Friday, March 1, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

[ክቡር ሚኒስትሩ የሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸማቸውን ለተከበረው ምክር ቤት ካቀረቡ በኋላ ከምክር ቤቱ አባላት የሚነሱ ጥያቄዎችን እየተቀበሉ ማብራሪያ በመስጠት ላይ ናቸው]

 • ክቡር ሚኒስትር መንግሥት ለሕዝብ ይፋ ያደረገው ነገር ከምን እንደደረሰ ቢያብራሩልን?
 • ምንድነው ይፋ ያደረገው? ጥያቄውን ትንሽ ቢያብራሩት?
 • ከአራት ዓመት በፊት በኦጋዴን አካባቢ ነዳጅ መገኘቱን ለሕዝብ በቴሌቪዥን አብስሮ ነበር።
 • እህ።
 • ነገር ግን ይህ ጉዳይ ምን ደረጃ እንደደረሰ የሚታወቅ ነገር የለም። በዚህም ምክንያት ሕዝባችን ለጥርጣሬና ለተዛቡ መረጃዎች ተጋልጧል።
 • እህ…
 • ክቡር ሚኒስትር እኛም እንደ ሕዝብ ተወካይ ማወቅ ይገባናል።
 • ትክልል ነው።
 • ስለዚህ ክቡር ሚኒስትር ነዳጁ ይመረታል ወይስ አይመረትም? የሚለውን ማብራሪያ ቢሰጡበት ለማለት ነው።
 • ጥሩ። እንደምታውቁት ወደዚህ ኃላፊነት ከተመደብኩ ገና አንድ ዓመት ተኩል ቢሆነኝ ነው።
 • አንድ ዓመት ተኩል ብዙ ሊመስል ይችላል። ነገር ግን ከዘርፉ ስፋት አንፃር ሁሉንም ጉዳዮች ለማወቅ በቂ አይደለም።
 • ክቡር ሚኒስትር ቅድም እኮ ስለኖራ ምርት ሲያብራሩልን ነበር?
 • አዎ። ስለኖራ ጉዳይ አብራርቻለሁ።
 • ታዲያ ስለ ኖራ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተው እንዴት ስለ ነዳጅ መረጃ አይኖርዎትም?
 • እኔ ወደዚህ ኃላፊነት ከተመደብኩ ገና አጭር ጊዜ በመሆኑ በቂ መረጃ የለኝም። እንደዚያ ማለቴ ግን ባልደረቦቼ ምላሽ አይሰጡበትም ማለት አይደለም።
 • እንደዚያ ከሆነ ጥሩ። እኔ የሚያልፉት መስሎኝ ነው ክቡር ሚኒስትር።
 • አይደለም። የተከበረው ምክር ቤት ጥያቄማ ምላሽ ማግኘት አለበት። ስለዚህ ክቡር ሚኒስትር ደኤታው እዚሁ ስላሉ ዕድሉን ለእርሳቸው እሰጣለሁ።
 • ክቡር ሚኒስትር፣ እኔ እኮ እርስዎ ከተመደቡ በኋላ ነው ወደዚህ ኃላፊነት የመጣሁት?
 • አንተን ማለቴ አይደለም። ተቀዳሚ ሚኒስትር ደኤታውን ማለቴ ነው?
 • ክቡር ሚኒስትር እኔም መረጃው የለኝም።
 • እንዴት?
 • ክቡር ሚኒስትር እኔም እርስዎ ከመሾምዎ ስድስት ወራት አስቀድሞ ነው የተመደብኩት?
 • ለማንኛውም በእኛ በኩል የምክር ቤቱ ጥያቄ ምላሽ ማግኘት እንዳለበት እናምናለን።
 • በኦጋዴን ነዳጅ ተገኝቷል ወይስ አልተገኘም የሚለውን የተከበረው ምክር ቤት ጥያቄን እንደ ግብዓት ወስደን በቀጣይ ማብራሪያ የምንሰጥበት ይሆናል።
 • እኛ ሳናውቀውና ፈቃድ ሳንሰጥ ነዳጅ ሊመረት እንደማይችል ግን የተከበረው ምክር ቤት እንዲረዳ እንፈልጋለን።

[ክቡር ሚኒስትሩ በመኖሪያ ቤታቸው ከባለቤታቸው ጋር የምሽቱን የቴሌቪዥን ዜናዎች እየተከታተሉ ሳለ ባለቤታቸው በተመለከቱት አንድ ዜና ላይ ጥያቄ አነሱ]

 • እኔ ምልህ?
 • እ…?
 • ይኼ ነገር ተደጋግሞ ሲነገር እስማለሁ ግን ምን እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም።
 • የቱ ነገር?
 • አሁን ቴሌቪዥኑ ላይ የተነገረው ዜና?
 • ውይ አላስተዋልኩትም… ስለምን ጉዳይ የተወራውን ማለትሽ ነው?
 • ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የሚለው ዜና፡፡
 • እ… ስለሱ ምንድነው ያልገባሽ?
 • ኢትዮጵያ ታምርት ማለት ምንድነው? አሁን እየተመረተ አይደለም እያላችሁ ነው?
 • ፈጽሞ ከዚያ ጋር አይገናኝም።
 • እና ምን ለማለት ነው?
 • ከውጭ የሚገባ ምርትን በአገር ውስጥ ለመተካት የተጀመረ ብሔራዊ ንቅናቄ ነው።
 • እንደዚያ ነው እንዴ?
 • አዎ። ምክንያቱም እዚሁ ሊመረት የሚገባ ምርትን ከውጭ በማስገባት አገሪቱ የምታገኘውን አነስተኛ የውጭ ምንዛሪ ማመናመን መቆም አለበት በሚል መነሻ የተጀመረ ንቅናቄ ነው።
 • ኦው ይኼማ የሚደነቅ ሐሳብ ነው።
 • እስኪ አስቢው …የመቶ ሚሊዮን ሕዝብ አገር ክብሪት በዶላር ከውጭ ስታስገባ?
 • ልክ ነህ፣ በጣም ያናድዳል።
 • በጣም በቀላሉ በአገር ውስጥ ሊመረቱ የሚችሉ ምርቶችን ከውጭ ማስገባት ማቆም አለብን ብለን የጀመርነው ነው።
 • ውጤቱ ግን እንዴት ነው?
 • ይገርምሻል ገና ከጅምሩ ብዙ ምርቶችን ነው በአገር ውስጥ ማምረት የቻልነው።
 • አትለኝም?
 • በቁም ነገር ነው የምልሽ።
 • እስካሁን ምን ዓይነት ምርቶች ተተኩ?
 • ለምሳሌ የሠራዊቱን ጫማና ዩኒፎርሞች ሙሉ በሙሉ በአገር ውስጥ ምርት መተካት ተችሏል።
 • ምን?
 • ምነው ደነገጥሽ?
 • አይ… ትልልቅ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ታደርጋላችሁ ብዬ ገምቼ ስለነበረ ነው።
 • ትልልቅ ጉዳዮች ማለት?
 • ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚያስወጡ ምርቶች ላይ ማለቴ ነው።
 • ለምሳሌ ምን?
 • ያው አሁን ላይ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እየወጣ ያለው የጦር መሣሪያ ግዥ ላይ ነው።
 • ጦር መሣሪያ ነው ያልሽው?
 • አዎ።
 • ስለዚህ?
 • እሱን መተካት ነዋ?
 • በምን?
 • በአገር ውስጥ ምርት!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...

የጋራ ድላችን!

ከፒያሳ ወደ ቄራ ልንጓዝ ነው። ለበርካታ ደቂቃዎች ሠልፍ ይዘን...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ ነው የሚደንቀው? የልደታ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ሕዝባዊ ውይይት ላይ ምን ጉዳዮች ተነሱ? በአስማት ነው የምንኖረው ሲሉ ቅሬታቸውን...

[ክቡር ሚኒስትሩ የካቤኔ አባል የሆኑት አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያዳመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል አግኝቼ ላነጋግርዎት የፈለግኩት። ጥሩ አደረክ። ምን አሳሳቢ ነገር ገጥሞህ ነው? ክቡር ሚኒስትር ተወያይተንና ተግባብተን ያስቀመጥናቸው አቅጣጫዎች፣ በተለይም...

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት ሞባይል ስልካቸው ላይ አተኩረው ሲመለከቱ ቆይተው፣ በድንገት ካቀረቀሩበት ቀና ብለው ባቤታቸውን ጠየቁ]

ምን ጉድ ነው የማየው? ምን ገጠመሽ? የመንግሥት ሚዲያዎች የሚያሠራጩት ምንድነው? ምን አሠራጩ? አልሰማህም? አልሰማሁም፣ ምንድነው? ዳግማዊ አፄ ምኒልክ መልዕከት አስተላለፉ እያሉ ነው እኮ። እ... እሱን ነው እንዴ? አዎ። የምታውቀው ነገር አለ? አዎ። የዓድዋ...