Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
እኔ የምለዉበዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ቀን:

  • ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ

በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር)

በየዓመቱ ኅዳር 21 ቀን 2016 ዓ.ም. በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ያጡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን እንዘክራለን::

በዚህ አጋጣሚ በአፅኖት ማስታወስ ያለብን ባለፉት ሃያ ዓመታት በጋራ ባደረግነው ከፍተኛ ጥረት ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ውጤት ብናስመዘግብም፣ በዚህ ወቅትም ጥቂት የማይባሉ የማኅበረሰብ ክፍሎች በቫይረሱ በመያዝና ተያያዥ በሆኑ ችግሮች ተፅዕኖ ሲደርስባቸው ይስተዋላል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ከፊታችን የሚጠብቀን ሥራ አነስተኛ ባይባልም ለማስተላለፍ የምፈልገው መልዕክት የመጣውን ለውጥና የተሳካ ጉዞ እያስታወስን፣ ያጣናቸውን ውድ ሕይወቶች በማሰብ ዓላማችንን ከግብ ለማድረስ በጋራ ለመሥራት ቁርጠኛ መሆን እንደሚጠበቅብን ነው፡፡

ባለፉት ሃያ ዓመታት የአሜሪካ መንግሥት የዓለም አቀፍ የኤችአይቪ/ኤድስ ሥርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ፣ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ (ፔፕፋር) የተሰኘውን ፕሮግራም በመቅረፅ የቫይረሱን ሥርጭት ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት በከፍተኛ ሁኔታ ሲደግፍ ቆይቷል፡፡ በዚህም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሃያ ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የፀረ ኤችአይቪ ሕክምናና ክትትል እንዲያገኙ አስችሏል::

በተመሳሳይ በኢትዮጵያም የአሜሪካ መንግሥት በፔፕፋር በኩል እ.ኤ.አ. ከ2004 ጀምሮ ወደ ሦስት ቢሊዮን ዶላር በመመደብ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚደረገውን ጥረት በከፍተኛ ሁኔታ ሲደግፍ ቆይቷል። በዚህም ከ470 ሺሕ በላይ ወንዶች፣ ሴቶችና ሕፃናት የፀረ ኤችአይቪ መድኃኒት እንዲያገኙ ድጋፍ በማድርግ ላይ ይገኛል፡፡

በተጨማሪም በየዓመቱ ከ350 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ ወላጆቻቸውን በኤችአይቪና ተያያዥ ምክንያቶች ላጡ ሕፃናት ሁሉን አቀፍ የሆነ የኤችአይቪ መከላከል፣ ሕክምና፣ የሥነ ልቦና፣ ማኅበራዊ፣ እንዲሁም የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ይህም ጥረት ኤችአይቪ የማኅበረሰብ ጤና ቀውስ ሆኖ እንዳይቀጥልና ሥርጭቱን በመግታትና በመቆጣጠር እ.ኤ.አ. በ2030 ለማሳካት ያስቀመጥነውን የጋራ ግብ ለመምታት እንደሚያግዝ አምናለሁ፡፡

የአሜሪካ የዓለም አቀፍ የጤና ጥበቃና የውጭ ግንኙነት አምባሳደር የሆኑት ዶ/ር ጆን ንኬይጋሶንግ በቅርቡ በዚሁ ላይ አፅንኦት በመስጠት ይህንን የጋራ ግብ ለመምታት በጋራ በትብብር ለመሥራት፣ ከምንጊዜም በላይ ትኩረት መሰጠት ያለበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ለዚህም የመንግሥታት፣ የማኅበረሰብ፣ የሲቪክ ማኅበራት፣ የሃይማኖት ተቋማትና የግል ተቋማት ሚና ከፍተኛ ሲሆን በጋራ ያስቀመጥነውን ሕይወትን የማዳን፣ በሽታውን በመከላከልና በመቆጣጠር ዙሪያ ለምናደርገው ጥረት በአንድነት መሥራት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡

ፋር አገሮችና ማኅበረሰቦች ኤችአይቪን በመከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ የሚሠሩትን ሥራዎች በመደገፍና የጤና አገልግሎት መስጫ ተቋማትን በማጠናከር ሌሎች መሰል የኅብረተሰብ ጤና ችግሮችን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና የተሻለ አገልግሎት አሰጣጥ የሚያስችል አቅም እንዲያጎለብቱ ማድርግ ተችሏል፡፡ በተጨማሪም ይህንን የጋራ የሆነውንና በ2030 ለማሳካት ያስቀመጥነውን የጋራ ግብ ለማሳካት ይቻል ዘንድ ፔፕፋር ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የሚሆን ዕቅድ በመንደፍ እየሠራ ሲሆን፣ በዚህም በአምስት ዋና ጉዳዮች ላይ በማተኮር ሙሉ፣ ተደራሽ፣ አስተማማኝና ቀጣይነት ያለው የጤና አገልግሎት ሥርዓትን በአጋርነት በመገንባት፣ ሳይንሳዊ ምርምሮችን በማሳደግ፣ እንዲሁም የማኅበረሰቡን ተሳትፎና የአመራር አቅም በማሳደግ፣ የጤና መረጃን በዘመናዊ መንገድ በማደራጀትና ለውሳኔ ግብዓትነት በመጠቀም ከጤና ሚኒስቴርና ከሌሎች አጋሮች ጋር በቅርበት እየሠራ ይገኛል፡፡

እኩል የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ማዕከል በማድረግ ፔፕፋር ኤችአይቪን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያደርገውን ጥረት ከምንጊዜውም በበለጠ በመቀጠልና የጤና አገልግሎት መስጫ ተቋማትን በማጠናከር የሚያደርገውን ድጋፍ ይቀጥላል፡፡

ፔፕፋር እስካሁን አጋርነትንና ትብብርን በዋናነት በማስቀደም ለኢትዮጵያ መንግሥት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ በመቀጠል፣ በተለይም በግጭት ለተጎዱ አካባቢዎች የተለየ ትኩረት በመስጠት የኤችአይቪንና ቲቢ በሽታን ለመከላከል የሚከናወኑ ሥራዎችን በመደገፍ አገሪቱ ኤችአይቪን ለመቆጣጠር የምታደርገውን ጥረት በመደገፍ የጋራ ግቦቹን ለማሳካት ይሠራል፡፡

በዚህ ዕለት በዓለም አቅፍ ደረጃ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎችን ስናስብ፣ በሽታውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የምናደርገው ጥረትና ያስመዘገብናቸው ስኬቶች ከምንጊዜውም በላይ የጋራ ግባችንን ለማሳካት መቃረባችንን ያመለክታሉ፡፡ ፔፕፋር ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ያለውን አጋርነት ይበልጥ በማጠናከርና ኤችአይቪን በመቆጣጠር ግባችን የሆነውን ከኤድስ ነፃ የሆነ ማኅበረሰብ የመገንባት ህልማችንን ዕውን በማድረግ ለመላው ኅብረተሰብ ምቹና የተሻለ ሁኔታ ለመፍጠር እንተጋለን፡፡

ከአዘጋጁ፡- ጸሐፊው በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ሲሆኑ፣ ጽሑፉ የእሳቸውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...