Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ እየጨመረ የመጣው ፆታዊ ጥቃት

ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ እየጨመረ የመጣው ፆታዊ ጥቃት

ቀን:

አምራች በሆኑ ወጣቶች አሉታዊ ተፅዕኖ ያደርሳሉ ከሚባሉ ችግሮች መካከል የወጣቶች የሥነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎት ተደራሽ አለመሆን አንዱ ነው፡፡ ፆታዊ ጥቃት፣ ያለ ዕድሜ ጋብቻ፣ ያልታቀደና ያልተፈለገ እርግዝናም ተጠቃሽ ችግሮች ናቸው።

ምንም እንኳን ችግሩ በሁሉም ወጣቶች የሚከሰት ቢሆንም፣ በተለያዩ አካባቢዎች በሚቀሰቀሱ ግጭቶች ከቀዬአቸው ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ሴት ወጣቶች የበለጠ ተጋላጭ እንደሆኑ ‹‹ሜክ ዌይ›› አገር በቀል ያልሆነ ፕሮጀክት አስታውቋል።

 ፕሮጀክቱ ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመሆን ኅዳር 20 ቀን 2016 ዓ.ም. ባካሄደው የውይይት መድረክ፣ የሥነ ተዋልዶ ጤና ግንዛቤ ማነስ፣ እየደረሱ ስላሉ ፆታዊ ጥቃቶችና ተያያዥ ጉዳዮች የተነሳ ሲሆን፣ ለ16 ቀናት በሚቆየው ፆታዊ ጥቃትን መሠረት ያደረገ ንቅናቄ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ እንደሚኖር ተነግሯል።

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በተለያዩ ምክንያቶች የሚፈናቀሉ ወጣቶችና ሴቶች ፆታዊ ጥቃትን ጨምሮ ሌሎች አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ቀውሶች በስፋት እንደሚያጋጥማቸው በውይይቱ ወቅት ተመላክቷል፡፡

በተፈናቃይ መጠለያ ካምፖች ውስጥ እየደረሱ ያሉ ፆታዊ ጥቃቶች ሰፊ ሲሆኑ፣ በተለይ ደግሞ በአካል ጉዳተኞች ላይ ችግሩ የከፋ ነው ተብሏል።

በየአካባቢው ብዙ የአስገድዶ መደፈር ጥቃት ሰለባ የሚሆኑ ሴቶች እንዳሉ ቢታወቅም፣ አብዛኞቹ በወቅቱ ሪፖርት ባለመደረጋቸው ትክክለኛ አኃዙን ለማስቀመጥ አዳጋች እንደሆነም ተነግሯል።

አምራች የሆነው ወጣቱ የማኅበረሰብ ክፍል የሥነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎት የማግኘት ፍላጎቱ በጣም ከፍተኛ ቢሆንም፣ እንደ አገር እየቀረበ ያለው የሥነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎት ከፍላጎቱና ከወጣቶች ቁጥር ጋር የማይመጣጠን እንደሆነ የተናገሩት የፕሮጀክቱ ካንትሪ ዳይሬክተር አቶ ነጋሽ ባዱ ናቸው።

ወጣቶችና አካል ጉዳተኞች ፆታዊ ጥቃት በሚደርስባቸው ወቅት ጤና ጣቢያዎች ተገቢውን አገልግሎት ከመስጠት አንፃር ሰፊ ክፍተቶች ይታያሉ ያሉት አቶ ነጋሽ፣ በተለይ በተፈናቃዮች መጠለያ ማዕከላት ተጠልለው የሚገኙ ሴቶችና አካል ጉዳተኛ ወጣቶች ለችግሩ የበለጠ ተጋላጭ እንደሆኑ ጠቁመዋል፡፡

 ዳይሬክተሩ አንዳንድ ጥናቶችን ዋቢ አድርገው እንደተናገሩት፣ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላና በአገሪቱ እየታየ ካለው ግጭት ጋር ተያይዞ የአስገድዶ መድፈር፣ ያለ ዕድሜ ጋብቻና ያልታቀደ እርግዝና ከአምስት እስከ ስድስት እጥፍ ጨምሯል።

በአካል ጉዳተኞች ላይ የሚደርሰው ጥቃት በዚሁ ልክ ጨምሯል ብለዋል። ማንኛውም ጥቃት ከመፈጸሙ በፊት ድርጅታቸው ተጋላጭ የሆኑትን ወጣቶች በመለየት እንዴት መከላከልና ጥቃቱ ከደረሰባቸው በኋላ ወደት መሄድ እንዳለባቸው የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራን እንደሚሠሩ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ፆታዊ ጥቃት እየተበራከተ መጥቷል የሚሉት ደግሞ የኢትዮጵያ ሴት አካል ጉዳተኞች ማኅበር አባል ወ/ሮ ባንችጊዜ አዳነ ናቸው።

‹‹ፆታዊ ጥቃት በአካል ጉዳተኞች ላይ ከሁሉም የከፋ ነው፤›› የሚሉት ባንችጊዜ፣ ብዙ ጊዜ ጥቃቱ የሚደርሰው በቅርብ ሰዎችና በቤተሰብ በመሆኑ ችግሩን እንዳከበደው አክለዋል።

ስለ ተፈጸመው ጥቃት ለአካል ጉዳተኞችም ሆነ ለጤነኞች ወጥቶ ለመናገር አስቸጋሪ ነው፣ ምክንያቱም ለማንና ወዴት እንደሚጮህ የሚታወቅና የተመቻቸ መንገድ አለመኖሩ አስቸጋሪ ያደርገዋል ሲሉም ተናግረዋል።

በሌላ በኩል መንገዶችን ጨምሮ ሌሎች የአገልግሎት መስጫ ተቋማት አካል ጉዳተኞችን መሠረት ያደረጉ አይደሉም፣ በዚህም ብዙዎች ካሰቡትና ከተመኙት ለመድረስ ትልቅ ፈተና እየሆነባቸው ነው ብለዋል።

ምንም እንኳን ስለ አካል ጉዳተኞች ሕገ መንግሥቱ መብትና ጥቅሞችን ቢገልጽም፣ ተፈጻሚነቱ ከታች ባለው ሠራተኛ ይሁንታ ላይ የተመረኮዘ በመሆኑ፣ ሕጎች ተጨምረውበት ቢሻሻልና ተግባራዊነቱ ቢፈተሽ መልካም ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...