች የጫኑ ታክሲዎች አውቶቡሶችን በማስከተል በጥናቱ ተዘርዝረዋል፡፡ በአውቶሞቢል የሚደርሱ አደጋዎች በ15 በመቶ ድርሻ አራተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ፣ በባቡር የደረሱ አደጋዎች ዝቅተኛውን አንድ በመቶ ድርሻ ብቻ በመያዝ በመጨረሻ ደረጃ ላይ ናቸው ተብለዋል፡፡

በጥናቱ በአዲስ አበባ ከፍተኛ የተሽከርካሪ አደጋ የሚከሰትባቸው ኮሪደሮችና ውስን አካባቢዎች ተመላክተዋል። ከአብነት እስከ ሰባተኛ፣ ከዊንጌት እስከ አጣና ተራ፣ ከባንቢስ እስከ ኡራኤል፣ እንዲሁም ከዘነበወርቅ እስከ አየር ጤና ያሉት ኮሪደሮች ዋና ዋና አደጋ የተመዘገበባቸው ኮሪደሮች መሆናቸው በጥናቱ ተለይተዋል፡፡

በሠፈሮች ደረጃ መገናኛ ተቀዳሚው የአደጋ ሥፍራ ነው የተባለ ሲሆን፣ አየር ጤና ቻይና ካምፕ የሚባለው አካባቢና ኃይሌ ጋርመንት በሁለተኛና በሦስተኛ ደረጃ ተቀምጠዋል።

ከፍተኛ የተሽከርካሪ አደጋ ሥፍራዎች ተብለው ከተዘረዘሩት ግማሽ የሚሆኑት፣ ከፍጥነት ወሰን በላይ ከማሽከርከር ጋር በተያያዘ የሚጠቀሱ ናቸውም ተብሏል።

የትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ክበበው ሚደቅሳ፣ የትራፊክ ምልክቶች የሚፈቀድ የፍጥነት መጠን ከሚጠቅሱባቸው የከተማ አካባቢዎች ውጭ የሚገኙ የትኛውም አካባቢዎች የተፈቀደው የማሽከርከር ፍጥነት ወሰን 50 መሆኑን፣ በገበያዎችና ሕዝብ በሚሰበሰብባቸው አካባቢዎች ወደ 30 ዝቅ ይላል ብለዋል።

‹‹ከፍጥነት ወሰንና ጠጥቶ ከማሽከርከር ጋር በተያያዘ ያሉ የትራፊክ ጥሰቶች ላይ አስተዳደራዊ ቅጣቶች የሚያስተላልፈው ደንብ ቁጥር 208/2011 ማሻሻያ ያስፈገዋል፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

እንደ አቶ ክበበው ማብራሪያ፣ በደንቡ መሠረት ለጠጥቶ ማሽከርከር የተቀመጠው ወሰን 0.8 ነው፡፡ ዓለም አቀፉ አሠራር ግን 0.5 ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘም ለከባድና ለሕዝብ መገልገያ ተሽከርካሪዎች አሽከርካሪዎች የሚፈቀደው የአልኮል መጠን ወደ 0.2 ዝቅ መደረግ እንዳለበት ጠቁመዋል።

‹‹ከራሳቸውም አልፎ በብዙ ሰዎች ሕይወት ላይ የሚወስኑ አሽከርካሪዎች የሚዳኙበት የሕግ ማዕቀፍ ቅጣት ከፍ ሊል ይገባል፤›› ሲሉ አቶ ክበበው ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...