Sunday, March 3, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅእንደነገርኩሽ ነው

እንደነገርኩሽ ነው

ቀን:

አፍሽም ለብቻው ስሙን እያወጣ

ጆሮሽም ለብቻው ስሙን እያወጣ

ወየው ወየው እንጂ ወዬ የሚል ታጣ

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

አምላክም እንደ ሰው

ባለመስጠት ሞላ ከመስጠት ጎደለ

ብጠራው ብጠራው አቤት አልል አለ

ማለትሽን ሰምቼ ምስኪን አመልሽን

ከመልክሽ አዛምደሽ ከምትጠረጥሪው

እስቲ ቅፅሉን ተይና በዋና ስም ጥሪው

ሰሚን ሲበድሉ ጠሪን ሲበድሉ

ለጌታም ቅፅል ስም አወጡለት አሉ

በልጥፍጥፍ መአት ዋናው ገፅ ፈረሰ

ስም አውጪው ሲበዛ አቤት ባይ አነሰ

አመሌን አመልሽን ለማያውቁ ሁሉ

ጠርቼው አልመጣም ትዪኛለሽ አሉ

እሷ የስም ሀብታም

ትጠራው አታጣ ትሸኘው አታጣ

እኔ ባለ አንድ ስም ምን ሰምቼ ልምጣ?

ሰሚን ሲያናንቁ ጠሪን ሲያቃልሉ

የስም ፋብሪካ ነው ጉራንጉሩ ሁሉ

እንደነገርኩሽ ነው

የላክሽው ፎቶ አንሺ

በጥላሽ ከልሎ ባንቺ ብርሃን ኩሎ

ፎቶ ነስቶኝ ሄደ ፎቶ አነሳሁ ብሎ

ፓ! ፓ! ፓ! ካሜራ ኧረረ !! ካሜራ

በሌሉበት ሁሉ ማንሳት የማይራራ

ሊያውም በክት ልብስ ጥለት አዛንቄ

ሊያውም በጀግና ልብስ በኒሻን ደምቄ

እያገላበጠ

ተዟዟርር እያለ ሲያነሳኝ ሰንብቶ

በትኖልኝ ሄደ ልብስ የሌለው ፎቶ

ካሜራሽ ስልጡኑ ካንቺ እኩል ያወቀ

ፎቶ ያነሳል አሉኝ ልብስ እያወለቀ

እንደነገርኩሽ ነው

የማንም ያልሆነን ያንተ ነው ተብዬ

በመሠለኝ ፋንታ ፍሬምሽን ሰቅዬ

ግራ የገባው አይን ከዕርቃን ይፋጠጣል

የጀግና ፎቶዬ የበዓል ፎቶዬ ከሱቅሽ ይሸጣል

አንቺ የመልክ ሀብታም ቀለም የተረፈሽ

አንቺ የልክ ሀብታም መስመር የተረፈሽ

የተኩላዎች ክፋት በበጎች ስም ፅፈሽ

መጥቀሻል ይሉኛል በምኞት መሠላል

ግድየለም ምጠቂ

ቅዠት ሲደጋገም ከህልም ይማሰላል

እንደነገርኩሽ ነው

ቧልተኛው ዶክተርሽ በስላቁ ፈዞ

አከምኩ ይለኛል

የራሱን መዳኒት ለመምተኛው አዞ

የመምተኛሽ ጉዳይ

የመምተኛው ደሞ

ከዶክተርሽ ባሰ ሁለቴ ገደለኝ

ተመረመርኩልህ ይቺን ዋጣት አለኝ

በታመመ ልኩ ጤና ሲሰፍርልኝ

በሽተኛ ልጅሽ ተመረመረልኝ

መድሃኒት ከሰረ

ጤና ተቃወሰ በሽታ ተስፋፋ

ግብረ ገብ ጎደለን ስነ ምግባር ጠፋ

ጉባኤ ሰብስበው ሰበብ ሲያዳምቁ

እኔን የገደለኝ

ከበሽታው ይልቅ በሽተኛው በውል አለመታወቁ

ያንቺዬማ አይነቱ

ማድማቱን ደብቆ

መድማቱን ለብቻ እያስመረመረ

ፈውስ በስም ብቻ ተድበስብሶ ቀረ

በኔ ና አንቺ አለም

ከማዘን ማሳዘን ከመሳት ማሳሳት

ከደም ማነስ ደም ማሳነስ

ከመርሳት ማስረሳት በእጥፍ ይቀድማል

ከህመሙ በላይ ህመምተኛው ያማል

ኧረ ያንቺስ ነገር

ትንሽ እየሰፋ ብዙ መቅደድ ያውቃል

ክርሽ ሳይነካ መርፌሽ ብቻ ያልቃል

ኧረ ያንቺስ አራጅ ቅርጫውን ሳንበላው

ያልቅብሻል አሉ ሞረድ እና ቢላው

ጎዳናው ሳይጠበን አመል እያጋፋን

እንኳን አካሄዱ አቋቋሙ ጠፋነ።

(በረከት በላይነህ)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...